Get Mystery Box with random crypto!

አማኝ በምን ይሸለማል? ክፍል-11 በአዲሱ ኪዳን በአክሊል የተሰየሙ ለአማ | Maranatha Digital Network

አማኝ በምን ይሸለማል?
ክፍል-11
በአዲሱ ኪዳን በአክሊል የተሰየሙ ለአማኞች የሆኑ 5 ሽልማቶች ይገኛሉ። እነርሱም:–

የድል አክሊል
☞ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች የማይጠፋ/የማይበላሽ አክሊል ብለው ይጠሩታል። ሐዋርያው ጳውሎስም ይሄንን አክሊል በጨዋታ ከሚታገል ስፖርተኛ ጋር አያይዞ ያነሳል [1ቆሮ. 9÷25-27፤ 2ጢሞ. 2÷5]።

☞በጊዜው በግሪክ ለሚካሄደው ታላቅ ውድድር (Olympic game) ተወዳዳሪው ከትግሉ ቀደም ብሎ ለ10 ወራት ያህል የዝግጅት ልምምድ ያደርግ ነበር። በእነዚህም ወራት የስፖርት ህጉ በሚፈቅደው መሠረት አስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል፤ የሚመገበውም በታዘዘው አይነት እና መጠን ብቻ እንጂ #የፈለገውን_የመብላት_መብት_አይኖረውም። በእነዚህም ጊዜያት ተወዳዳሪው ለራሱ ፈቃድ እና ፍላጎት ሳይሆን ለስፖርቱ ሕግ በመገዛት ራሱን ከተለያዩ ነገሮች ማቀብ ግድ ይለዋል። ይህም ብዙ ነገሮችን #አይ! #አያስፈልግም” ማለትን ይጠይቃል።

☞በሚያልፈው ምድራዊ ነገር ይልቅ በሰማያዊው ነገር ትኩረታቸው ተወስዶ ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር በማስገዛት ስጋቸውን እየጎሰሙ የተስተካከለ ኑሮ በመኖር የታመኑ አማኞች ሁሉ ይህን የማይጠፋውን የድል አክሊል ይሸለማሉ።

የጽድቅ አክሊል
☞ይህ መልካም ሥራ በመስራት የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም ለሚጣጣሩ ትዕቢተኞች የሚሰጥ ክፊያ አይደለም። በራስ ጥረት የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለመደለል መሞከር የከንቱ ከንቱ ነው። የእግዚአብሔር ጽድቅ የሰው ልጅ ሊረዳው የማይችል ዋጋ የተከፈለበት ነገር ግን በነፃ የሚሸመት እጅግ ውድና ከክፊያ ደርዝ ያለፈ በስራ ያይደለ በክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ የሆነ ነው።

የጽድቅ አክሊል የጌታ ኢየሱስን በክብር መገለጥ /መምጣት/ በናፍቆት ለሚጠባበቁ ቅዱሳን ሁሉ የሚሰጥ ነው። እነኚህ አማንያን ከጌታ ጋር ለመሆንና ፊቱን ፊትለፊት ለማየት እጅግ ጉጉት ያደረባቸው ናቸው። [2ጢሞ. 4÷7–8]
በተጨማሪም ጳውሎስ ይህ የጽድቅ አክሊል እንደተዘጋጀለት የተናገረው ሩጫውን እንደሚገባ እስከመጨረሻ በመሮጡ ነው።
✪#ሩጫውን የሚለው ቃል ጳውሎስ የራሱን ሳይሆን በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ የክርስቶስ ሐዋርያ በመሆን የሮጠውን የወንጌል አገልግሎት ሩጫ የሚያመላክት ነው።

የሕይወት አክሊል
☞ይህ የዘላለም ህይወትን የሚያመለክት አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል። የዘላለም ሕይወት አማኞች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ብቻ ያገኙት የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው እንጂ በመልካም ሥራ የሚመጣ እንዳይደለ የክርስትና እምነት አብይ/ወሳኝ ትምህርት ነው። #ደህንነት_ከእግዚአብሔር_ቍጣ_የዳንንበትና_እግዚአብሔር_ራሱ_ከራሱ_ጋር_ልያስታርቀን_ወዶና_ፈቅዶ_የራሱን_ውድ_ልጅ_በእኛ_ምትክ_በመሠዋት_የተገኘ_እንደሆነ_የማያስተምር_የትኛውም_ትምህርት_የክርስቶስን_ወንጌል_በቀጥታ_የሚፃረር_ኑፋቄ_ነው

የሕይወት አክሊል ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር የተነሳ ስለክርስቶስ ወንጌልና ስለእምነታቸው በልዩልዩ ፈተናዎች የተፈተኑና እስከሞት ድረስ የታመኑ (ሰማዕት የሆኑ/ የተሰው) ቅዱሳን ሁሉ ከጌታ ዘንድ የሚቀበሉትን ብድራት ያመለክታል [ያዕ.1÷12፤ ራዕይ 2÷10]።

የደስታ አክሊል
☞ብዙን ጊዜ “ነፍሳትን ያሸነፉ /የማረኩ/ የሚቀበሉት አክሊል”»» “Soul-winner's Crown” በመባል ይታወቃል። ይህ አክሊል ወንጌልን ላልሰሙ ሰዎች በማድረስ የተሰማሩ እና አማኞችን (በተለይም አዳዲስ አማኞችን) በሚገባ እንዲመላለሱ ወይንም የደቀመዝሙርነትን ህይወት እንዲገልጡ የሚያስተምሩ ሁሉ ከጌታ ዘንድ የሚቀበሉት ብድራት ነው። [1ተሰ. 2÷19–20]

የክብር አክሊል
☞ይህ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንጋ በመጠበቅ የታመኑ እረኞች /መሪዎች/ የሚቀበሉት ብድራት ነው [1ጴጥ. 5÷4]። ቤተክርስቲያን (ቅዱሳን) ከትምህርት መፍገምገም/ መንገዋለል /ግራመጋባት ተጠብቃ በእግዚአብሔር ቃል ተኮትኩታ እንዲታድግ /ከመንፈሳዊ ህፃንነት እንድትወጣ/ በመትጋት የታመኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች (ሽማግሌዎች) ከጌታ ዘንድ የሚሰጣቸውን ሽልማት /ዋጋ ያመለክታል።

የጌታ ጸጋና ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2