Get Mystery Box with random crypto!

አማኝ በምን ይሸለማል? ክፍል-6 ¶ቅዱሱ መጽሐፋችን ከአዳም አንስቶ የሰዉ ል | Maranatha Digital Network

አማኝ በምን ይሸለማል?
ክፍል-6

¶ቅዱሱ መጽሐፋችን ከአዳም አንስቶ የሰዉ ልጆች ሁሉ ፍርድን እንደሚቀበሉ ቢያስተምረንም ሁሉም ግን በተመሳሳይ ጊዜ አንድ አይነት ፍርድ እንደሚቀበሉ አይነግረንም፡፡ እግዚአብሔር አብ በሙታንና በሕያዋን ላይ እንዲፈርድ ለወልድ ሰጥቶታል፤ ቀን ቀጥሮም ወስኗል (ዮሐ. 5፡22)፡፡ የጌታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ከሚያረጋግጥልን ብዙ ነገሮች አንዱ:- ማንም ያለ ፍርድ/ ፍርድ ሳይቀበል/ እንደማይቀር ነው (ሐዋ. 17፡30-31)፡፡ ሐዋርያዉ ጴጥሮስ፡- ኢየሱስ አደራ ብሎ ካዘዛቸዉ ጉዳዮች መካከል የፍርድ ነገር መካተቱን መናገሩ… (ሐዋ. 10፡32) እኛም ረጋ ብለን ልናጤነዉ የሚገባ ለመሆኑ ጥርጥር የለዉም፡፡

¶በብዙ አማኞች ዘንድ ስለ ጌታ መምጣት ያለዉ ምልከታ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ሊፈትሽ እና ሊታረም የተገባ መሆኑን ከራሴዉ እርምት ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ፡፡ የጌታ መምጣት የምንደሰትበት ሳይሆን የምንሰጋበት እንደዉም ያለንበትን የመንፈሳዊ ህይወት ድካም ተመልክተን #አሁን_ባይመጣ የምንልበት ደረጃ የደረስን ጥቂቶች አይደለንም፡፡ #ልብ_ሊባል_የተገባ_እዉነታ_ግን_የጌታን_መምጣት_እየሰጉ_መኖር_የተስተካከለ_ህይወት_እንዲኖረን_የሚያበረክተዉ_አንዳች_ነገር_አለመኖሩ_ነዉ፡፡ ይልቅ የጌታን መገለጥ /መምጣት/ በጉጉት መጠባበቅ እጅግ መልካም እንደሆነና የጠራን ታማኙ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻ ድረስ ራሱ እያጸናን መልካም ኑሮ እንድንኖር እንደሚያስችለን የቃለ-እግዚአብሔር ትምህርት ነው።

¶ከመጽሐፍ ቅዱሳችን አስተምሮ እጅግ በተጻራኒ መጽናኛ ቃል እና ትልቁ ተስፋችን የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ጉዳይ አሁን ላይ አማኙ እንድሰጋ ከዳረጉት ነገሮች አንዱ #የፍርድ_ፍርሃት እንደሆነ ግልፅ ነው። “#በፍርድ_ፊት_ቆሜ_ስራዬ_ለመዳን_የማያበቃ_ሆኖ_ከዘላለም_ህይወት_እጎድል_ይሆን?” እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ስለጌታ መምጣት ባለን ምልከታ ብዥታ የሚፈጥሩ መሆናቸው አጠያያቂ አይደለም። ስለሆነም በቅዱሱ መጽሐፍ ሰፍረው ከሚናገኛቸው የፍርድ አይነቶች ሁለቱን ቀንጨብ አድርገን ለተወሰኑ ክፍሎች እንደሚከተለው እንመልከት....

የታላቁና ነጩ ዙፋን ፍርድ[ራዕይ. 20፥11-15]

¶በግሪኩ "Thronos" በመባል የሚታወቅ ሲሆን በታላቅና ነጭ ዙፋን ላይ በተቀመጠው እግዚአብሔር ወልድ ፊት ሙታን/ ያለክርስቶስ የሆኑ ሰዎች/ ብቻ የሚቆሙበት ነው።
¶ዓለም በኃጢአት ምክንያት የሚትኰነንበት በመሆኑ ያልዳኑ ሰዎች ብቻ በፍርዱ ፊት ይቆማሉ።
¶ፍርዱ የሚከናወነው #የኋለኛው_ትንሣኤ ተካፋይ በሆኑ ሰዎች ሁሉ ላይ ሲሆን መፈጸሚያ ጊዜውም ከሺው አመት መንግሥት በኃላ ነው።
¶በዚህ ፍርድ ፊት የቆመ ማንኛውም ሰው ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያልተገኘ በመሆኑ ወደ ዘላለም ጥፋት /የእሳት ባህር/ ሁለተኛው ሞት ይጣላል እንጂ የመዳን ተስፋ የለውም።

ቅዱሳን ወደዚይኛው ፍርድ እንደማይመጡ የትኛውም ሰው ከተናገረው በላይ ፍርድን ሁሉ ሊፈርድ ከአብ የተቀበለውና ሁሉ የሚመለከተው ወልድ «እውነቱን ልንገራችሁ! ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ህይወት ተሻግሯልና በኃጢአቱ ምክንያት ለፍርድ አይቀርብም።» [ዮሐ.5÷24 ሕያውቃል ትርጉም] ብሎ ተናግሯል።
¶የአድስ ኪዳን ማዕከላዊ ጥቂስ በሆነው ዮሐ.3÷16 የሰፈረውን እውነታ በ18ኛው ቁጥር ሲያብራራ “#በእርሱ_በሚያምን_አይፈረድበትም” ይላል።
ይቀጥላል..........
የጌታ ጸጋ ይብዛልን!!
|.Maranatha Digital Network.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2