Get Mystery Box with random crypto!

አማኝ በምን ይሸለማል? ክፍል -9 ¶ከዚህ ቀደም በነበሩ ክፍሎች በአዲ | Maranatha Digital Network

አማኝ በምን ይሸለማል?
ክፍል -9
¶ከዚህ ቀደም በነበሩ ክፍሎች በአዲስ ኪዳን ከሚገኙ ፍርዶች መካከል አንዱንና የመጨረሻ የሆነውን (ከምድር እና ሰማይ መጨረሻ በኃላ የሚፈፀመውን) ስንመለከት ቆይተናል። በእነዚያ ክፍሎች የታላቁና ነጩ ዙፋን ፍርድ የእግዚአብሔር ቍጣ በሀይል የሚገለጥበት መሆኑን እና አማኞችን እንደማይመለከት ለመመልከት ሞክረናል። በዛሬው እና በቀጣዮቹ ክፍሎች ደግሞ አማኞችን ከሚመለከታቸው ፍርዶች አንዱ የሆነውን ቀጥለን እንመለከታለን.. መልካም ንባብ ተመኘው...

የክርስቶስ የፍርድ ወንበር [2ቆሮ.5÷9-10፤ ሮሜ 14÷10]

¶በግሪኩ “βῆμα”»» “Bema” በመባል የሚታወቅ ሲሆን አማኞች በዚህ ምድር ሲኖሩ “ምን?፤ ለምን?” እንደሰሩ ሥራቸው የሚፈተንበት ከዚያም እንደየስራቸው መጠን ብድራትን የሚቀበሉበት ነው።
¶ከዚህ ቀደም አጽንዖት እንደሰጠነው በአማኝ የሚገለጠው መልካም ሥራ ከአማኙ ጉብዝና፣ ልዩ አቅም እና ችሎታ የመነጨ ሳይሆን #እግዚአብሔር_ራሱ መልካም የመስራትን ፍላጎት ሆነ የማድረግን ብቃት በአማኙ ውስጥ እንደሚሰራ [ፊል. 2÷13] እንዲሁም እስከ ጌታ መምጫ ድረስ እንደሚያስቀጥለን [ፊል. 1÷6] ጸጋው እንደሚረዳን መዘንጋት አይገባም።
¶ይህ ፍርድ ያልዳኑትን (የኋለኛው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑትን) እንደማይመለከትና እና የፍርዱ ተቀባዮች መዳን አለመዳናቸውን የሚያረጋግጡበት አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል። [ክፍል 3 እና 4ን መለስ ብለው ይመልከቱ]።
¶የፍርዱ ውጤትም መሸለም አልያም አለመሸለም ነው። #ከሽልማት_ጋር_እንጂ_ነፃ_ስጦታ_ከሆነው_ከዘላለም_ሕይወት_ጋር_የሚገናኝ_አይደለም!! (በቀጣዩ ክፍል በሰፊው እንመለከታለን)
¶የፍርዱ መፈጸሚያ ጊዜ ከንጥቀት በኋላ ከበጉ ሰርግ በፊት በአየር ላይ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም #የጻድቃንን_ትንሣኤ ተከትሎ እንደሆነ ተናግሯል [ሉቃ. 14÷14]

ስለትንሣኤ ያውቃሉ
ስለትንሣኤ ወደፊት በደንብ የተብራራ ትምህርት ይዘን እንደምንቀርብ እያሳወኩ ቁንጽል የሆነውን እንደሚከተለው አሰናድቼላችኋለሁ።
✓ከአዳም አንስቶ እስከመጨረሻው ትውልድ ድረስ የሰው ልጅ በሙሉ እንደሚነሳ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል። #ፈርሶ_የሚቀር_ሥጋ_ጠፍቶ_የሚቀር_ሰው_የለም። ዳሩ ግን የሁሉም ትንሣኤ በደፈናው በአንድ ላይ /አንድ ጊዜ/ የሚፈጸም ሳይሆን በራሱ ተራ እንደሆነ ቅዱሳት መጽሕፍት ያረጋግጡልናል [1ቆሮ. 15÷23]።
¶የትንሣኤ ትምህርት የክርስትና መሰረታዊ ትምህርት እንደሆነና እውንተኝነቱ ማረጋገጫ የክርስቶስ ትንሣኤ መሆኑን የእውነት ቃል በግልጥ ያስተምራል ።

ዳንኤል በዘመኑ ድንቅ ነገር በራዕይ ተመልክቶ ነበር [ት/ዳን 12÷2]። የሙታን ትንሣኤ እንዳለና “...እኵሌቶቹ ወደ #ዘላለም_ሕይወት እኵሌቶቹም ወደ #እፍረትና ወደ #ዘላለም_ጕስቍልና።” እንደሚነሱ አይቷል። ጌታም #ለሕይወት_ትንሣኤ እና #ለፍርድ_ትንሣኤ ከመቃብር የሚወጡ እንዳሉ ተናግሯል [ዮሐ.5÷28]። ከላይ የቀረቡትን ጥቅሶች በጥንቃቄ ካስተዋልን ሁለት አይነት ትንሣኤዎች እንዳሉ መረዳት አዳጋች አይሆንብንም።

1-የፊተኛው ትንሣኤ
ራእይ 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ √በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው #ብፁዕና_ቅዱስ ነው፤
√ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ #ሥልጣን_የለውም፥
√ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን #ሺህ_ዓመት_ይነግሣሉ።
¶ለክርስቶስ የሆኑት በክብር የሚነሱበት ነው።
¶የቅዱሳን ወይም የጻድቃን ትንሣኤ በመባል ይታወቃል።
¶የዳኑ ሰዎች ለሕይወት የሚነሱበት ነው (ለሕይወት ትንሣኤ)።

በውስጡ ሦስት ተራቸውን የጠበቁ ትንሣኤዎች ያካትታል።
. ከፊል ትንሣኤ
¶ጌታ ከተነሳ በኋላ ከብሉይ ኪዳን ብዙዎች ቅዱሳን ተነስተው (ከመቃብሮቻቸው ወጥተው) ነበር። [ማቴ. 27÷52-53]

. የቤተክርስቲያን ንጥቀት
¶በክርስቶስ ሆነው ያንቀላፉት መቃብሮቻቸው ተከፍቶ በመውጣት፤ በሕይወት የምንቀር ደግሞ በቅፅበተ-አይን በመለወጥ የማይበሰብሰውን ሰማያዊውን አካል እንካፈላለን። [ፊል. 3÷20፤ 1ተሰ 4÷13-18]

ሐ.በሰባቱ ዓመት መከራ የሚገደሉ
¶ከቤተክርስቲያን ንጥቀት በኃላ ለ7 ዓመት በምድር ላይ መከራ (በአየር ላይ የበጉ ሠርግ) እንደምሆን የታወቀ ነው። በዚህን ጊዜ የሚሰበከውን የመንግሥቱን ወንጌል በመቀበላቸውና ለአውሬው ምስል ባለመስገዳቸው የሚገደሉት ከሺው አመት መንግሥት በፊት ይነሳሉ። [ራዕ. 20÷4፤ 6÷9....]
ይቀጥላል.....
ጸጋና ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን!
|.MARANATHA DIGITAL NETWORK.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2