Get Mystery Box with random crypto!

የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochen — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochen — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የሰርጥ አድራሻ: @yeabatochen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 488
የሰርጥ መግለጫ

💒💒ለምጠፋ መብል ሳይሆን ለዘለዓለም ሕይወት ሊሆን ይገባል 💒💒💒የሐ.፫፥፭
እግዚአብሔር አምላካችን የዘለዓለም ሕይወት በምናገኝበት ጽኑ ክርስትና ራሳችንን የምንመረምርበት ንጹሕ ልቡና በምክረ ካህን በምንኖርበት ትህትና እንዲያጸናን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አስተየት መልዕክት ካለዎት በዚ ቦት ያገኙኝ
👇👇👇👇
@Tadeyedingelbot https://t.me/yeabatoch
👆👆👆👆

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-26 08:08:03 አዲስ የመስቀል መዝሙር
38 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 06:59:20   ርኅወተ ሰማይ 
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች፤ አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም::
❖ የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ::
❖ እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል፤ በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል::
❖ ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ፤ በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል::
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ
  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ‹‹ዘርዐ ያዕቆብ›› ብሎ ስሙን መልአክ ነው ያወጣለት፤ ሲወለድም ብርሃን ቤቱን ሞለቶት ታይቷል፤ ግማደ መስቀሉን ከአባቱ ከዐፄ ዳዊት ተረክቦ በማስመጣት በግሸን አስቀምጦታል፡፡
❖ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የጻድቁን የደብረ ቢዘኑን የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ከጠጣችው በኃላ የእምነቷን ጽናትና ጥልቀት አይተው ጻድቁ ባደረባቸው መንፈስ ቅዱስ ትንቢትን በመናገር "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፤ በትንቢታቸውም መሠረት
ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡
❖ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለሀገራችንም ሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ውለታ ውለዋል፤ ጣዖት አምልኮን ከሃገራችን ለማጥፋት ብዙ ሺህ ካህናትን አሰልጥነው በመላ አገራችን አሰማርተዋል፤ የኑፋቄ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉባኤያትን አዘጋጅተዋል፡፡
❖ ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰው ለአገልግሎት አብቅተዋል፤ ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፤ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡
❖ እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሳ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፤ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ብዙ ሥርዓቶችም በሊቃውንት እንዲሠሩ አድርገው ሌሎች ብዙ በጐ ተግባራትንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡
በረከቱ ረድኤቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን
116 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 06:56:46 የአባቶቼን ርስት አልሰጥም pinned «''በከፍተኛ ቁጣ የተሞላ ሰው ራሱን ይገድላል። ይህ ሰው ለስህተት ተጠያቂ የሆነና ደካማ ጤንነት ያለው ሰው ነው። ጢስ ንቦችን ከቀፎአቸው እንደሚያስወጣቸው ቁጣም እውቀትን ከልብ ያስወጣል።'' ቅዱስ ኤፍሬም»
03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 06:56:10 ''በከፍተኛ ቁጣ የተሞላ ሰው ራሱን ይገድላል። ይህ ሰው ለስህተት ተጠያቂ የሆነና ደካማ ጤንነት ያለው ሰው ነው። ጢስ ንቦችን ከቀፎአቸው እንደሚያስወጣቸው ቁጣም እውቀትን ከልብ ያስወጣል።''
ቅዱስ ኤፍሬም
125 views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 06:56:10 "ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡

እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ወደ_ኦሎምፒያስ)
114 views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:35:41
" " ንግሥተ ሳባ (ማክዳ) " "
(እንኳን ተወለድሽልን)

" ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።"

(የማቴዎስ ወንጌል 12 : 42)

✿ከበረከተ ልደቷ ይክፈለን፡፡✿

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
147 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:19:21 "ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡"

(ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
219 views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:19:21 #ስም_ብቻ_ምን_ሊጠቅመኝ

መጠሪያ ብቻ ከሆነኝ -- እኔ ክርስቲያን መባሌ
በግብሬ ካላሳየሁት -- ካልተዋሐደ ከአካሌ
በጨለማ መቅረዝ ሆናኝ-- እግሬን ከእንቅፋት ካላዳነ
ጌታዬ በኔ ካልከበረ -- ስሙ በኔ ካልገነነ
ሻማ ሆኜ ካላበራሁ -- ጨለማ ለዋጠው ወገኔ
ስሙ ብቻ ምን ሊጠቅመኝ -- ምን ሊሠራልኝ ነው ለኔ?
በአርባ ቀኔ ስጠመቅ -- ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ
በእምነት ዳብሬ እንዳድግ -- መልካም ፍሬን እንዳፈራ
ሥነምግባር መጠመቄን-- እንዲያሳየኝ አጉልቶ
ክርስትናዬን እንዲናገር -- በደረስኩበት ሁሉ ገበቶ
የተቀበልኩት ልጅነት -- በእኔነቴ ዙርያ አብርቶ
ለዚህ ነበረ ምክንያቱ -- የጥምቀት ክርስቲያን መሆኔ
በጸበሉ ነጽቼ -- ልጁ የተባልኩ እኔ
በአነጋገር በሥራዬ -- ክርስትናዬን ካላሳየሁ
ጌታዬ በሰጠኝ መክሊት -- አትርፌበት ካልተገኘሁ
እንደተዘናጋሁ ካለቀ -- ከተጨረሰ ዘመኔ
ክርስቲያን መባሌ ምን ሊረባኝ -- ምን ሊጠቅመኝ ነው ለ'ኔ?
101 views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:35:36 የአባቶቼን ርስት አልሰጥም pinned a photo
07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:34:03
❖ ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ፤ ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው፤ ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን፤ ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸውሠ የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።

ምንጭ
አባ እንጦንስ
109 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ