2022-07-27 07:39:06
አማኝ በምን ይሸለማል? ክፍል-10
2-የኋለኛው ትንሣኤ
✧ ከሺው ዓመት መንግሥት በኃላ የሚፈጸም ሲሆን #
ያልዳኑ_ሰዎች_ለፍርድ (ለኩነኔ) የሚነሱበት ሁለተኛው ትንሣኤ ነው።
✧ የዚህ ትንሣኤ ተካፋይ የሚሆኑ ሙታን ሁሉ በታላቁና ነጩ ዙፋን ፍርድ ፊት ይቆማሉ። ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው ከዚህ ፍርድ ፊት የሚቆም ማንኛውም ሰው ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ስላልተገኘ ሁለተኛው ሞት ይሰለጥንበታል (በእሳት ባህር ውስጥ ይጣላል)።
✧ ዳንኤል እንደተመለከተው ለእፍረት(ለውርደት) እና ለዘላለም ጕስቍልና የሚነሱበት
የኅጥኣን ትንሣኤ ነው [ት/ዳን. 12÷2]።
✧ በፊተኛውና በኋለኛው ትንሣኤ መካከል ቢያንስ የሺህ ዓመት ልዩነት አለ። “#የቀሩቱ_ሙታን ግን ይህ #
ሺህ_ዓመት_እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው።”
— ራእይ 20፥5
✧ ከፊተኛው ትንሣኤ በኋላ የሺው ዓመት (የመሲሁ) መንግሥት በምድር ላይ የሚሆን ሲሆን ከኋለኛው ትንሣኤ በኋላ ግን ምድርና ሰማይ ከፊቱ ይሸሻሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በታላቅ ትኩሳት ይቀልጣል። [2ጴጥ. 3÷12፤ ራዕይ 20÷11]
Дየፍርድ ወንበር ፍርድ አሰጣጥ //––••–––••–––••–––••––//
✧ያልዳኑ ሰዎች ሁሉ (የኋለኛው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑቱ) የዚህ ፍርድ ተካፋይ አይሆኑም።
✧ፍርዱ የአማኞችን ንጥቀት ተከትሎ (ጌታ "#በጻድቃን_ትንሣኤ" ብሎ እንደተናገረው»» ሉቃስ 14÷14) በአየር ላይ ከበጉ ሠርግ ፊት ይፈጸማል።
✧“
ክርስቲያኖች በእምነት አማካኝነት በክርስቶስ ያገኙትን ዘላለማዊ ጽድቅ የሚመለከት ሳይሆን፤ በዚህ ምድር ሲኖሩ ለሠሩት ሥራ የሚቀበሉት ፍርድ ነው።” (የአድሱ መደበኛ ትርጉም ማጥኛ)
የፍርድ አፈፃፀሙን በአግባቡ ለመገንዘብ 1ቆሮ. 3÷11–15 እጅጉን ይረዳናል። ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አራት ነጥቦችን እንደሚከተለው እንመልከት....
፩ ብቸኛው መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው [ቁ.11]☞የቤተክርስትያን የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ክርስቶስ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምሩናል። እርሱ #
የተፈተነ_የመሠረት_ድንጋይ ስለሆነ (ት/ኢሳ. 28÷16) ያለጥርጥር ጽኑና አስተማማኝ ነው። መጽሐፍ
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም” እንደሚል በእርሱ ላይ ያለ ከመሠረቱ (ከክርስቶስ) የተነሳ ሕይወት አለው።
፪ ያ ቀን [ቁ.13]☞ይህ «ያ ቀን» የተባለው ቀን ፍርዱ የሚፈጸምበት፤ ይሄውም አማኞች በክርስቶስ ፍርድ ወንበር (Bema seat) ፊት የሚቀርቡበት ነው። በዚህን ቀን የፍርድ ተቀባዩ መዳን አለመዳን ሳይሆን
ሥራው ይፈተናል። አማኙ በምድር በኖረበት ዘመን የኖረው ኑሮ ሁሉ ይገለጣል (ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል)።
#እሳቱ_የእያንዳንዱን_ሥራ_ጥራት_የሚፈትን_እንጂ_ፍርድ_ተቀባዩን_የሚፈጅ_አይደለም ¶ከዚህ ቀጥለን የምንመለከታቸው ቀሪዎቹ ሁለት ነጥቦች ከፍርዱ ውጤት ጋር የተያያዙ ናቸው። ቁ.12 ላይ “ማንም ግን በዚህ መሠረት (በክርስቶስ) ላይ...” በማለት የፍርዱ ምክንያት አማኞች በተመሠረተው መሠረት »»በክርስቶስ ላይ ያነጹት (የገነቡት) ኑሮ እንደሆነ በግልፅ ያስቀምጣል።
፫ ሥራው ተፈትኖ ያለፈለት ይሸለማል [ቁ.12&14]☞ወርቅ፣ ብርና የከበረ ድንጋይ➜ በእሳት ተፈትኖ የሚያልፈውን (የሚጸናውን) ሥራ የሚያመላክቱ ሲሆኑ በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ የጤናማ ክርስትና ህይወት ምሳሌዎች ናቸው።
የእግዚአብሔር ጸጋ ረድቶአቸው.... ክቡር በሆነው እግዚአብሔርን በመምሰል ህይወት የኖሩ፣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ፈቃድ በማስገዛት በክርስቶስ ደም የተዋጁበትን የሚመጥን ኑሮ ለመኖር የጣሩ፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመኖር የተጉ አማኞች ከጌታ ዘንድ ምስጋና ይቀበላሉ [1ጴጥ. 1÷6–7፤ 1ቆሮ. 4÷5]።
፬ ሥራው የተቃጠለበት ይጎዳበታል (ሽልማት ይቀርበታል) [ቁ.12&15]
☞እንጨት፣ ሳር እና አገዳ➜ በእሳት ተፈትኖ ማለፍ የማይችለውን (የሚቃጠለውን) እንደ ሰው ጥበብና መንደራዊ ከንቱ ኑሮ የመኖር የደካማ ህይወት መግለጫዎች ናቸው።
1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።
▼▼(አዲሱ መ.ት)
¹⁵ ሥራው የተቃጠለበት ግን #ሽልማት_ይቀርበታል፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ ይሁን እንጂ #የሚድነው_በእሳት_ውስጥ_በጭንቅ_እንደሚያልፍ_ሆኖ_ነው።
☞መጽሐፍ ቅዱሳችን አማኝ በምድር በኖረበት ደካማ ኑሮ ምክንያት ድነቱን ያጣል ብሎ አያስተምረንም #ምክንያቱም_ድነት_ወይም_የዘላለም_ሕይወት_በክርስቶስ_በኩል_የሆነ_ገና_ደካሞች_ሳለን_የተሰጠን_የእግዚአብሔር_ነፃ_ስጦታ_እንጂ_በሥራችን_ላይ_የተመሠረተ_አይደለም!!
ይቀጥላል........
ጸጋና ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን!
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
3.4K viewsYOKABID 4ME, edited 04:39