2022-07-11 10:23:01
መከራው ሲበዛ መልካምነትሽ ይፈተናል::ልብሽ ሳይወድ ይጨክናል::
-
የአለም ክፋት ካስጠላሽ የአምላክ መልካምነት አለልሽ::
-
ከአምላክሽ መንፈስ ውጪ የአለም ነገር ጊዚያዊ ነው::የምታገኚው ሰው ጠባዩ ማስመሰል ነው::
-
በመጥፎ ሰው ምክንያት መልካምነትሽ አይጥፋ::
-
እንደ እንሱ ክፋት ሳይሆን እንደ አምላክ መልካምነት አስተናግጃቸው::
-
ያንቺ የህይወት ጨዋታ ከአምላክሽ ጋር ብቻ ነው::ይህ ዘለዓለማዊ የመንፈስ ጉዞ ነው::
-
ለእያንዳንዱ መጥፎ ሰው መልካም ስትሆኚ በእያንዳንዱ ሰከንድ አምላክ መልካም ይሆንልሻል::በአይን የማይታይ በረከቱን ወደ አንቺ ያመጣልሻል::
-
ከአለም ስኬት ሲያርቁሽ ወደ አምላክ ያቆርቡሻል::እና ምን ያናድሻል?
-
ሲጀመር የተጎዳሺው አምላክን ከልብሽ ስላራቅሺው ነው::የቀደመ መልካምነትሽን ስላጣሺው ነው::
-
ከአለም እና ከሰው ከአምላክ ብቻ የሚገኘውን ፍፁምነት አትጠብቂ::በሰዎች ክፋት እና ስህተት ስርፕራይዝድ አትሁኚ::
-
አለም ካስጠላሽ አምላክ አለልሽ::
-
አምላክን ግን በልብሽ ማዕከል አግኚው::የውስጥሽንም ፍላጎት ንገሪው::ሰዎች የሰበሩትን ስሜት ያክመው::ያለ እንክን በረከቱን ያቀርበው::የልብሽንም ሰላም ይመልሰው::
-
አሜን!!!
Photo : አርባምንጭ ጫካ ውስጥ(የማንያዘዋል እሸቱ ሪትሪት!)
-
@manyazewaleshetu
2.1K viewsedited 07:23