Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል። በ | Brand watches and bags shop 2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል።

በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው።

በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።

በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

@newsetv