Get Mystery Box with random crypto!

ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewaleshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል?

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-12-15 16:41:35 #ደስ_የሚል_ቀን_ስትፈልጊ

ደሞ ነጋ ከማለት ተመስገን ነጋልኝ ማለትሽ በራሱ ቀንሽን ያማረ መልካም ውብ ያደርገዋል እእእ ታድያ ምን እየጠበቅሽ ነው እህቴ ተመስገን ነጋልኝ በይ እንጂ ' አንተም ቢሆን ተመስገን ነጋልኝ በል እንጂ ህህ!!

የበረከት የምስጋና ደስ የሚል ቀን ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu።
1.3K viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 11:00:16 መንገድህን እመነው!

ጉዞ መጀመር ስታስብ ብዙ አያሌ መሰናክሎች ታይተውሃል ፤ ከመዳረሻው ይልቅ እንቅፋቶቹ ጎልተውብሃል ፤ ከጉዞው ጠዓም ይልቅ ፍራቻው ስሜትህን ረብሾታል ፤ ስጋቱ ተገዳድሮሃል ፤ የተለመዱ የሚመስሉ መጀመር ስታስብ የሚከሰቱ ፣ አለመጀመርንና በነበሩበት የመቆየትን ምርጫ ሊያጎሉ የሚጥሩ ጫናዎች ነበሩበህ ። ነገር ግን እነዚህን ሁሉ አልፈህ መንገድህን ጀምረሃል ፤ ጉዞ ላይ ነህ ። ከመቆም መሔድን ፤ ከስንፍና ብርታትን ፤ ከመተው ማድረግን ፤ ከመተኛት መሮጥን መርጠሃል ።

ምርጫህ ትክክል እንደሆነ አትጠራጠር ፤ በእርግጥም እንደሚያስከብርህ እመን ። የቆሙ ፣ ባሉበት የሰነበቱ የት እንዳሉ ፣ ምን አይነት ህይወት እንደሚኖሩ አይተሃል ። የዘመናት ለውጥ እንጂ የነርሱ ለውጥ አልታየህም ። ጉዞ የጀመሩ ፣ የተሻለውን የፈለጉትም ምን ላይ እንዳሉ ታውቃለህ ፤ ምንም በፍጥነት ባይሆንም ካሰቡት ደርሰዋል ፤ ያሰቡትን አሳክተዋል ።

አዎ! ጎዳናዎች በበዙበት የሚስማማህን መምረጥ መቻል ፤ በምርጫው መፅናትና በእርሱም መጓዝ ትልቁ ጥንካሬህ እንደሆ አስብ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ዝም ብለህ መንገድህን እመነው! ከጀመርክ ወዲያ ጥረትህ ይሔን ያክል ነው ። መንገድህ እራሱ ይወስድሃል ። የጅማሬ ጊዜያት ከባድ ይሆናሉ ፣ ቀደሚዎቹ ቀናት ፈተና ይበዛባቸዋል ፤ ጫናቸው ያይላል ፤ ስጋት ይደቀንባቸዋል ፤ ትኩረትህ ይበታተናል ፤ ግራ ልትጋባም ትችላለህ ። ከጀመሩ ቦሃላ ግን ትለቁ ፈተናህ መንገድህን ማመንና በእርሱ መፅናት ፣ በእርሱም መጓዝ ይሆናል ። ሃሳብን ሰብሰቦ ፣ ትኩረትን አስተካክሎ ፣ ጥሞና ሰቶ ፣ ምርጫን አክብሮ በጀመሩት መንገድ መጓዝ እራስን ለሂደቱ አሳልፎ እስከመስጠት የሚያደርስ መሱዓትነት ቢፈልግም ከቶ ወደኋላ አትመለስ ፤ የሚጠበቅብህን ሁሉ አድርግ ፤ ፊት ለፊትህን ተመልከት ፣ ጅማሬህ ቢፈተንም ፍፃሜህ በእርግጥም እንደሚያምር አትጠራጠር ፤ በመንገድህ ተማመን ።

join us...
@manyazewaleshetu
1.4K viewsedited  08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 12:12:50
6ትናንሽ ታሪኮች

፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

1 በአንድ ወቅት በአንድር መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዙ ተገኘ፡፡

(ይ
እምነት ይባላል፡፡)

፣፣፣፣፣፣፣፣፣

2 ህጻን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካች እንጂ አታለቅስም ፡፡ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!!

ይህም እርግጠኝንት ይባላል፡፡

፣፣
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

3 በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በህይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም(የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!!

ይህም ተስፋ ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣፣፣

4 ወደ ፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን)እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!!

ይህ ደሞ በራስ *,መተማማን
ይባላል፡፡**

፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

5 ዓለም ላይ የሚወርደውን መከራና ስቃይ እናያለን ይሁን እንጂ አሁንም እንጋባለን

ይህም ፍቅር ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣

6
አንድ ሽማግሌ በለመበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት ጉሩም ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች

“እኔ የስድሳ ኣመት ሽማግሌ አይደለሁም ፣የአርባ አራት
መታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአስራ ስድሰት ኣመት ወጣት እንጂ”

ይህ ለራሳቸእን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡

፣፣፣፣


መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!!


እምንት ፣እርግጠኝነት ፣ተስፋ ፣በራስ መተማማን ፣ ፍቅርና ለራሳችሁ ጥሩ አመለካካት ሳይለያችሁ ኑሩ !!!
@manyazewaleshetu
1.5K viewsedited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 12:09:17 #ሕይወታችሁን_ለመለወጥ_ከፈለጋችሁ...

ሕይወታችሁን ለመለወጥ ከፈለጋችሁ ምርጫችሁን ለውጡ፡፡ ምርጫ ሳይለወጥ ሕይወት አይለወጥም፡፡

• የምትውሉበት አካባቢ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

• የምታዩትን ማሕበራዊ ሚዲያ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

• የምትይዙትን የቅርብ ጓደኛ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

• የምታነቡትን መጽሐፍ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

• በየቀኑ በመደጋገም የምታደርጓቸውን ልማዶች ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

ራሳችሁ የማይሆን ምርጫ እየመረጣችሁ የማይሆን ሕይወት ውስጥ ስትገቡ ብትነጫነጩ ምንም አታመጡም፡፡

ምርጫችሁን አስተካክሉ! ትክክለኛን ነገር ምረጡ!

@manyazewaleshetu
1.4K viewsedited  09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 21:58:24 ሁሉንም መቀየር!

ትላንት ላይመለስ አልፏል ራስህን መውቀስ አቁም! አሁንን መኖር ጀምር፤ ዛሬ ቆራጥ ከሆንክ ሁሉንም መቀየር፣ ሁሉንም እንደ አዲስ መጀመር፣ ያበላሸኸውን ማስተካከል ትችላለህ። ወዳጄ እድልህን ተጠቀምበት ይሄንን ቀን ያላዩ ብዙዎች አሉ።

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
470 viewsedited  18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 20:08:41 #ማዕበሉ_ካልተረጋጋ_አንተ_ተረጋጋ

በሕይወትህ የሚከሰቱት ማዕበሎች (ችግሮች) መፍትሄ የሚያገኙበት መንገድ ከሁለት አንዱ ነው፡- 1) ማዕበሉ (ችግሩ) ይረጋጋል፣ ወይም 2) የችግሩ ማዕበል እያለ አንተ ትረጋጋለህ፡፡

በሕብረተሰቡ መካከል እንደአሸናፊነት የሚታየው ሁኔታ ከችግር ነጻ የሆነና ሁሉን ቸግር ገርስሶ የማለፍ ሁኔታ ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ አመለካከት በስሜታችን ላይ ይህ ነው የማይባል አጉል ተጽእኖ አሳድሮብናል፡፡ ስለሆነም፣ ያጋጠመን ችግር እስከሚወገድ ድረስ ልክ “እንደሌሎቹ” ሙሉ ሕይወት መኖር የምንችል አይመስለንም፡፡

እውነታው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ከቻልክና ከተቃናልህ የችግር ማዕበሉን አረጋጋውና አስወግደው፣ ካልቻልክና ካልቀናልህ ግን እንተው ተረጋጋና አርፈህ ኑሮህን ኑር፣ መንገድህንም ቀጥል፡፡

ይህ ከላይ የጠቀስኩት አመለካከት ሁለት እውነታዎችን ከመቀበል የሚመነጭ ነው፣
1) ሁል ጊዜ ከሕይወታችን ችግር አይቀሬ ነው፣
2) ሁሉም ችግር ደግሞ በቀላሉ አይወገድም፡፡

ስለዚህም መወገድ የሚችለውን ችግር በማስወገድ፣ የማይወገደውን ችግር ደግሞ ችግሩ የሚያስከትለውን መጨናነቅ ከእኛ በማስወገድ ነው የምናሸንፈው፡፡

ችግር ካልተወገደ በስተቀር የተሳካ ሕይወት እንደሌለህ ስታስብ፣ ዘወትር የማይለወጥ ነገርን ስትታገል ትኖራህ፣ ሁል ጊዜ “ለምን?” በሚል ጥያቄ ውስጥ ትኖራህ፣ ተስፋ ቢስነት ይጫጫንሃል፣ እንዲሁም ሁሉም ሰው ከችግር ነጻና ደስተኛ፣ አንተ ብቻ ችግረኛ እንደሆንክ በማሰብ ድብርት ውስጥ ትገባለህ፡፡

በተቃራኒ ግን የችግሩ ማዕበል ባይይረጋጋም አንተ ስትረጋጋ መነጫነጭን ታቆማለህ፣ የፈጠራ ብቃትህ ይወጣል፣ አዳዲስ መንገዶችን ትቀዳለህ፣ ችግሩን ጠንካራ ለመሆን ትጠቀምበታለህ፣ ከችግሩ ባሻገር አልፈህ ከሄድክ በኋላ ለብዙዎች ደጋፊ ትሆናለህ፡፡

በል የችግሩ ማዕበል ባይረጋጋም አንተ ተረጋጋ!!

@manyazewaleshetu

827 viewsedited  17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 11:09:13 የሚጠብቀን አይተኛም !

ሁላችንም የፈጠረን ፈጣሪ እጅ ላይ ነን በራሳችን የቆምን አደለንም የምድር ባለቤት የሁላችን ፈጣሪ ሁሌም እኛን ለመጠበቅ አይተኛም አያንቀላፋም ስለዚህ ምንድነው ታድያ የሚያስፈራን ?

ቤታችንን ከሌባ ለመጠበቅ ዘበኛ ወይም አደገኛ አጥር ወይ ደግሞ ውሻ አስቀምጠን ነፃ ሆነን ያለስጋት እንተኛ የለ ታድያ ከሁሉ በላይ ሁሉን የፈጠረ ፈጣሪ እየጠበቀን ካለ ምንም ነገር ሊያሸንፈን እንዴት ይቻለዋል ?

የተባረከ ቀን ተመኘኝ
@manyazewaleshetu
451 viewsedited  08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 21:06:38 ራስህን እመነው!

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ። የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው።

ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
673 viewsedited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 08:10:24 ለትርፍ ድከም !

ይደክማል አይደል? የምትፈልገው ቦታ ሩቅ ሲሆን ያን ሁሉ መንገድ መጓዝ ይደክማል መሀል ላይ ስትደርስ አቁም አቁም በቃህ ይልሀል አይደል ግን ደግሞ አስበኸዋል ሲበቃህ ስትቆም ልትመለስ ስታቅድ ያን ሁሉ ደክመህ ደክመህ ልፋትሀሰ ያለምንም ውጤት ባዶ ሲቀር ? ደግሞ ይበልጥ የሚያሳዝነው የመጣህበትን መንገድ ድጋሚ ስትመለስ የምትለፋው ልፋት መልሶ ያው መሆኑ ነው ለህልምህ ብትደክም እኮ ለውጤት ነው ለመመለስ ግን መድከም ትርፉ ኪሳራ ነው !

መልካም ሰኞ ተመኘን
@manyazewaleshetu
170 viewsedited  05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 21:26:13 ሳይንስ እና ፈጣሪ

ሳይንሱ "ሰው ደጋግሞ ያሰበው ሀሳብ ህይወቱ ላይ ይገለጣል" ይላል። ይሄንን ብናውቅም ብዙ መጥፎ ሀሳቦችን ደጋግመን እናስባለን ግን አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን ከሀሳብ በዘለለ እውነት ሆነው አያውቁም። ያሰብናቸው ጥቂት መልካም ሀሳቦች ግን ተሳክተው አይተናል።

አየህ ፈጣሪ ከሳይንስ በላይ ነው፤ ደጋግመህ ያሰብከውን ብዙ ክፉ ነገሮች ሁሉ አስቀርቶ ትንሿን በጎ ሀሳብህን እውነት ያደርጋል። ሀያሉ አብሮህ ከሆነ አንዲት 'ተመስገን' የምትል የምስጋና ጠጠር ሚሊየን ግዙፍ ጭንቀቶችህን አመድ ታደርገለች። ወዳጄ አትጨነቅ አልልህም ግን አመስግን!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
622 viewsedited  18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ