Get Mystery Box with random crypto!

Maranatha Digital Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ maranatha_fellowship — Maranatha Digital Network M
የቴሌግራም ቻናል አርማ maranatha_fellowship — Maranatha Digital Network
የሰርጥ አድራሻ: @maranatha_fellowship
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.19K
የሰርጥ መግለጫ

#Maranatha_digital_Network #youth center #spreading the gospel of the lord Jesus Christ #christian living #Christian fellowship
Follow us on:-
instagram : maranatha_fellowship
facebook: maranathafellowshipEthiopia
Telegram group @Maranatha_Fellowship2

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 15:57:28
#MDN_BIBLE_VERSE

#የእግዚአብሔር_ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን #ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ”
— 1ኛ ዮሐንስ 3:1

|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
1.1K viewsBĚ ĤØPÊ, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 05:56:49ጥያቄ አለኝ✷

◗እግዚአብሔር አብ በውድ ልጁ እኔን፣ አንተንና አንቺን የወደደበትን ጥልቅ ╣ፍቅር╠ የትኛው ርቱዕ አንደበት ይገልፃል
◗በሀሳብ ምጥቀት በንግግር ብልሃት ይሄንን 。♡#ፍቅር♡。 ደርሶ ማን ሊያብራራው ይችላል
◗የአንድ አይደለም የአለም ቋንቋዎች ሁሉ ተናጋሪ፤ ሁሉን አዋህዶ ከሁሉም ቋንቋዎች ቃላትን ተውሶ ለቀናት፣ ለወራት ወይንም ለዓመታት ሳይሆን ዘላለም ስለ ፍቅሩ አውርቶ የሚጠግብ ማነው
◗የዚህ ድንቅ 灬ºፍቅርº አቻ ገለፃ የቱ ነው

☞የትኛው ወዳጅ ነው እኔ ጠላቱ በተወደድኩበት መወደድ መጠን የተወደደ
☞የትኛው አፍቃሪ ለነፍስ ነፍሱን ሳይሰስት ሰጠ
☞የማን ቁስል በአምላክ ቁስል ፈውስን አገኘ
☞የማንስ የጽድቅ ልብስ ነው ያለልብስ ዕርቃኑን በእንጨት በተቸነከረ ጌታ የተገኘ

#ብዙ_ምህረት_የተትረፈረፈ_ጸጋ_ከመንፈሳችሁ_ጋር_ይሁን አሜን
ARANATHA DIGITAL NETWORK
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
1.2K viewsBemnet Ermias, 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 13:36:52
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ከዚህ ቀደም በቻናላችን እንደሚታወሰው '#'አማኝ_በምን_ይሸለማል?'' የተሰኘ ትምህርት በቅርቡ ማለቁ አይዘነጋም። በትምህርቱ ውስጥ ተጠቅሰው ስለነበሩት የክርስቶስ #የፍርድ_ወንበር(Bema) ፍርድ እና #የታላቁና_የነጩ_ዙፋን(Thronos) ፍርድ ልዩነት በምስል የተገለጠውን በጥንቃቄ እናስተውል መልዕክታችን ነው።

#የክርስቶስ_ጸጋና_ምህረት_ይብዛልን

ARANATHA DIGITAL NETWORK
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
2.1K viewsBĚ ĤØPÊ, 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:16:00
“... ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም.....” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥50
በዚህ ጥቅስ መሠረት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
40%
የሚወርሰው እውነተኛው ማንነታችን መንፈሳችን ሲሆን ስጋ ደግሞ በምድር ብቻ የሚኖርና ከሞት በኃላ ጥቅም የሌለው ነው።
17%
ከትንሣኤ በኋላ የሚኖረን አካል ሥጋ እና ደም የሌለው ነው።
8%
ምንም ያህል የእግዚአብሔር ርስት ተካፋዮች ብንሆንም ከስጋችን የተነሳ ከእግዚአብሔር መንግሥት ልንጎድል እንችላለን።
36%
የሰማይን ክብር የሚመጥን አካለ-ሰውነት በትንሣኤ ጊዜ እንደምንካፈል ያረጋግጣል።
213 voters2.5K viewsBemnet Ermias, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 12:57:02 አማኝ በምን ይሸለማል?
ክለሳ እና ማጠቃለያ
☞በመልካም ሥራ አኳያ ስጦታ በሆነው ድነትና ሽልማት መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት የሚያወሳ ነው።

☞ከዚህም ጋር አያይዞ ስለእግዚአብሔር ቍጣና የኃጢአት ስርየት፣ ስለ ትሮኖስ (ታላቁና ነጩ ዙፋን ፍርድ) እና ስለ ቤማ (የክርስቶስ ፍርድ ወንበር) እንዲሁም ስለፊተኛውና ኋለኛው ትንሣኤ ጥቂት ማብራሪያ ያዘለ ነው።

☞ከዚህም በተጨማሪ ቅዱሳን በዙሪያቸው ያለውን እያዩ ከመድከም ይልቅ ምንም ያህል የሰዎች ምላሽ ተገቢ ባይሆንም በቅንነት እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ ለማነሳሳት ይሁን..

ስለመዳንና ስለሽልማት አጠር ያለ መግለጫ በድምፅ ለማስቀመጥ ተሞክሯል... ሁሉም እንዲሰማው በጌታ ፍቅር ጥሪዬን አቀርባለሁ

ጸጋ ላይ ጸጋ ይብዛልን፤ አሜን።
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
649 viewsBemnet Ermias, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 12:42:27
#MDN_BIBLE_VERSE

“ከማመስገን ጋር #ነቅታችሁ_በትጋት ጸልዩ።”
— ቆላስይስ 4፥2 (አዲሱ መ.ት)

|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
2.2K viewsCUP 10 »»»»»»»»»»»», edited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 22:53:41 አማኝ በምን ይሸለማል?
ክፍል-11
በአዲሱ ኪዳን በአክሊል የተሰየሙ ለአማኞች የሆኑ 5 ሽልማቶች ይገኛሉ። እነርሱም:–

የድል አክሊል
☞ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የማይጠፋ/የማይበላሽ አክሊል ብለው ይጠሩታል። ሐዋርያው ጳውሎስም ይሄንን አክሊል በጨዋታ ከሚታገል ስፖርተኛ ጋር አያይዞ ያነሳል [1ቆሮ. 9÷25-27፤ 2ጢሞ. 2÷5]።

☞በጊዜው በግሪክ ለሚካሄደው ታላቅ ውድድር (Olympic game) ተወዳዳሪው ከትግሉ ቀደም ብሎ ለ10 ወራት ያህል የዝግጅት ልምምድ ያደርግ ነበር። በእነዚህም ወራት የስፖርት ህጉ በሚፈቅደው መሠረት አስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል፤ የሚመገበውም በታዘዘው አይነት እና መጠን ብቻ እንጂ #የፈለገውን_የመብላት_መብት_አይኖረውም። በእነዚህም ጊዜያት ተወዳዳሪው ለራሱ ፈቃድ እና ፍላጎት ሳይሆን ለስፖርቱ ሕግ በመገዛት ራሱን ከተለያዩ ነገሮች ማቀብ ግድ ይለዋል። ይህም ብዙ ነገሮችን #አይ! #አያስፈልግም” ማለትን ይጠይቃል።

☞በሚያልፈው ምድራዊ ነገር ይልቅ በሰማያዊው ነገር ትኩረታቸው ተወስዶ ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር በማስገዛት ስጋቸውን እየጎሰሙ የተስተካከለ ኑሮ በመኖር የታመኑ አማኞች ሁሉ ይህን የማይጠፋውን የድል አክሊል ይሸለማሉ።

የጽድቅ አክሊል
☞ይህ መልካም ሥራ በመስራት የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም ለሚጣጣሩ ትዕቢተኞች የሚሰጥ ክፊያ አይደለም። በራስ ጥረት የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለመደለል መሞከር የከንቱ ከንቱ ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ የሰው ልጅ ሊረዳው የማይችል ዋጋ የተከፈለበት ነገር ግን በነፃ የሚሸመት እጅግ ውድና ከክፊያ ደርዝ ያለፈ በስራ ያይደለ በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ የሆነ ነው።

የጽድቅ አክሊል የጌታ ኢየሱስን በክብር መገለጥ /መምጣት/ በናፍቆት ለሚጠባበቁ ቅዱሳን ሁሉ የሚሰጥ ነው። እነኚህ አማንያን ከጌታ ጋር ለመሆንና ፊቱን ፊትለፊት ለማየት እጅግ ጉጉት ያደረባቸው ናቸው። [2ጢሞ. 4÷7–8]
በተጨማሪም ጳውሎስ ይህ የጽድቅ አክሊል እንደተዘጋጀለት የተናገረው ሩጫውን እንደሚገባ እስከመጨረሻ በመሮጡ ነው።
✪#ሩጫውን የሚለው ቃል ጳውሎስ የራሱን ሳይሆን በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ የክርስቶስ ሐዋርያ በመሆን የሮጠውን የወንጌል አገልግሎት ሩጫ የሚያመላክት ነው።

የሕይወት አክሊል
☞ይህ የዘላለም ህይወትን የሚያመለክት አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል። የዘላለም ሕይወት አማኞች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ብቻ ያገኙት የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው እንጂ በመልካም ሥራ የሚመጣ እንዳይደለ የክርስትና እምነት አብይ/ወሳኝ ትምህርት ነው። #ደህንነት_ከእግዚአብሔር_ቍጣ_የዳንንበትና_እግዚአብሔር_ራሱ_ከራሱ_ጋር_ልያስታርቀን_ወዶና_ፈቅዶ_የራሱን_ውድ_ልጅ_በእኛ_ምትክ_በመሠዋት_የተገኘ_እንደሆነ_የማያስተምር_የትኛውም_ትምህርት_የክርስቶስን_ወንጌል_በቀጥታ_የሚፃረር_ኑፋቄ_ነው

የሕይወት አክሊል ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር የተነሳ ስለክርስቶስ ወንጌልና ስለእምነታቸው በልዩልዩ ፈተናዎች የተፈተኑና እስከሞት ድረስ የታመኑ (ሰማዕት የሆኑ/ የተሰው) ቅዱሳን ሁሉ ከጌታ ዘንድ የሚቀበሉትን ብድራት ያመለክታል [ያዕ.1÷12፤ ራዕይ 2÷10]።

የደስታ አክሊል
☞ብዙን ጊዜ “ነፍሳትን ያሸነፉ /የማረኩ/ የሚቀበሉት አክሊል”»» “Soul-winner's Crown” በመባል ይታወቃል። ይህ አክሊል ወንጌልን ላልሰሙ ሰዎች በማድረስ የተሰማሩ እና አማኞችን (በተለይም አዳዲስ አማኞችን) በሚገባ እንዲመላለሱ ወይንም የደቀመዝሙርነትን ህይወት እንዲገልጡ የሚያስተምሩ ሁሉ ከጌታ ዘንድ የሚቀበሉት ብድራት ነው። [1ተሰ. 2÷19–20]

የክብር አክሊል
☞ይህ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንጋ በመጠበቅ የታመኑ እረኞች /መሪዎች/ የሚቀበሉት ብድራት ነው [1ጴጥ. 5÷4]። ቤተክርስቲያን (ቅዱሳን) ከትምህርት መፍገምገም/ መንገዋለል /ግራመጋባት ተጠብቃ በእግዚአብሔር ቃል ተኮትኩታ እንዲታድግ /ከመንፈሳዊ ህፃንነት እንድትወጣ/ በመትጋት የታመኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች (ሽማግሌዎች) ከጌታ ዘንድ የሚሰጣቸውን ሽልማት /ዋጋ ያመለክታል።

የጌታ ጸጋና ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
4.8K viewsBemnet Ermias, 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 22:07:16 ፍቅር እንደዚህ ነው

በአንድ ወቅት የባቡር ሀዲድ መስመር ተቆጣጣሪ ሆኖ የሚሰራ አንድ ግለሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰው የሚቆጣጠረው መንገድ... ባቡር ካልመጣ ከታች ለሚያልፉ መኪኖች ክፍት የሚደረግና ባቡር ከመጣ ለባቡሩ የሚዘረጋ ተታጣፊ መንገድ ነው፡፡ ይህም የዘውትር ምግባሩ ነው፤ የየዕለት ስራውን የሚሰራው ይኸው ሰው በአንዲት ቀን እንደተለመደው ማልዶ ተረኛ ስለነበር ወደ ሥራው ይሄዳል።

ቀትር ላይ የትምህርት ጊዜውን ጨርሶ ከአባቱ ጋር ወደ ቤት ሊመለስ የመጣው የሚወደውና እንደብሌኑ የሚሳሳለት በስትርጅናው የወለደው አንድ ልጁ ይመጣል። የሥራ መውጫ ሰዓቱ ገና ስለነበር ልጁን አንዲጫወት ነግሮት፤ ወደ ሥራው ይመለሳል። ከውጪ ሆኖ የሚጫወተውን ልጁን ትኩር ብሎ በመስኮት የሚመለከተው አባት ሀሳብ ወሰደው፤ ድንገት ከሀሳቡ ላይ የባቡር መምጣት ምልክት ደውል አስባነነው። በዚህን ጊዜ ለመወሰን ከባድ የሆነ ችግር ገጠመው፤ እየታጠፈ በሚዘረጋው መንገድ ስር ልጁ ይጫወት ነበር አሻግሮም ሲያይ ባቡር እየመጣ ነው፡፡ መንገዱን ካልዘረጋ ባቡሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይሞታሉ ከዘረጋው ደግሞ ልጁ ሊሞትበት ነው፡፡ አሁን አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ያ የሚሳሳለትና የእርጅና ልጁ አይከለክለው ነገር ርቋል ባቡሩን እንዳያስቆመው እየፈጠነ ነው.....
የማጠፊያና የመዘርጊያውን አዝራር(Button) ይዞ ግራ እንደተጋባ ቆሞ ነው ያለው... አሁን ባቡሩ እየቀረበ ነው አዝራሩን ካልተጫነ ስለነገሩ የማያውቁት ማለቃቸው ነው በዚህም ተጨነቀ በሌላ በኩል ደግሞ ንጹሁና ምስኪኑ ልጁ አለ። በዚህን ጊዜ መወሰን ግድ ሆነበት፤ እያነባና እያዘነ አንድ ውሳኔ ለመወሰን ተገደደ ይህም ውሳኔ ልጁ ላይ ስለነዚያ ባቡሩ ውስጥ ስለሚገኙት ያባትዬውን ጭንቅ ስለማያውቁት አዝራሩን(Button) በመጫን ተሳፋሪዎቹን ማዳን ሆነ፡፡ በብዙ ጭንቅ ሆኖ አዝራሩን ተጫነ፤ መንገዱም ተዘርግቶ ብቸኛ ልጁን ጨፈለቀው። ባቡሩም ውስጥ ያሉት የተደረገላቸውን ሳያውቁ በልጁ ሞት ተሻገሩ። ባቡሩ እንደተሻገረ ሰውዬውም የልጁ አስክሬን ወዳለበት ሮጠ ደርሶም የልጁን አጥንትና ደም እየደባበሰ ማልቀሱን ተያያዘው። ዳሩ ግን በባቡሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ባቡሩ በልጁ ላይ ተረማምዶ ሲሻገር ለነበረው መንገራገጭ ትኩረት ሰጡ። ያ ልጁን ያጣው አባት ግን ያውቀዋል ስቃዩን ዋጋውን፡፡

ዛሬ እኛም ብንሆን እንደ ባቡር ተሳፋሪዎቹ በእግዚአብሔር ፍቅር በልጁ ሞት ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተሻገርን ሰዎች ነን፡፡ የዳንነው በነጻ ቢሆንም ዋጋው ውድ አባትና ልጅ የሚያውቁት ስቃይ ነው።

ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
—1ኛ ዮሐ.4:10


.Maranatha Digital Network. @Maranatha_Fellowship @Maranatha_Fellowship2
3.7K viewsYOKABID 4ME, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 11:47:36
#MDN_BIBLE_VERSE

"#ስትንፋስ_ያለው_ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። #ሃሌ_ሉያ።"
-መዝሙረ ዳዊት 150:6

|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
2.5K viewsBĚ ĤØPÊ, 08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 13:18:16
ቀጥለው ከቀረቡት አማራጮች መካከል ስለ ሕይወት አክሊል ትክክል የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
18%
A. ወደፊት ከጌታ እጅ የምንቀበለውን የዘላለምን ህይወት ያመለክታል።
14%
B. በክርስቶስ ድነትን ያገኙ ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዳላቸው ማሳያ ተደርጎ ይሰጣቸዋል።
21%
C. በሕይወታቸው ዘመን የጌታን መምጣት በንቃት በመጠባበቅ የኖሩ ቅዱሳን የሚቀበሉትን ብድራት ያመለክታል፡፡
47%
D. ስለወንጌል መከራ የደረሰባቸውና በልዩልዩ ፈተናዎች ያለፉ ቅዱሳን ከጌታ የሚቀበሉት ብድራት ነው።
245 voters2.7K viewsYOKABID 4ME, 10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ