Get Mystery Box with random crypto!

አማኝ በምን ይሸለማል? ክፍል-7 ¶በ6ኛው ክፍል ስለፍርዶች መመል | Maranatha Digital Network

አማኝ በምን ይሸለማል?
ክፍል-7

¶በ6ኛው ክፍል ስለፍርዶች መመልከት መጀመራችን የሚረሳ አይደለም። ዛሬም ቀጥለን #ስለእግዚአብሔር_ቁጣ እንማማራለን መልካም ንባብ ተመኘው....

¶መጽሐፍ ቅዱሳችን ስለእግዚአብሔር ቁጣ ግልፅና የተብራራ ትምህርት አለው። በብሉይም ሆነ በአዲሱ ኪዳን ቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ተጽፎ ስለሚናገኝ ለማናችንም አዲስ ቋንቋ እንደማይሆን እሙን ነው። ሁላችሁም ምንነቱን ቢትጠየቁ ጥሩ ምላሽ እንደሚትሰጡ አልጠራጠርም። እንደእኔ ምልከታ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚከተለው ይብራራል....
የእግዚአብሔር_ቍጣ:– በረባ ባልረባ ፊትን እንደማኮፈስ ያለ መሠረት የለሽ እንደሰው ቁጣ ሳይሆን ከቅድስና ባህሪው ጋር የሚጻረረውን #ኃጢአትን የሚበቀልበት ትክክለኛ የሆነ ለኃጢአት ያለው ጥልቅ ጥላቻ ነው።
፨ይሄ ፍቅር ከሆነው ማንነቱ ጋር የሚጣረስ ባህሪው ሳይሆን ከአመፅ ጋር ምንም አይነት ትብብር እንደሌለው የሚያሳይ የቅድስና ባህሪው ነው። #ቅዱስ_የሆነው_እግዚአብሔር_በቅዱስ_አደራረጉ_በኃጢአት_ላይ_ይቆጣል።

የእግዚአብሔር ቊጣ እነማንን ይሆን የሚመለከተው? መጽሐፍ ምን ይላል
¶መጽሐፍ ቅዱሳችንን ረጋ ብለን ስናጠና #የእግዚአብሔር_ቊጣ ወደፊት ሊገለጥ ያለና አለም ከዚህ ቀደም ፈጽማ አይታው የማታውቀው ከምናስበው በላይ እጅግ አስጨናቂ እና አስፈሪ እንደሆነ እንረዳለን። ይህ በፍርድ የሚገለጠው የእግዚአብሔር ቊጣ:- #ታላቁንና_ነጩን_ዙፋን_ፍርድ በሚያመለክት መልኩ»»» “ታላቁ የቊጣ ቀን” በመባል ተሰይሟል። በእርግጥ የሰባቱ ዓመት መከራም ቊጣው የሚገለጥበት መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው።

ቆላስይስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በእነዚህም ጠንቅ #የእግዚአብሔር_ቍጣ_በማይታዘዙ_ልጆች_ላይ_ይመጣል፤
⁷ እናንተም ደግሞ ትኖሩባቸው በነበራችሁ ጊዜ፥ በፊት በእነዚህ ተመላለሳችሁ።

የማይታዘዙ ልጆች” እነማን ይሆኑ
¶በእምነት የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ነገር ግን ለመታዘዝ የደከሙ (ክፍተት የታየባቸው) አማኞች ይሆኑን? #አይደለም
¶ከላይ በጥቅሱ ግልፅ ሆኖ እንደምናነበው:- የእግዚአብሔር ቍጣ የሚመጣው #በማይታዘዙት_ልጆች ላይ እንደሆነ ከገለጸ በኃላ በ7ኛው ቁጥር “#እናንተም_ደግሞ” በማለት አማኞችን»» የማይታዘዙ ብሎ ከመደባቸው ጎራ ለይቶ ያስቀምጣል።

¶በኤፌ.2፥1–3:– በክርስቶስ ሆነው ሕያዋን ከመሆናቸው በፊት አማኞች ስለነበራቸው የቀድሞ ማንነት በግልፅ ያብራራል። በዚሁ ክፍል መሠረት “#የማይታዘዙ_ልጆች” የአየር አለቃ መንፈስ ለሆነው /ለሰይጣን/ ፈቃድ ተገዝተው የሚኖሩ #የቁጣ_ልጆች እንጂ #የእግዚአብሔር_ልጆች_አይደሉም
•|ከዚህ በተጨማሪ በ2ተሰ.2÷8–10 እነዚህ የማይታዘዙ የተባሉቱ የማይታዘዙት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንደሆነና የእግዚአብሔር በቀል የዘላለም ጥፋት እንደሚያስከትልባቸው በዝርዝር ተቀምጦ እናገኛለን።
እኛም ሁላችን እንደዚያው (የቍጣ ልጆች ማለትም ለቍጣ የተጠበቅን) ነበርን። ስለት በስቶ ያቆሰለው፣ የፀሐይ ትኩሳት ያደከመው፣ የግርፋት ብዛት መልከ-ጥፉ ያደረገው፣ ከሰዎች ንቀትን የጠገበ... ያ.. የጽድቅ ልብሳችን ሊሆን ያለልብስ ዕርቃኑን የተሰቀለልን»» በጠላቶቹ ፍቅር ተነድፎ በእንጨት ላይ የተሰፋልን.. በመስቀል የዋለልን ፍቅር #ከጉድ_አወጣን። ክብር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን

¶በአጠቃላይ የዘላለም ጥፋትን የሚያስከትለው የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ማለትም ለወንጌል እውነት በእምነት በማይታዘዙት ላይ ሊገለጥ ያለ ነው። #የማይታዘዙ የሚለው ቃል በግሪኩ ἀπείθεια [apeítheia] ሲሆን፤ ትርጓሜውም »» የማያምኑ/ አማኞች ያልሆኑ ማለት ነው።

ኤፌሶን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ከዚህ የተነሣ #በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።
⁷ እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤
⁸ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ #አሁን_ግን_በጌታ_ብርሃን_ናችሁ፤


ከዚህ ቀጥለን በቀጣዩ ክፍል አማኞችን የእግዚአብሔር ቍጣ አይመለከትም ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ምክንያቱስ ምን እንደሆነና ዋስትናው/ ማረጋገጫው ምን እንደሆነ እንመለከታለን።
ጸጋ ይብዛልን አሜን
ይቀጥላል.....
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2