Get Mystery Box with random crypto!

የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsihofoch — የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsihofoch — የተፃፉ ሃሳቦች•°•°•°•
የሰርጥ አድራሻ: @tsihofoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 147
የሰርጥ መግለጫ

ልቦለድ /ኢ-ልቦለድ ብቻ በተከሸነ ጥኡም የብዕር ቀለማት
የሚለቀቅበት ቻናል ነው! …ሃሳብ ፣ የተፃፉ ፅሁፎች ካሎት @tizta4 ይጠቀሙ ………! @keneyalew_teweld
ንም ይጎብኙ !!!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2020-09-01 06:14:42 ‹‹ሻይ በምሬት››
በ ሕይወት እምሻው ……………

ዛሬ በጠዋቱ አስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝና ስራ ከመሄዴ በፊት አንድ ወዳጄን ለማግኘት አስፋልት ዳር ካለ የሰፈር ካፊቴሪያ ተቀምጬ ቅመም ሻዬን በብርድ እጠጣለሁ። ወሬ አያለሁ። ነፋሱ ይጋረፋል። ብርዱ ያንዘረዝራል።
በትንሽ ብርጭቆ የቀረበልኝ ሻይ ስላልጠቀመኝ ሁለተኛ አዘዝኩና ፕላስቲክ ወንበሬ ላይ እየተመቻቸሁ ወደ ጎን ዞርኩ።

እኔ ያለሁበት ካፊቴሪያ አጠገብ የሚገኘው ስጋ ቤት እና ግሮሰሪ ገና በማለዳ ቄጠማውን ጎዝጉዞ (አሁን አሁን ሁሉም የአዲሳባ ስጋ ቤቶች መለያ ሆኗል)፣ ደማቅ መብራቶቹን ከጥግ እስከጥግ የሰቀለው የስጋ ግድግዳ ላይ አብርቶ ደንበኛ ይጠብቃል።

ቢላውን ደጋግሞ የሚሞርደው የሉካንዳ ቤቱ ሰራተኛ ሲሞርድ የሚያወጣው ድምፅ ደምበኛን ከአስፋልት ጠልፎ ያስገባlt ይመስል ሳያቋርጥ መሳሉን ቀጠሏል።

‹‹እስቲ አሁን ገና ሁለት ሰአት እንኳን ሳይሞላ ማነው ስጋ ቤት መጥቶ ቁርጥና ጥብስ የሚያቀላጥፍ…? በዚህ ያበደ ኑሮ ማነው እንዲህ የደላው…›› በሚል ሃሳብ ከመያዜ አይኖቼን ከባለሞረዱ ሰው ዝቅ ሳደርግ በቄጠማ ከተሸፈነው የቤቱ በረንዳ ወለል ላይ ከተቀመጡ ስምንት የሚሆኑ ፕላስቲክ ወንበሮች አራቱ በሰው እንደተያዙ ሳይ ገረመኝ።
ከዚያ ደግሞ በማን እንደተያዙ ስመለከት ይባስ ገረመኝ።አራቱም በእድሜ የገፉ ሰዎች ናቸው።ሁለቱ ደግሞ ነጠላ እና ወፈር ያለ ሹራብ ቢጤ የደረቡ እናቶች ናቸው። አንደኛው አዛውንት ምርኩዝ ይዘዋል።አራቱም አንድ ጠረጴዛ ከበው ይቀመጡ እንጂ አንድ ላይ የመጡ አይመስሉም። ከሚታየኝ አይነጋገሩም።
እየበሉም እየጠጡም አይደለም። ጠረጴዛቸው ባዶ፣ እጃቸው ቁሩን ሽሽት እኪሳቸው፣ ወይ ደግሞ ከነጠላቸው እና ስር ነው።ግራ ተጋባሁ።
በእኔና በእነሱ በረንዳ መሃከል ሰፊ ርቀት ስላልነበር ብቻዬንም ከምሆን፣ ጉጉቴም በከንቱ እንዳይቀር ታስተናግደኝ የነበረችውን ልጅ ጠራሁና፤

‹‹እሙዬ…እዚያ ጋር ብሄድ ችግር የለውም አይደል…ሻዩን እዛ አታመጪልኝም?›› አልኳት።

‹‹ችግር የለውም ሂጂ…! የእኛው ማለት ነው›› ስትል አፍታም አልወሰደባት።
ተንስቼ ሄድኩና አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ አንዱን ወንበር ጎትቼ እየተቀመጥኩ…

‹‹እንዴት አደራችሁ….? በጣም ይበርዳል አይደል…?›› ብዬ ወሬ ለመጀመር የመጀመሪያውን ሙከራ አደረግኩ።
አራቱም በየተራም፣ በአንድ ጊዜም ባልጠበቅኩት ጉጉት፤ …………………

‹‹እግዛሄር ይመስገን….እንዴት አደርሽ ልጄ….አዎ…ይበርዳል…በጣም ይበርዳል .››

የሚሉ ቃላትን መልሰው ወረወሩልኝ። ሁኔታቸው የዝምታቸውን አጥር የሚያፈርስ ሰው በማግኘታቸው የተደሰቱ ያስመስልባቸዋል።
ቀረብ ብዬ ሳያቸው ኑሮ የሞላላቸው፣ የደላቸው፣ በጠዋት ሉካንዳ እና ግሮሰሪ የሚያስመጣ ምቾት ያላቸው አለመሆኑን ከፊታቸው ተረዳሁ እና ይበልጥ ግር ብሎኝ፤ እርግጠኛ ሳልሆን…

‹‹እንዴት በዚህ እድሜያችሁ በዚህ ጠዋት ስጋ ልትበሉ እና መጠጥ ልትጠጡ መጣችሁ?›› ብሎ መጠየቅን ፈርቼ፣

‹‹በጠዋቱ እንዴት ነው እዚህ….›› ብቻ አልኩ።

‹‹ሰልፉ ሳይበዛ…ሰዉም ሳይነጋጋ እንድረስ ብለን ነዋ!›› አሉ ወፈር ያሉት እናት ፈጠን ብለው።
ምንድነው ያሉት? ሰልፉ ሳይበዛ…ሰዉም ሳይነጋጋ እንድረስ ብለን ነዋ?

‹‹የምኑ ሰልፍ?›› አልኩ አሁንም በበዛ ጥንቃቄ አራቱንም እያየሁ።

‹‹የዚህ ነዋ ልጄ…!›› አሉ የቅድሟ ሴትዮ አሁንም ፈጠን ብለው በአመልካች ጣታቸው በጎን በኩል ከጀርባቸው ወዳለው ግድግዳ እየጠቆሙ። አይኔ ጣታቸውን ተከትሎ ሄደ። ፓስታ ቤት። ካፍቴሪያውም፣ ሉካንዳ ቤቱም ያሉበት የኮንዶሚኒየም ህንፃ ስር ያለ ፖስታ ቤት።
ነገሮች በፍጥነት ተያያዙልኝ።
እነዚህ አራት አረጋውያን በዚህ ጠዋት፣ በዚህ ብርድ ሉካንዳ ቤት ደጃፍ የተቀመጡት ጮማ ሊቆርጡ፣ ቢራ ሊጠጡ አይደለም። በፖስታ ቤት በኩል የሚሰጣቸውን የጡረታ ገንዘብ ሊቀበሉ ነው።

‹‹ልጁ ስለሚያውቀን ከምንቆም ያስቀምጠናል…የተባረከ ልጅ ነው….›› አሉ ሌላኛዋ ሴትዮ

የሚቀጥለውን ጥያቄዬን ሳልጠይቅ።
ያልጠበቅኩት ስለገጠመኝ፣ ወሬውን በምን እንደምቀጥል ሳሰላስል ልጅቱ ሻዬን ይዛ መጣችና ሁሉንም በየጊዜው እንደምታያቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ አይታ፣ በቀልድ ለዛ ወፍረሟን ሴትዮ እያየች፤

‹‹ እማማ… ዛሬ መቼም ተቀብለው ኪሎ ቁርጥ ሊበሉ ነው አይደል…?ብቻ ሳይጋብዙኝ እንዳይሄዱ…›› አለች እየሳቀች።

አራቱም ከት ብለው ሳቁ። እኔም ፈገግ አልኩ።
እማማ በቅድሙ ፍጥነታቸው ‹‹አይ እናቴ…ቁርጡን እንኳን ተይው….በህልሜም አልመኘው….ይመስገነው…ቢያንስ ይህችን ሶስት ቀን ያቺን ቡናዬን በስኳር እጠጣለሁ…›› ብለው እንደገና ሳቁ። አሁንም ልጅቱም፣ ሶስቱም አዛውንት አጀቧቸው።

እኔ ግን አንጀቴ በሃዘን ታጠፈ።
የቀልዳቸው ምሬት እንኳን ከእነሱ ጋር ሊያስቀኝ የውሸት ፈገግታ ፊቴ ላይ መሳል ስላላስቻለኝ ፈገግ ለማለት እየታገልኩ ልጅቱ እንዳትሄድ በእጄ አቆምኳትና አራቱንም እያየሁ በእኔ ግብዣ ሻይ ቡና ይሉ እንደሆን ጠየቅኩ። ሁሉም በትህትና እምቢ አሉ።እህም።ዝም-ቅዝዝ አልኩና ሻዬን ለመጠጣት አነሳሁ። አሁን ግን ቅድም የጣፈጠኝ ሻይ… በስኳር ፋንታ የእማማ የኑሮ ምሬት የገባበት ይመስል ክፉኛ መረረኝ።

ውብ አሁን !

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
355 views03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-14 08:44:24 የማለዳ ማስታወሻ

ጧት አደል። ሀሳቦችህ ከ እንቅልፍ ጋር ተኝተው ነበሩ። ልክ ስትነቃ እነ አጅሬ ሀሳቦች አብረው ይነቃሉ። እነርሱም ፊትህን ልትታጠብ ከመሄድህ በፊት ያዛጋሉ።................... በል መጡ..... ....... የቤት ኪራይ ቀን አልፎ እንዳልከፈልክ ትዝ ይልሀል። የደሞዝ ቀን ርዝመቱ ሰማይ ይሆንብሀል።

ፊትህ ላይ ያሉት የውሃ እንክብሎች እየተንሸራተቱ ፂምህ ላይ ይንጠለጠላሉ። አከራይህ በር አካባቢ መኖራቸውን ልታረጋግጥ የመስኮትህን መጋረጃ በቀስታ ትገልጣለህ የሉም!!
ልብስህን በፍጥነት ትለብሳለህ። ብቻህን አየኖርክ ካልሲውን ማን ወሰደው እያልክ ትነጫነጫለህ።
ከ አልጋ ስር በፊት ያደረከውን ካልሲ ይሄማ ንፁህ ነው ብለህ ትለብሳለህ።ሸሚዝህን እየቆለፍክ መስኮት ዳር ቆመህ አከራይህ መኖራቸውን ታረጋግጣለህ።የሉም!!

በርህን ከፍተህ ወደ ግቢው በር ሩጫ በሚመስል እርምጃ ትራመዳለህ። በሩ እንደ ሰማይ ይርቅሀል። ከኋላህ ልክ Temple Run ጌም ላይ ያለው ጭራቅ የሚያባርርህ ይመስልሀል።የጊቢው በር ላይ ስትደርስ ሀይሌ ገ/ስላሴን የሆንክ ይመስልሀል። የ ማራቶን ሪከርድ የሰበርክ ይመስልሀል። በሩን ስትከፍተው። መጀመሪያ የሆነ የምታውቀው ድፍን የሴት ጫማ ታያለህ። ጫማው ውስጥ በ ካልሲ የታጅለ አግር ታያለህ። እንደገና ከፍ ስትል ባለ አበባ ሰማያዊ ቀሚስ ታያለህ። ቁርጤን ልወቅ ብለህ ትንሽ ቀና ስትል ነጠላ የለብሱ፤ ለምለም ቄጠማ የያዙ፤ ወይዘሮ አከራይህ። ፈገግ ......

ደና ዋል ተከራይ።

* * *
ዣንዣድ

የማለዳ ማስታወሻ ጀምረናል።
ይቀላቀሉን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
322 viewsedited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-08-01 08:06:42 # ሲጨልም

ደራሲ - እንዳለጌታ ከበደ

ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ
"ልጄ" አሉት አስተናጋጁን ፤"የገዛሁትን መድሀኒት
ይዤብህ መጣሁ ፣ እባክህ የሰጠኸኝ ወስደህ.."
አላስጨረሳቸውም።ግድግዳው ላይ ወደተለጠፈ
ው ፅሁፍ አመለከታቸው።

'የተሸጠ መድኃኒት አይመለስም' አረጋዊው በለሰለሰ ቃላት መማፀን ያዙ።

"ሰውዬ ዞር በል!ስራ ልስራበት!ለእንቶ ፈንቶ ጉዳይ የማባክነው ጊዜ የለኝም..."አለ ቁጣው እየተወለደ" ዛሬ በዚህ ሰውዬ እንድጨቀጨቅ ተፈርዶብኛል ልበል?"

"እባክህን ልጄ አሳፋሪ ነገር ደርሶብኝ ነው።...
ዘመድና ዕድር የሌለኝ ከርታታ ሽማግሌ ስለሆንኩ
እንጂ..."አሉት ትሁት በሆነች ፈገግታ ሊያባብሉት
እየሞከሩ፤ " ቅናሽ ዋጋ ብትከፍለኝም..."

"ይሄ ሰውዬ ነካ ያረገዋል ልበል?" አለና ሌሎች
መድኃኒት ገዥዎችን ያስተናግድ ገባ።"ከያዙ
አይለቁ"

"ድህነት ቢፈትነኝ ነው ልጄ" አሉ - ያደፈና የነተበ
ነጠላቸውን እያሳዩት። ነጠላው ከሰውነታቸው
በከፋ ሁኔታ ያረጀ ኮታቸውን ደብቆላቸዋል፤

"አቅሜ የደከመ ባይሆን ኖሮ..."አሉት፤ጫማ ካገኘ
የከረመ እግራቸውን እያዪ። አንዲት ተስተናጋጅ

"አልመልስም ካለ አልመልስም ነው። ለምንድነው ሚነዘንዙት?" አለች በሚነጫነ
ጭ ድምፅ ፤"ይሄኮ ፋርማሲ እንጂ አዛውንቶች
የሚጦሩበት የድኩማን መርጃ ድርጅት አደለም"

አነጋገሯን ያልወደደው የሚመስል ሌላኛው
ጎልማሳ ደግሞ፤ "መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ የገዙ
ከዚሁ መደብር ነው?"የሚል ጥያቄ አመጣ።

"አዎ ዶክተሩ ፅፎ በሰጠኝ መሠረት" ብለው መለሱለት።

"ምን ያህል ፈጀብዎ?"

"ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም።መድኃኒቱን ወስዶ ግማሹን እንኳን ቢሰጠኝ ምን አለበት?" አሉ በሃዘኔታ

"የሁለታችንንም የጋብቻ ቀለበት
አስይዤ ነው ከማምነው ሰው የተበደርኩት"

"መድሀኒቱን ለምን መመለስ ፈለጉ ?" ዘንቢል
ያንጠለጠሉ አንዲት አሮጊት። በዚህ ጊዜ አስተናጋጁ ጣልቃ ገባ ፤

" ባህላዎሕክምና ብትከታተል ኪስ እደማታራቁት ገብቷቸው ይሆናል!ወይ ፀበል ሊያጠምቋት!ወይ..."

"አይ ልጄ ! ጉዳዩን ብታውቀዎ ኖሮ ያፌዝክበት
ምላስህን ታፍርበት ነበር..." አሉ እንባ እየተናነቃቸ
ው ።"መድኃኒቱን ምን ላርገው ልዋጠው ወይስ?
ሽንት ቤት ልጨምረው?"

"ለባለቤቴ ነው ምገዛላት ብለው አልነበር?......
በጠና ታማብኛለች፤የእድሜዬ ጀምበር እየጠለቀ
ባለበት ሰዓት ለእህል ያላነሱና ለትምህርት
ያልደረሱ ሦስት ልጆች በትናብኝ እዳትሄድ
ፀልይልኝ ፤ ብለውኝ አልነበር?"

"ማለቱንስ ብዬህ ነበር ልጄ!.....ብዬ ነበር"

"እና ሩብ ሰዓት ያህል እንኳን ሳይቆዩ ሃሳብዎን
አሰርዞ ፤ የገዙትን መድኃኒት የሚያስመልስ ምን
ተዓምር ተፈጠረ?!" ቅድም የማይመለከተኝን ነገርሲዘላብዱልኝ ነበር እኮ"አረጋዊው አንገታቸውንደፉ። "እኮ ምን ቢፈጠር ነው.....?"

"ቤቴ ሳልደርስ ነው አንተ ዘንድ የመጣሁት"

"ለምን?" አሉ ሌሎቹ

"ሰፈርተኞቼ ደጄ ላይ ሲጯጯሁ ዐየው።ባለቤቴን
በህይወቷ ልደርስላት አልቻልኩም!"አሉ አረጋዊው
ድምፃቸው እየሻከረ፤እንባቸው እየወረደ።

የመድሀኒት ሻጭው ፊት ላይ ፀፀትና ድንጋጤ
እየታየ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ በሻከረ እጃቸው
ላይ አኖረ። ሌሎቹም ኪሳቸውን ይፈታትሹ ጀመር

"ይባርካቹ ልጆቼ! ከፈን መግዣ ስላልነበረኝ እንጂ
........"እንባ ተናነቃቸው።መንሰቅሰቃቸውን እየቀጠሉ ወጡ።

ፀጥታ!!!!!!

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ !ለምንድነው?
ለማዘን ወይም መልካም ለመሆንና ሰዎችን
ለመውደድ ምክንያ ምንፈልገው?????
እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ???

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
320 views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-13 19:18:42 ጭንብሊቲ እና አጋጣሚዉ


አቶ ኮረና ሀገራችንን ከጎበኛት በኋላ ጭንብል መልበስ ግድ ሆኗል፤ እኔም ከለባሾቹ ታጭቼ መልበስ ስጀምር መጀመሪያ ላይ ጆሮዬን ያቃጥለኝ ነበር ዳገት ስወጣ ደግሞ አንገቴን የታነኩ ያህል ያፍነኛል፤ በኋላ ላይ ግን ወደድኩት አቦ እንዴት መሠላችሁ

፦ የሆነ ቀን ነዉ በጣም ተናድጄ ነበር፤ ሰአቱም ደረሰና ወደስራ ለመሄድ በፍጥነት ለብሼ(ጭንብሉንም) ጉዞ ጀመርኩ፤

ወደ ስራ በዛ አካሄዴ ንዴቴ ተጨምሮበት እብድ አስመስሎኛል፤(ለነገሩ አለመሆኔን በምን አዉቃለሁ)
ለማንኛዉ እየለፈለፍኩ መሆኔን ያወኩት የራሴ ትንፋሽ ሲያቃጥለኝ ነበር ። እጄንም ሳየዉ ይንቀሳቀሳል፤

"አቤት ቅሌት" አልኩ የታወቀኝ ምናልባት ስራ ቦታዬ ስለደርስኩ ይሆናል (መድረሰኔም ልብ አላልኩ)
ትንሽ አሰብ አድርጌ "ወይኔ አሁን ማክስ ባለብስ ኖሮ ሰዉ አበደች እንዴ? አይለኝም" ነበር አልኩ ትዝ ይለኛል የሆነ ቀን መንገድ ስሄድ ኤርፎን ሰክቼ የበእዉቄን(በእዉቀቱ ስዩም) ወግ እየሰማሁ ሲሄድ አለመሳቅ አልቻልኩምና ሳቄን ለቀኩት!

መሃል አስፓልት ላይ መሆኔ እራሱ አልታወቀኝም ለነገሩ መሆኔንም ያወኩት "ምፅ እቺን የመሠለች ልጅ ስታሳዝን" ብላ አንድ ጎልማሳ ሴት በእዝነት አንገቷን ስታንቀሳቅስ ነዉ። (ይኸዉ ከዛ ወዲህ በኋላ መንገድ ላይ የበእዉቄን መስማት ትቻለሁ) ይሄንኑ በግርምት እያሰብኩ ንዴቴ እንደረገበልኝ አልታዘብኩም ነበር፥

"ፐለዉ! በቃ እቃ ማጠብ ሊቀር ነዋ(ስናደድ እቃ ነዉ ማጥበዉ )
ኦ! ይሄ ነገር ለካስ ትንፋሽ ላለማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ለንዴትም ሃሪፍ ነዉ። ፐ!"

ጭንብሊቲ አሁንም ቀጥላለች
በሁለተኛው ቀን ከመደብራችን ፊትለፊት የሆኑ ሰዎች ይጣላሉ ከመጣላታቸዉ የበለጠ ግን የሚጣሉበት መንገድ ስለተመቸኝ ቆሜ መሾፍ ጀመርኩ፤ የአዋቂ እርምጃ ተራርቀዉ ጭንብላቸዉ አፋቸዉን ብቻ ሸፍኖት በአፍንጫቸዉ እያነፈነፉ፣ አንደኛው እግሩን ልክ ካራቴ ፊልም ላይ እንዳሉት በሩቁ እያንጠራራ ይማታል(ደግሞ አልደረሰበትም ምፅ) ያኛዉ ደግሞ በምርኩዝ ወገቡጋ ይለዋል፤

"ኮሮናዊ መጣላት መሆኑ ነዉ አልኩ" ለካስ ድምፅ አዉጥቻለሁ ማዉጣቴንም ያወኩት "ሂሂሂሂ አንቺ ቀዉስ" የሚል ድምፅ ስሰማ ነዉ። የኔ ጉድ አያልቅም!

"ኢሺሼ ሲያስጠላ" አለች አጠገቤ ያለችዉ
"ምነዉ" አልኳት
"አታይዉም" ብላ እጇን ወደሚጣሉት ጠቆመችኝ!
ጉዴን ሳስብ ረስቼዉ ነበር፤ ሳየዉ ለካስ አንደኛው "አኽኽ ቱ" ብሎ ሊተፋበት ሲል የራሱ ጭንብል ላይ ለድፎታል!

አመሌ ተነሳብኝና ሆዴን እስኪያመኝ ተንከተከትኩ!

ገና በጭንብሊቲ የማየዉ ጉድ እየታየኝ፦"ባንቺ ምክንያት ነዉ በአንቺዉ ምክንያት" ብዬ ለጭንብሊቲ መዝፈን አሰኘኝ፣ ያዉ ለብቻችን ስንሆን ሚስጥረኛዬም አይደለች


………… ፈትሒያ

ስለ-ፅሁፉ ሃሳብ አስተያየት ካላቹ ፦ @Fethetulletiya
ይጠቀሙ………………

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
424 viewsedited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-12 06:48:52 ከጨረቃ ስር. . . .


. . . ኢዛና . . . .

. . .ክፍል . . . . . . . .


"አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ
ድንገት በሕልሜ አይቼሽ ብነቃ …"

የዳዊትን ዜማ ጮክ ብላ ታዜማለች : ስታዜም ወደጨረቃዋ አንጋጣ ነው ከጀርባዋ የተከፈተው የመጠጡ ቤት የሚንቦገቦግ መብራት ከፊል የፊቷን ገፅ እየቀያየረ ያሳየኛል ከፊል ፊቷን ደግሞ በጨለማው ውስጥ ያበራችው የምታዜምላት ጨረቃ ብረሐን ታሳየናለች :: ሲጋራዋን አንዴ ስትስበው እሳቱ ፈመ :: ከሷ ጎን አንዲት ሌላ ሴት ፀጉሯን እንደማስተካከል እያለች ድራፍቷን ትጎነጫለች ከመጠጥ ቤቱ ውስጥ ”ልጁን ያያችሁ አዬ እስቲ ን .ገ .ሩኝ …” ‘ሚለውን ዜማ ብዙ ድምፆች አጅበው ያዜማሉ :: የምሽቱ አየር ሞቅ ያለ ስለሆነ ከውስጥ ይልቅ በረንዳው ተመችቶኛል :: እዚህ ናዝሬት ከመጣው 1ሣምንት ሆነኝ የመጣዉበት ዓላማ ስላልተሳካ ዛሬ በተለይ ምርር ብሎኝ ነው የዋልኩት እዚች ቤት ሆኜ የምሽቱን ንግስቶች መልክ ሳጠናና ሳስተውል ይሄው ዛሬ 3ኛ ቀኔ ነው ::

አንዲት አጭር ሞንዳላ ሴት ከማጨሠው
'ሲጋራ‘ወጋው ‘ ስትለኝ ሌላ ሲጋራ ስሰጣት

”ፍሬንድ ምነው አንተ ደግሞ ቺክህ ጥላህ ኮበለለች እንዴ … የሆነ ትካዜ ምናምን ነገር … አቦ ግባና ወዝወዝ በልበት ካስፈለገም ድብርቱን ….”
አለችና ሌባ ጣቷን ካጣበቀቻቸው ሁለት ጣቶቿ ጋር ጧ ! አድርጋ እያማታች

”እኛ እንነቅልልሀለን ”
ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች : በፈገግታዬ ሸኘዋት ያቺ ልጅ አሁንም ታዜማለች ሢጋራው አልቆ አመድና ቁራሽ ስፖንጅ ሆኖ ተወርውሮዋል …

”መስኮት ከፍቼ ውጪ ባይሽ
ጨረቃም የለች አንቺም ጠፋሽ
ዳግም አልተኛ ምን አደርጋለሁ
እስክትመጪ እጠብቃለሁ ”

ስታዜም ወደ ጆሮዎቿ ጥግ ተንጋደው ቀልበስ ያሉ ዓይኖቿ ይጨፈናሉ ቀለም የቃሙ ከናፍርቷ ይሾላሉ … የምጠጣዉን ድራፍት ያዝኩና አጠገቧ ሄድኩኝ

”ይቻላል …?”
አልኳት አጠገቧ ያለዉን ወንበር ድራፍት በያዘ እጄ እያመላከትኳት አልመለሰችልኝም …
ከራሷ ጨማምራበት ካልሆነ መቼም የዳዊት ግጥም እንደሆን አልቅዋል ተቀመጥኩኝ

”ጨረቃ ትወጂያለሽ ?”
አልኳት እንደመፍራት ብዬ : ያቺ የቅድሟ ከመፀዳጃ ቤት ስትመለስ ገላምጣኝ ፈንጠር ብላ ተቀመጠች :

”እ … እኔን ነው ?”
አለችኝ ያቺ ጨረቃ አፍቃሪ

”እንግዲያ … ጨረቃዋማ እንኳንስ እኔን ልትሰማ አንቺንም ስታዋራ አላየዋት ለሷ ማወራው ”
አልኳት : ሳቀች ስትስቅ ሸራፋ ጥርሷ ሳቋን ቄንጠኛ አደረገላት :

”ከመጣህ 1 ሠዓት አልፎሀል እንዴት አሁን ታየውህ ?”
አለችኝ ተቀምጬ የነበርኩበትን ወምበር ገልመጥ አድርጋ ቀይ ፊቷ ስጠጋው እንደቅድሙ ሲጋራዋ ፍም ቦግ ብሎ ታየኝ :

”አሁን አይደለም የታየሽኝ ቅድም ነው ዘፈንሽን ማቋረጥ አልፈለኩም ነበር ” አልኳት።

* ይ * ቀ * ጥ * ላ * ል *

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
332 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-08 08:05:06 ህልምና እውነት

----- እቴጌይት

ቀኑን ሙሉ የፍሎሪዳን ሰማይ ተቆጣጥራ የዋልቸው ጸሀይ ከአድማሱ ጋር ፉክክር ገጥማ ላለመጥለቅ እየታገለች የምትፈነጥቀው ጮራ ለውሀው ዳር አካባቢ ልዩ ውበትን ለግሶታል:: ፍቃዱ የዘምባባው ዛፍ ስር አሸዋ ላይ ተንጋሎ ደረቱ ላይ ጋደም ያለቸውን የክርስቲናንእቴጌይቱና ይዳብሳል:: ከበረዶ የነጣ ቀለሟን ከእርሱ ጠይም ቆዳ ጋር አስተያየና ፈገግ ብሎ መዳበሱን ቀጠለ:: ሞቅ ያለውን አየር ለዘብ የሚያደርገው ንፋስ የውቅያኖሱን ውሀ አነስተኛ ማእበል እያሰራ ከአሸዋው ጋር ሲያላትመው የሚፈጥረውን ልዩ ድምጽ በጥሞና እያዳመጠ ሳለ ክርስቲና ቀና ብላ እይታው እጆቹን በለስላሳ ጣቶቿ መዳበስ ጀመረች:: ከመቅጽበት እንደኮረንቲ የሚነዝር ስሜት መላ ሰውነቱ ውስጥ መሰራጨት ሲጀምር ተሰማው:: ጣቱን በጣቷ እያፈተለተለች አንገቱ ስር ስትስመው ትንፋሹ እጥር እጥር እያለ ወንድነቱ እየጨመረ መሄድ ጀመረ:: ከአንገቱ ወደጉንጩ.... ከዛም ወደከንፈሩ ጥግ መሄድ ስትጀምር በመግነጢሳዊ ስበት እሱም ከንፈሯን ፍለጋ መዞር እንደጀመረ ከመቅጽበት የሆነ ነገር ግንባሩ ላይ ጠብ ሲል ተሰማው:: ፍንትው ካለ የረፋድ ሰማይ የምን ጠብታ ነው የመጣው ብሎ ከላዩ ላይ የተዘረጋውን የዘንባባ ዛፍ ቅርንጫፍ ቢያማትር ምንም የተለየ ነገር አልታየውም:: ግንባሩን ጠረገና ሀሳቡን ሲያሰባስብ ክርስቲና አንገቱ ስር እንደተወሸቀች የደረቱን ጸጉር ማፍተልተል ጀመራለች:: አይኑን በስሜት ጭፍን አድርጎ ምትሀታዊ ዳበሳዋን ማዳመጥ ሲቀጥል ከበፊቱ የተለቀ ጠብታ ግንባሩ ላይ ከዛም ጉንጩ ላይ ጠብ ጠብ ጠብ.....ማለት ሲጀምር በእልህ ደስ ከሚለው ስሜት ላለመውጣት ቢታገልም አልቻለም::....ድንገት ከእንቅልፉ ብንን አለና ኩምሽሽ ባለ ስሜት 'ኡፍፍፍፍ' ብሎ ወደጣራው ተመለከተ:: ገዳም ሰፈር ያለው የቤቱ የቆርቆሮ ጣርያ ቀዳዳ ሙዝዝ ያለውን የአዲስ አበባ የሀምሌ ዝናብ እያሾለከ የሚያንጠባጥበው ነበረ ፊቱና እያረጠበው የነበረው:: እንጥብጣቤውን ለማምለጥ አልጋው ላይ ፎቀቅ አለና ኩምሽሽ አንዳለ የክፍሉን ግርግዳ ሲያይ ያለፈው ዓመት ከአሮጌ መጽሄት ላይ ቀዶ የለጠፈው የክርስቲና አጉሌራ ፖስተር አፈጠጠበት:: ወዲያውኑም ትናንትና ከአክስቱ ልጅ ጋር በቪዲዮ ያየወን ፍሎሪዳ ውሀ ዳር የተሰራውን የፍቅር ታሪክ አስታወሰና ቁና ተነፈሰ:: 'ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ....አይ ሕልምና እውነት"

*-----------አለቀ ------------*

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
319 views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-06 14:49:10 --- ሽማግሌው

---- ግሩም ተበጀ

ገና በጠዋቱ --- 2 : 30 ላይ . . . ክሊኒካችን በህ
መምተኛ በተጨናነቀበት ወቅት ነበር አንድ አረጋ
ዊ ወደ ክሊኒካችን የገቡት። በግራ ክንዳቸው ላይ
የቁስል እሽግ ይታያል። በግምት 70 ዓመት የሚ
ሆናቸው አዛውንት ናቸው። በቀስታ አግዳሚው
ወንበር ላይ ተቀምጠው ሰዓታቸውን ማየት ጀመ
ሩ። የቸኮሉ ይመስላሉ።

"ምን ልርዳዎት" አልኳቸው።

የቀስሉ እሽግ እንዲቀየርላቸው ነው የመጡት።
ከ30 ደቂቃ በኃላ ግን ቀጠሮ ስላላቸው ቸኩለዋል

በህክምና ሊያገኙ የሚችሉት ገና ከ1 ሰዓት በኃላ
እንደሆነ ይገባኛል።ምን ማድረግ እችላለሁ! ግን
እስቲ ቢያንስ ቁስሉን ፈትቼ ልየው ብዬ እሽጉን
ስፈታው ቁስሉ ደርቋል።

በጣም ጥሩ!

ከአንዱ ዶክተርጋ ተነጋገሩክ።አስፈላጊውን መድኃ
ኒቶችና የህክምና የህክምና ቁሳቁሶች ወስጄ ህክ
ምናውን አከናወንኩላቸው። አረጋዊው ወደ ቀጠሯ
ቸው በጣም በመቸኮላቸው ምክንያት ትዕግስት
አጥተዋል።አሁንም የሚያዩት የእጅ ሰዓታቸው
ቁስሉ ያለበት ግራ ክንዳቸው ላይ ነው ያለው።
ስለዚህ እንዴት ሰዓታቸውን ይዩ . . .። ቁስሉን እየ
ፈታሁላቸው እሳቸው አሰግገው ሰዓታቸውን ለማየ
ት ይጣጣራሉ።

"ለመሆኑ ይሄ ያህል የቸኮሉበት ቀጠሮዎት የት
ነው . . ."አልኳቸው እንደ ጨዋታ ያህል።

"3 : 00 ሰዓት ላይ ከባለቤቴ ጋር ቁርስ ለመብላት
ቀጠሮ አለኝ" አሉኝ።

"አሀ . . ."

ቁስላቸውን መልሼ አያሸግኩላቸው አረጋዊው ታሪ
ካቸውን አጫወቱኝ። እንዳሉኝም እንዲህ የቸኮሉት
ከሚስታቸው ጋር 3 : 00 ሰዓት ላይ ቁርስ የመ
ብላት ቀጠሮ ስላላቸው ነው። ሚስታቸው ግን
ቤት አይደለም ያሉት።ህመምተኛ ናቸው። ሆስፒታ
ል ነው ያሉት።

"ባለቤትዎ ሀይለኛ ሴት ናቸው ማለት ነው . . ስለ
ዚህ ነው ላለማርፈድ ይሄን ያህል የቸኮሉት" አልኳ
ቸው።

"አይ . . . እሷ እንኳን ምንም አትለኝም"አሉኝ አረጋ
ዊው ፤ "እኔው ነኝ . . "

"እንዴት . . ." አልኳቸው እንዲጫወቱ ፈልጌ።

"አይ ልጄ ፣ ባለቤቴማ ላለፉት አምስት ዓመታት
አልዛይመር በተባለ የመርሳት በሽታ ተይዛ ባለቤ
ቷ እንደሆንኩ እንኳን አታውቅም" አሉኝ ትክዝ ብለ
ው።

ገረመኝ። አረጋዊው ላለፉት አምስት አመታት አን
ድም ቀን ሳያስተጓጉሉ ሆስፒታል እየሄዱ ከባለቤ
ታቸው ጋር ቁርስ ቆርሰዋል።ባለቤታቸው ግን
እያንዳንዱን ቀን ከተለያየ ሰው ጋር ቁርስ እንደበሉ
ነው የሚያውቁት።

ግማሽ ምዕተ ዓመት በዘለቀው ትዳራቸው . . .
የትዳር አጋራቸው የሆኑትን ባለቤታቸው ፈፅሞ
ረስተዋል። ምስኪኑ አረጋዊ ግን ሁልቀን ሳያረፍዱ
ሆስፒታል እየተገኘ ጨርሶ ከማያስታውሷቸው ባለ
ቤታቸው ጋር ፍቅርን ይቆርሳሉ።


ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
318 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-05 09:18:46 የሺህ ዘመን ቀጠሮ

ደራሲ - - - እሙሼ

ክፍል - - -


"ፍስሃዬ አርፏ" ብላ ልትቀጥል ስትል ንጉሱ አንገቷ
ን ጨምድዶ "ኖ ኖ ኖ!በፍፁም እዳትጨርሽው!ፍሰ
ሃ ይመጣል!"አለ አፍጥጦባት።

ዳንኤል በእግሮቹ ጫፍ ቁጢጥ ብሎ ተቀምጦ
አቀርቅሮ ማልቀስ ጀመረ። ድንጋጤ ከሸነቆራቸው
አይኖቹ የሚንጠባጠበው እንባ አዋራ ላይ እያረፈ
የአፈር ገንፎ የመሰለ የላቆጠ ጭቃ ይሰራል።

"አዎ ፍሰሃዬ ይቺን ቀን እንደናፈቀ አግኝቷችሁ ተቃ
ቅፎ ማልቀስ እንዳለመ ነው ለዘላለሙ ያሸለበው"
አለች ልጅቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች።


ኡሞጃ - ናይሮቢ - ኬንያ - 1998ዓ.ም

ፍሰሃ በጀርባው ከተኛበት ቀና ለማለት እየሞከረ
"እሺ በይኝ ሂጂ . . .እኔ ምንም አልሆንስልሽ። በኔ
ምክንያት ያንቺ ሂወት መበላሸት የለበትም። እባክ
ሽ እሺ በይኝ!" ከሚቆራረጥና ከሚያቃስት ድምፅ
የወጣ ልመና።

"ምናለበት ፀጥ ብለህ ራስህን ብታስታምመው!
አንተ በኔ ቦታ ብትሆን የማታደርገውን ነገር ለምን
እኔ እንዳደርገው ትጠይቀኛለህ !? አንተ ብትሆን
እኔ ታምሜ ትተህኝ ትሄድ ነበር!?"ሆድ ብሷት ማል
ቀስ ጀመረች።

"አንቺ ሴት ነሽ ለኔ ብለሽ እድልሽን ማበላሸት የለ
ብሽም። ይሄን እድል ካሳለፍሽ ሌላ እድል ለማግኘ
ት ብዙ ዓመት መጠበቅ አለብሽ።ለዛ ነው አይ ኦ
ኤም ሄደሽ ምርመራሽን አድርገሽ ሂጂ የምልሽ።"
ተናግሮ ሲጨርስ አቃስቶ በጀርባው ተዘረረ።

"ይሄውልህ ፀጥ ብለህ ተኛ ስልህ እምቢ ብለህ
አመመህ አይደል!?"አለች እያለቀሰች።
ፈገግ ብሎ ሊያያት ሞከረ።

"ብዙ ስታወራና ስትጨነቅ እንደሚያምህ ታውቃለ
ህ ለምን ፀጥ ብለህ አትተኛም።ምናለበት የምልህ
ን ብትሰማኝ" ልመናዋን የኬንያታ ሆስፒታል ነርስ
ሰላምታ አቋረጣት።

"ኔያጅ ገብረ ስላሴ" አለች ነርሷ የልቡን ምት ለመ
ለካት የፍሰሃን እጅ ሳብ እያደረገች።ብዙ ኬንያውያ
ን ሁሉንም ወንድ አበሻ ወይም ገብረ ስላሴ ወይ
ም ቀነኒሳ ብለው ነው የሚጠሩት።ነርሷ የፍሰሃን
እጅ እንደያዘች "በቅርብ ሰሃት የወሰደው ነገር አለ
እንዴ?" አለች ወደ ሰላም እያየች። ሰላም በአሉታ
ራሷን በፍጥነት እየተራመደች ፍሰሃ የተኛበትን መ
ኝታ ክፍል ለቃ ወጣች።

"አየህ አይደል? አየህ!"ሰላም ሳትጮህ በቁጣ
ድምፅ ተናገረች።

ነርሷ ከሁለት ዶክተሮች ጋር ተመልሳ መጣች።ነር ሷ ሰላምንና ከፍሰሃ ጎን የተኛ ኬንያዊ ታማሚ አስ
ታማሚዎች ክፍሉን ለቀው እንዲወጡ ጠየቀች።

ከደቂቃዎች በኃላ ፍሰሃ የተኛበትን አልጋ እያጣደ
ፉ እየገፉ በአጠገቧ ሲያልፉ ሰላም በህልም
ውስጥ ያለች ያህል ፍዝዝ ብላ ነበር የምታየው።

ፍሰሃ እንደምንም ታግሎ አፉን ከፈት አድርጎ . . .
"ሂጄ!" . . የምትል ቃል ተነፈሰ በሰላም አጠገብ
ሲያልፍ።

"ምናለበት አሁን እንኳን ፀጥ ብትል።"አለች ሰላም
ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል የተወሰደ ያለውን ፍሰሃ በዳ
መኑ አይኗ እያየች።

"ከፍሰሃዬ አንደበት የሰማሁት የመጨረሻ ቃል
"ሂጂ!" የሚል ቃል ነበር" አለች እያለቀሰች።

ዳንኤልና ንጉሱ በእውንና በቅዠት መሃል ሆነው
እያለቀሱ ያዳሞጧታል።

"እናም ዘመድና ጓደኛ እንደሌለው ለብቻሽ ቀበርሽ
ው?" ዳንኤል ጠየቀ።

"የት ነው የተቀበረው?"ንጉሱም ጠየቀ።

"እሱ እኮ ነው ከሆዴ አልወጣ ብሎ ሁሌም የሚያ
ስለቅሰኝ" አለች አፍንጫዋን በነጠላዋ እያበሰች።

"ምኑ ነው ከሆድሽ ያልወጣው"ጠየቀ ንጉሱ

"አለመቀበሩ! ፍሰሃ አልተቀበረም"ድንገት ጮሃ
ማልቀስ ጀመረች።

ዳንኤልና ንጉሱ ግራ በመጋባት ተያዩ። ሁለቱም
ተመሳሳይ ነገር እያሰቡ ነበር፤ የልጅትዋ የአእምሮ
ጤንነት አጠራጣሪ ስለመሆኑ።

"ጤነኛ አልመሰልኳቹም አይደል?" አለች በማያቋ
ርጥ ለቅሶዋ መሃል። ዳንኤል በአዎንታ ራሱን ከነቀ
ነቀ በኃላ ነው ያደረገው ነገር ስህተት እንደሆነ
የገባው።

"የፍሰሃዬ አስክሬን በህክምና ወጪ እዳ ተይዞ
አልተቀበረም።እዳው ካልተከፈለ መቅበር አይቻል
ም . . "ንግግሯ ድንገት በገነፈለ ለቅሶ ተቋረጠ።

"ምም እእእእንን?" አከታትለው ተመሳሳይ ጥያቄ
ጠየቁ የሰሙትን ማመን ባልቻለ ድምፅ።

"አዎ የ ፍስሀዬ አስክሬን በእዳ ተይዟል።በአንድ
ሚሊዮን የህክምና ወጪ እዳ ተይዟል"ብላ ማልቀ
ስዋን ቀጠለች። ማልቀሷ የምታቆመው ለፍሰሃ
ጓደኞች ምላሽ ስትሰጥ ብቻ ነው።

"አንድ ሚሊዮን ሽልንግ!?" በዶላር ስንት ማለት
ነው?" ጠየቀ ዳንኤል።

"ወደ አስር ሺ የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ይመስለኛ
ል።" አለች።

"እንዴት አስክሬን በእዳ ተይዞ ሳይቀበር ለሁለት
አመት ይቀመጣል!?" ግራ ገብቶት ጠየቀ ዳንኤል

"የፍሰሃዬ አስክሬን ብቻ አይደለም በእዳ የተያዘው
የፍሰሃዬ አስክሬን ያለበት ቦታ ብቻ የሌሎች የአራ
ት ኢትዮጵያውያን አስክሬን በእዳ ተይዞ ሳይቀበር
ተቀምጧል"አለች እያለቀሰች።

"ነገ ሄጄ የወንድሜን አስክሬን ይዤው እመጣለሁ
!" አለ ዳንኤል ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ።

"ሄደን እናመጣዋለን!"አለ ንጉሱ

ዳንኤልና ንጉሱ ጊዮን ሆቴል ላሊበላ ባር ቁጭ
ብለው ቢራ በእንባው ተያይዘውታል።ሊጎነጩ
ብርጭቆዋቸውን ሲያነሱ የእንባ አንኳር የቢራ
ብርጭቆዋቸው ውስጥ ጠብ ይላል።በጉንጫቸ
ው ላይ የሚፈሰው እንባም አልፎ አልፎ ወደ አፋ
ቸው ይሰርጋል።

ነገ በጠዋት ወደ ናዮሮቢ ይሄዳሉ።በእዳ የተያዘ
የጓደኛቸውን አስክሬን ለማስለቀቅና ለአገሩ አፈር
ለማብቃት።ከስምንት ዓመት በፊት ሶስት ጓደኛሞ
ች ነበሩ!ዛሬ ግን ሁለት ቀርተዋል።ስደት ጓደኛቸ
ውን ብቻ ሳይሆን ደስታቸውንም ነበር. . . .
የነጠቃቸው።

*አለቀ ! ?********

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
365 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-05 09:18:45 የሺህ ዘመን ቀጠሮ

ደራሲ - - - እሙሼ


"ተንስኡ ለፀሎት" ለሚለው የቄሱ የፀሎት ጥሪ
በግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለቅዳሴ የተሰበ
ሰበ ምእመናን "እግዚኦ ተሰሃለነ" በማለት ተስጥኦ
ውን መለሱ።

ሶስት ወጣቶች ቅዳሴውን ከመስማት ውጪ ተስ
ጥኦውን አይመልሱም። ምን አልባትም ቤተ ክርስ
ትያኑ ግቢ ውስጥ ይቁሙ እንጂ ቅዳሴውንም
አይሰሙትም። ሶስቱም ወጣቶች የሚያስቡት
ከደቂቃዎች በኃላ ስለሚጀምሩት የስደት ጉዞ ነው

ቀኑ እለተ ገብርኤል ነው፣ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና
ሁለት አመተ ምህረት። ሶስቱ ወጣቶች የመጨረሻ
ቸውን የስንብት ቃል ለመተንፈስ እጅ ለእጅ ተያይ
ዘው አይኖቻቸውን ወደ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክር
ስተያን ላኩ።

"ሀብታምም እንሁን በድህነትም ችግር ውስጥ
እንሁን ምንም ያህል ርቀት ከሀገራችን ርቀን ቢሆን
ም የምንኖረው መስከረም አንድ ቀን ሁለት ሺህ
አመተ ምህረት ማለዳ አንድ ሰሃት ላይ እዚች ቦታ
የግድ መገናኘት አለብን! ያ ቃላችን ነው!" አለ
ዳንኤል።

"ቃላችን ነው !እግዚያብሔር ይርዳን!ቅዱስ ገብሬ
ል ይከተለን።አሉ ንጉሱና ፍሰሃ
"እግዚአብሔር ሁላችንንም ከምንሰደድበት በሰላ
ም መልሶ እንዲያገናኘን አምላካችንን በፀሎት
እንጠይቀው" አለ ዳንኤል።

"አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ
መንግስትህ ትምጣ . . "በቅዳሴው መሀል ጮክ
ብለው መፀለይ ጀመሩ።ሲፀልዩ እንባቸው ከጉን
ጫቸው ይወርድ ነበር።

ጷግሜ ስድስት ቀን 1999 ዓ.ም

ዳንኤል ጷግሜ ስድስት የሚባል ቀን እረዝሞበት
ደጋግሞ "ምን አይነት የተንዘላዘለ ቀን ነው" ይላል
ሰሃቱን ተመለከተ ከምሽቱ ሁለት ከሃያ ሶስት ደቂ
ቃ ። ለቀጠሮው ስምንት ሰዓት ተኩል ይቀረዋል።
ስምንት ሰዓቱ ስምንት ሺ ዘመን መስሎ ታየው።
ስምንቱን ሰዓት የት ሄዶ እንደሚያሳልፈው ግራ ገ
ብቶታል ። መጠጥ ቤት መሄድ አልፈለገም።በአ
ጠቃላይ መጠጣትም አላሰኘውም። ጠጥቶ
እንቅልፍ ጥሎት የሺህ ዘመን ቀጠሮው እንዲያ
መልጠው አልፈለገም። አልጋው ላይ በጀርባው ጋ
ደም ብሎ መፅሀፍ ለማንበብ ሞከረ ነገር ግን ም
ንም የማንበብ ፍላጎት አልነበረውምና መፅሀፉን
አስቀምጦ በአፍ ጢሙ ተደፍቶ ተኛ።ምክንያቱ
ባልገባው ሁኔታ መላ ሰውነቱ በላብ ረጣጥቧል።

በደመ ነፍስ እጁን ሰዶ ስልክ አንስቶ ሁለት ቢራ
አዘዘ። ቢራው ካዘዘ በኃላ ነው "ምን ማድረጌ ነው
!?" ያለው።ሃሳቡን የመቀየር እንኳን እድል ሳያገኝ
የሂልተን ሆቴል አስተናጋጅ ሁለት ቢራ ይዞለት መ
ጣ። በሂልተን ሆቴል የመስተንግዶ ፍጥነት ተገረ
መ።

"በስንት ሰዓት ነው ከስራ የምትወጣው?"አለው
አስተናጋጁን።

"ጠዋት አንድ ሰዓት" አለ አስተናጋጁ።

"ዋው! ያማ ጥሩ ነገር ነው። ጠዋት አምስት ሰዓት
ኦ ማለቴ ጠዋት አስራ አንድ ሰዓት ላይ ትቀሰቅሰ
ኛለህ ? የማልቀርበት ቀጠሮ ስላለኝ ነው።"

"ምንም ችግር የለውም።ደውለው ሪሴፕሽን መቀ
ስቀስ የሚፈልጉበትን ሰዓት ከነገሩ በሰዓቱ ተደው
ሎ ሊቀሰቀሱ ይችላሉ።" አለ።

"ያ እሱንም አደርጋለሁኝ። ምን አልባት እነሱ ከረ
ሱት አንተ እንድትቀሰቅሰኝ ብዬ ነው"አለ ዳንኤል
አስተናጋጁ በአወንታ እራሱን ነቀነቀ።

ዳንኤል "እንካ ይቺን ያዛት!" ብሎ እጁን ወደ አስ
ተናጋጁ ዘረጋ። አስተናጋጁም በምስጋና ጎንበስ
ብሎ ከተዘረጋው እጅ ላይ ያለውን ነገር ተቀበለ።
አስተናጋጁም የተሰጠውን ነገር ገለጥ አድርጎ
ሲመለከተው የአንድ መቶ የአሜሪካ ዶላር መሆ
ኑን ተረዳ።

ዳንኤል ግንባሩን የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስት
ያን ላይ አስደግፎ እየፀለየ እያለ "ዳኒ!" የሚል
የሚጮህ ድምፅ ከፀሎቱ አናጠበው። ያንን ድም
ፅ ሰምቶ የሚቀጥለው ፀሎት አልነበረውም።የፀ
ሎቱ አንዱ ምክንያት ይህን ድምፅ መስማት ነው
ና።

ንጉሱ ተንደርድሮ መጥቶ ዳንኤል ላይ ተጠመጠ
መበት። አንዳቸው የአንዳቸዎን አካል ጥብቅና
ጭምድድ አድርገው ወደራሳቸው ስበው ለአፍታ
ተቃቅፈው ቆሙ። ቃላት ከአንደበታቸው አልወጣ
ም።እንባ በጉንጫቸው እየወረደ ለአፍታ አይን ለአ
ይን ይተያዩና ደግመው ይተቃቀፋሉ።መተቃቀፋቸ
ውን እንባቸው ያጅበዋል። የአንዳቸው እንባ የአንዳ
ቸውን ገላ ያርሰዋል። ተቃቅፈው ቆመው በሃሳብ
ነጎዱ። በሃሳብ ወደኃላ ስምንት ዓመት ተጉዘው
የተለያዩበትን ጊዜ አስታወሱ።ሌላ የሚያቅፋቸው
እጅ በቶሎ እንዲመጣ ጓጉ። የፍሰሃ እጆች።

ዳንኤል ሰዓቱን መልከት አደረገና "ሃያ ደቂቃ አረ
ፈደ እኮ ምን ሆኖ ይሁን !?" አለ የንጉሱን ፀጉር
እንደማስተካከል ዳበስ እያረገ።።

"ይመጣል!" አለ ንጉሱ በርግጠኝነት።

"ለማንኛውም እንገናኝ የተባባልንበት ቦታ እንሂድ"
አለ ዳንኤል።የተቀጣጠሩበትን የደውል ማማ
ከቆመበት ቦታ ቢያዩትም ቦታው ላይ ለመገኘት
መራመድ ጀመሩ።

"አምሮብሃል ካናዳ ተስማምቶሃል ማለት ነው?"
አለ ንጉሱ ወደ ዳንኤል እያየ።

ዳንኤል መልስ ከመስጠቱ በፊት አንዲት ቆንጆ
ሴት በነጠላ እንደተከናነበች አጠገባቸው መጥታ
ቆማ "ዳኒና ንጉሱ ናቹ አይደል?"አለች በፎቶ ላይ
ካየቻቸው ቢለወጡም እነሱ እደሆኑ ግን እርግጠ
ኛ ነበረች።

"አዎ! አዎ!" አሏት በቅደም ተከተል በወጣ ድምፅ

"እፎይ!"አለች በረጅሙ። የውስጥ እፎይታዋ የፈ
ነቀላቸው የሚመስሉ የእንባ ዘለላዎች ነጠላ ላይ
ተንጠባጠቡ።

"ምንድን ነው?ማነሽ አንቺ? ለምን ታለቅሻለሽ?"
ጠየቀ ንጉሱ።

"ፍሰሃ ነው አይደል ምጠብቁት?"

"አዎ ታውቂዋለሽ!?የት ነው ያለው?"በጥድፊያ
ጠየቀ ዳንኤል።

እንግዳዋ ሴት አይኖችዋን በነጠላዋ ሸፍና ጮሃ
ማልቀስ ጀመረች።"አንተ ነህ ፍሰሃዬ ቃልህን
ያልጠበከው አንተ ነህ ለአገርህ መሬት ያልበቃል
ው!" ማልቀስዋን ቀጠለች።

ንጉሱ አንገቷን ጨምድዶ ያዛት። በድንጋጤ ማልቀ
ስዋን አቁማ ፈጣ ተመለከተችው።
"አንድ ችግር ገጠመው እንዳትዩኝ ! ፍሰሃ ይመጣ
ል!" አለና ጨምድዶ አንቆ እንደያዛት ሲረዳ ይቅር
ታ ብሎ ለቀቃት ።

ዳንኤል እንባው ከጉንጩ እየወረደ።

"ምንድን ነው የሆነው ?ፍሰሃ የት አለ?" አለ ወደ
እንግዳዋ ሴት እያየ።

****ይቀጥላል*******

ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
324 views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-04 17:54:36 እኔ እና እኔ

"ባዶ እግሬን ነኝ። ጥርሴ ከከንናፍሬ እየተገጫጨ ይመለሳል ሰዉነቴ ያለ ፍቃዴ ይንቀጠቀጣል፣ ይሄ ነዉ የማልለዉ ወላፈን ፊቴን ይለበልበኛል ለከሰለዉ ነፍሴ ትንፋሼ ይነድለታል፤
ገርጥጦ ወዜን የቀማኝ ስብራት አመድ አስመስሎኛል።

ዝናብ የለም ፣ፀሀይም የለም፣ ሙቀትም የለም፣ ቅዝቃዜም የለም፣ ለምን የሚለዉ ቃል ግን ሃሳቤ ላይ አለ፤
ለምን?እንዲህ ሆነ? ለምን አልዘነበም? ዘንቦስ ለምን ህመሜን አላጠበም? ለምን ፀሀይ ጠለቀች?በሙቀቷስ የበረደዉን ሆዴን ለምን አታሞቅም? ለምን አልቀዘቀዘም? ቀዝቅዞስ ጥዝጣዜዉ ከድብርቴ አያነቃኝም? ለምን? ለምን? ለምን?.....ጠያቂ እንጂ መላሽ በሌለበት መላጣ አስፋልት እኔ እና እኔ እየተቦቃቀስን ወደ ገደላማ ስፍራ ሄድን፤
ድንገት ቀና አልኩኝ፤ ሰማዩ ደብሮታል፣ ያልነበረችዋ ፀሀይ ጀምበሯን ወጣ አድርጋ በሰማዩ ቁርጭራጭ እየተሸፈነች ጫፏ ብቻ ይታያል።

"ምነዉ ተፈጥሮም አሽሟጠጠችብኝ? አሁን እቺ ፀሀይም በአቅሟ የኔን ነፍስ መምሰሏ ምን ይሉታል? ለነገሩ አራጋቢዉ ካለ አቃጣዩም ሞልቷል" አልኩ የኔ በማይመስል ኑሮ በመረረዉ ሸካራ ድምፅ....."

**************
"ድርግም" አደረኩት አይኔ ያለ ልክ ከቀኝ ወደ ግራ ከላይ ወደ ታች ይጉረጠረጣል፤ በጣም ግራ ገብቶኛል ከዚህ በላይ ማንበብ አልቻልኩም፤
የማነባት(ሲጠብቅም ሲላላ) ደራሲው በሆነ መመርመሪያ መሳሪያ ሙሉ ታሪኬን እየተከታተለ ሳያዛንፍ የፃፈ መሠለኝ፤ የራሴዉ ሀሳብ ለራሴ ገርሞኝ ሆ! አስባለኝ!

ገፀባህርይ ላይ ያለችዉ "ማክዳ" ትርጉሙን ባላዉቀዉም ማ-ክዳ ሆነልኝ፤ ማ?-ክዳ? እንደዚህ ተቀጣች? ይሄ ሁሉ ታመመች? እንዴትስ ማንም ስብራቷን ሊጠግንላት አልዳዳዉም?
ስብራትን፣ ህመምን፣ ስቃይን....ለሰዉ ሲያጋሩት ይቀላል የሚባል ነገር አይገባኝም።(መብቴ ነዉ) ምክንያቴን ልንገርህ?
ስንት ያስጨነቁኝ ህመሞች እሾኾች ነፍሴን ሲወጉት....አቅላይ ተብዬጋ ሲቀርብ ቀልድ መሠለ? ስንቱስ "አይዞን" በሚል አጭር ቃል ተዳፈነ?....ስለዚህ አይቀልም፤ ለሁለተኛ ወገን መንገር ልክ እንደ "ኡፍፍፍ" እንደ ማለት ነዉ። ትንፋሽ እንጂ ብሶት አያወጣም አለቀ!
"Life is resycle" ከሆነ ታመህም ድነህም ተሹመህም ተሽረህም ትኖራለህና ስትታመም....አጋጣሚዉን ጠብቀህ አይንህ "ለነገህም አትል" እስኪልህ አልቅሰህ አፍንጫህ "ምነዉ ስራዬን ባታበዛዉ?" እስኪልህ ተነፋርቀህበት፣ ሰዉነትህ ተንዘፍዝፎ በእንባህ ሲታጠብ ነፍስህን ባያክማት እንኳ ፋታ ይሰጥሃል።

እንባህን ጥርግርግ አድርገኸዉ
"እስቲ ጥርስህን" ተብለህ እንደምታሳየዉ ከንፈርህን ካላቀቅክ በቃ ደስተኛ ነህ አሉ!(ጥልሳም አለች ሚሚ)

አንተም ትላለህ አዎን ደስተኛ ነኝ። ነፍሴ የቤትህ መጋረጃ አይደለምና ገልጠህ አታየዉም። ግን እንድታየዉ የፈቀድኩልህን ጥርሴን ብቻ ስለማሳይህ ደስተኛ ነኝ። ...የነፍሴን ዜማ በራሴዉ መድረክ እያዜምኩ፥ ዝናን (ጥንካሬ) አተርፋለሁ።
በቀሪው ደግሞ "ኢኝኝኝኝኝ"እልሃለሁ



………… ፈትሒያ

ስለ-ፅሁፉ ሃሳብ አስተያየት ካላቹ ፦ @Fethetulletiya
ይጠቀሙ………………


ውብ አሁን

╭══•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀: ══╮
@tsihofoch
@tsihofoch
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ ══╯
290 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ