Get Mystery Box with random crypto!

“የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወ | Brand watches and bags shop 2

“የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
*************
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ የስግብግቡ ጁንታ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ እጁን ለመከላከያ በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል።

በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነዋል።

አሁን ግን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር እንደሚከናወን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገለፁት።

@newsetv