Get Mystery Box with random crypto!

ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewaleshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል?

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-01-06 10:00:51 #ፅናት_ያስፈልግሀል!

አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤ በህይወት የሚያሸንፈው ብርቱ የሆነ ወይ አስተዋይ የሆነው አይደለም፤ ውስጡ ላመነበት ነገር እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ነው።

ወዳጄ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ላመንክበት ጉዳይ ነገር ዋጋ መክፈል መኖር ጀምር ከዛ በአላማህ ፅና!

ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው
@manyazewaleshetu     
214 viewsedited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 21:45:55 ከሰዎች ብዙ አጠብቅ!

ሰዎች የማይረዱህ አንተ ጋር እውነት ስለሌለ አይደለም፤ ልፋትህን የማያደንቁልህ እየጣርክ ስላልሆነ አይደለም፤ ለመልካምነትህ መልሳቸው ተቃራኒ የሆነው አንተ ጋር ችግር ኖሮ አይደለም።

ችግሩ ካንተ መልካምነት አይደለም፤ ችግሩ ከነሱ አንድ ነገር መጠበቅህ ላይ ነው። ከሰዎች ምንም አጠብቅ፤ የማይታለፍ የሚመስለውን አሳልፎ ለዛሬ ያደረሰህ ፈጣሪ ነው፤ ከሱ ብቻ ጠብቅ! አለቀ! ወዳጄ ካንተ የሚጠበቀውን ግን ሁሌም ማድረግ አትርሳ!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
585 viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:01:00 #አንጣደፍ !

ሁላችንም በዚች ምድር ላይ ስንኖር ትልቅ አሻራ ጥለን ማለፍ እንፈልጋለን ፤ ፍላጎታችን መልካም ሆኖ ሳለ ግን ነገሮች በአንዴ ካልተቀየሩ እያለን ከራሳችን ከሚገባው በላይ ስንጠብቅ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ሳናደርግ እንቀራለን !

እውነት ነው ትልቅ ደረጃ መድረስ አለብን ግንበሂደትና በትዕግስት ለራሳችን ጊዜ በመስጠት ይሁን!
በህይወትዎ ማስተካከልና ማሻሻል ለሚፈልጉት ክፍተትዎ ከጎንዎ አለው ፈጣሪም አለ።
         
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው
@manyazewaleshetu       
489 viewsedited  09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:00:10 ለራስህ ዋጋ ስጥ !

በህይወትህ እያጋጠመህ ያለውን ችግር ችላ አትበለው ! እህቴ እያወላወልሽ ከተቸገርሽ ነገሮችን በምታስቢያቸው ሳይሆን ባልፈለግሻቸው መንገዶች እየተከናወኑ ከሆነ !

ያቀድሽውን ነገር ለማሳካት ከተቸገርሽ እድልሽ ሆኖ ሳይሆን አንድ ሳታውቂው እየያዘሽ ያለ ያለፈ ታሪክ ፣ ልማድ ወይም ደግሞ ያልታከመ ማንነት ኖሮ ነው!

እናም ወደራስሽ ዞር ብለሽ የችግሩን መሰረት ከስሩ ለማጥናት እና ለመቀየር ስሪ ! ሁሌም ለራሳችን ትኩረት ሰጥተን መንገዳችንን የማስተካከል ግዴታ አለብን!

ቆንጆ ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
510 viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 21:19:27 እንደምትቀይረው እመን!

ጂም ሮን የተባለ ደራሲ ላንተ ብሎ ፑሽ-አፕ (ስፖርት) እንዲሰራልህ ሌላ ሰው አትቀጥርም ስለዚህ ከሌላ ሰው ብዙ አጠብቅ ይለናል። የኛን ሸክም ማንም አይሸከምልንም፣ እንደውም እኛ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሸክም ማቅለል እንደምንችል ማመን አለብን።

አሪፍ ነገር ስናገኝ በልፋቴ እንደምንለው ከባድ ነገር ሲገጥመንም በጥፋቴ ማለት አለብን። የኛ ጥፋት መሆኑን ስናምን ለመፍትሄው ግማሽ መንገድ ተጉዘናል። ሰበብ እንደሚያበዛ ሰው ቆሞ የሚቀር የለም!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu
638 viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 10:29:01 #ሁሉንም_ታልፋለህ!

ለራስህ ምን አይነት ጀግና እንደሆንክ ማሳየት አለብህ! ለምትወዳቸው ትደርሳለህ እንጂ አንተ የሌላ ሰው እርዳታ ጠባቂ አይደለህም! ወዳጄ አታስብ፤ ከማንም በላይ ፈጣሪ ይወድሀል፤ በህይወትህ አላልፉም ያልካቸውን ከባድ ጊዜያት በሙሉ አልፈሀል።

አሁንም ታልፋለህ!

@manyazewaleshetu
64 viewsedited  07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 11:31:23 እረፍት !

እረፍት ማለት በስራ ቀናቶቻችን ለራሳችን ማድረግ ያልቻልነውን ነገር ማድረግ የምንችልበት እድል የምናገኝበት ወደራሳችን ወደማንነታችን መለስ ብለን የማየት እድል የምናገኝበት ቀን ነው ስለዚህ በደንብ አድርገን በሚገባ እንጠቀምበት ሲያመልጠን እንዳንቆጭ ያለንን አናባክን !

መልካም ሰንበት ተመኘን
@manyazewaleshetu
779 viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 19:01:14 #መቋቋም_ሲያቅትህ!

የህይወት ፈተናዎች የሚደጋገሙት ማን እንደሆንክ ይበልጥ እንድታውቅ ነው፤ በተለይማ መቋቋም ሲያቅትህ ሊያበረቱ ይችላሉ።

ብረት እንደ ጋለ ነው የሚቀጠቀጠው ምክንያቱም ያኔ የምንፈልገውን ቅርፅ ለማስያዝ ይመቻል። አንተም በደስታህ ወራት ፀባይህን ህይወትህን ማሻሻል ላይታይህ ይችላል ትዘናጋለህ፤ ፈጣሪ ሊያነቃህ ፈተናዎችን ይልካል ካልሰማህ ሌላም ይጨምራል እንደ ጋለ ነው ሚቀጠቀጠው ያልኩትን አትርሳ።

ታዲያ ምን ይሻላል? መፍትሄው ፈጣሪ ምን ሊያስተምረኝ ነው ብሎ ማሰብ፤ ከዛ በዚህ ከባድ ፈተና ውስጥ ግዙፉና ሀያሉ ማንነትህ ሲወጣ ታየዋለህ!

መልካም አዳር ተመኘው
@manyazewaleshetu
850 viewsedited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 13:37:23 ርዕስ: የልማድ አስደናቂ ሀይል
ደራሲ: ጄምስ ክሌር
ዘውግ: self help
የገፅ ብዛት:264
Atomic Habits by James Clear

በትንሽ ለውጥ ትልቅ ውጤት

ልምዶቹን ለመለወጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የግድ ማንበብ ያለበት መጽሐፍ ::

@manyazewaleshetu።
820 viewsedited  10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 11:12:57
ብራዚላዊው ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ማምሻውን በ 82 አመቱ አርፏል። RIP
1.1K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ