Get Mystery Box with random crypto!

Maranatha Digital Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ maranatha_fellowship — Maranatha Digital Network M
የቴሌግራም ቻናል አርማ maranatha_fellowship — Maranatha Digital Network
የሰርጥ አድራሻ: @maranatha_fellowship
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.19K
የሰርጥ መግለጫ

#Maranatha_digital_Network #youth center #spreading the gospel of the lord Jesus Christ #christian living #Christian fellowship
Follow us on:-
instagram : maranatha_fellowship
facebook: maranathafellowshipEthiopia
Telegram group @Maranatha_Fellowship2

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-01 18:27:27 “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም::”
-ሮሜ 8:1

¶መኮነን ማለት በፍርድ ወይም በቅጣት ስር መውደቅ ማለት ሲሆን ከኩነኔ ነጻ መሆን ማለት ደግሞ ከቅጣት/ፍዳ ነጻ መሆን ማለት ነው። ኩነኔ የሌለበት ሰው ለፍርድ የሚያበቃ ጥፋት ያልተገኘበት እና ከተከሰሰበት ወንጀልም ነጻ ሆኖ የተገኘ ማለት ነው። #ኮናኙ_(ፈራጁ)_እግዚአብሔር #ተኮናኙ_(የሚፈረድበት) ደግሞ #የሰው_ልጅ_በሆነበት በዚህ ትዕይንት ውስጥ ጻድቅ በሆነው አምላክ ፊት ማን ሊጸድቅ ይችላል የሚለው ጥያቄ የሁላችንም ሊሆን ይገባል። ለዚህ ጥያቄ የራሴን መላ ምት ወደጎን ላድርግና መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚሰጠውን ምላሽ አብረን እናንብ፦

ኢዮብ 25፡4 “ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?”
ኢዮብ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥ ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት ሊነጻ ይችላልን?
¹⁸ እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤ #መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤
መክ. 7፡20 “በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና።”
ሮሜ 3:23 “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”

ኢዮብ፣ ጠቢቡ ሰለሞን እና ቅዱስ ጳውሎስ የጻፉትን ካነበብን በኋላ፣ ቅዱሳን የሆኑ መልዕክት እንኳን ጉድለታቸውን በሚመለከቱበት በእግዚአብሔር ቅድስና ፊት በራሴ ጻድቅ ሆኜ በመገኘት ከኩነኔ ልድን እችላልሁ ብሎ ማሰብ የማይቻል ብቻ ሳይሆን ድፍረትም ይመስለኛል። የእናነተን ምላሽ ለራሳችሁ ልተውና በብዙ መንገድ በእግዚአብሔር ላይ ያመጽኩትን እኔን ግን “ነጻ” የሚለው ቃል እንደማይመለከተኝ አስረግጬ መናገር እችላለሁ። በእግዚአብሔር መመዘኛዎች ሁሉ የኩነኔ ፍርድ የሚገባኝ ኃጢአተኛ/በደለኛ እንደሆንኩ ያለጥርጥር አውቃለሁ። ለእኔ የሚገባው ትክክለኛው ፍርድ “ወንጀለኛ!” የሚለው ብቻ ነው። ኩነኔ ለማንነቴ የሚመጥን ትክክለኛ የፍርድ አለንጋ ነው። ከጻድቅ ፈራጁ እግዚአብሔር አፍ የወጣውና የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጢአት ምክንያት የሚኰንነው ይህ ፍርድ እኔን ብቻ ሳይሆን የአዳምን ዘር ሁሉ እንደሚመለከትም ጥርጥር የለኝም። ከዚህ ኩነኔ በራሱ የሚያመልጥ ጻድቅ/ንጹህ ሰው በምድር የለምና።

ጻድቅ በሆነው አምላክ ፊት ያለ ኃጢአት ጻድቅ ሆኖ በድፍረት ሊቀርብ የሚችል አንድ ሰው ብቻ አለ። ይህ ሰው ኃጢአት አላደረገም (ዕብ. 4:15)። የእግዚአብሔርን መመዘኛዎች (ሮሜ 10:4) ሁሉ ሊያልፍ የቻለ ንጹሕ ሰው ነው (ዮሐ. 17:4)። ማንም ስለ ኃጢአት ሊወቅሰው አይችልም (ዮሐ. 8:46)። ይህ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። ኢየሱስ በአብ ፊት ጻድቅ ሆኖ መታየቱ ብቻ አይደለም የታሪኩ ሙሉ ሃሳብ። በእርሱ ሆነው ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን (የሚመጡትን) ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ (ኩነኔ) ነጻ ማድረጉ እንጂ (ሮሜ 8:1)። እርሱ ጻድቅና ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እነርሱም ጻድቃንና ቅዱሳን ተብለው መቆጠራቸውም እንጂ (1ቆሮ. 6:11፣ ሮሜ. 4:11)።

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ሥራ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገሩት ቅዱሳን ዓለም በኃጢአት ምክንያት ከሚያገኛት #ኩነኔ ወይንም #ከነጩ_ዙፋን_ፍርድ አምልጠዋል።

ይህ ነው እንግዲህ፣ “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” ማለት። እዚህ ላይ፣ ኩነኔ የሌለባቸው በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉቱ ብቻ እነደሆኑ አንባቢ ያስተውል!!! በክርስቶስ ኢየሱስ የሌሉ ሁሉ በኩነኔ ውስጥ ይኖራሉ።

“በእርሱ (በኢየሱስ) በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ዮሐ. 3:18

በአዳነው ዲሮ ዳባ

#ከEthiopiansite_ወንጌል_በድህረ_ገጽ_አገልግሎት_መጠነኛ_ማሻሻያ_ተደርጎ_የተወሰደ

|.Maranatha Digital Network.|
@Maranatha_Fellowship
@Maranatha_Fellowship2
2.5K viewsBĚ ĤØPÊ, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ