Get Mystery Box with random crypto!

የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochen — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeabatochen — የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
የሰርጥ አድራሻ: @yeabatochen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 488
የሰርጥ መግለጫ

💒💒ለምጠፋ መብል ሳይሆን ለዘለዓለም ሕይወት ሊሆን ይገባል 💒💒💒የሐ.፫፥፭
እግዚአብሔር አምላካችን የዘለዓለም ሕይወት በምናገኝበት ጽኑ ክርስትና ራሳችንን የምንመረምርበት ንጹሕ ልቡና በምክረ ካህን በምንኖርበት ትህትና እንዲያጸናን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አስተየት መልዕክት ካለዎት በዚ ቦት ያገኙኝ
👇👇👇👇
@Tadeyedingelbot https://t.me/yeabatoch
👆👆👆👆

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 08:36:35 የአባቶቼን ርስት አልሰጥም pinned «(14) የኖኅ መርከብ ፤ የሔኖክ መልካም ስራው ካልን
የመልከ ጼዴቅ _______እንላለን ?»
05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:33:16
(14) የኖኅ መርከብ ፤ የሔኖክ መልካም ስራው ካልን
የመልከ ጼዴቅ _______እንላለን ?
Anonymous Quiz
54%
ሀ) ቡራኬው
15%
ለ) መሠዊያ
23%
ሐ) ርግብ
8%
መ) ድንኳን
13 voters100 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:15:23 በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡

አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ለመዳን፣ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ መስራቱን አቁም፡፡

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
96 views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:11:35 የመጀመሪያው ሰው አዳም ገነት ተሰጥታው ሳለ፥ በአንዲት ትእዛዝ መተላለፍ ምክንያት ከክብሩ ተዋርዶ [በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት] ያን ኹሉ መከራና ሥቃይ ካገኘው፥ መንግሥተ ሰማያትን የተቀበልን፣ ተቀዳሚ ተከታይ ከሌለው አንድ ልጁ ጋር አብረን ወራሾች ከኾንን በኋላ ርግቢቱን ሳይኾን እባቡን ተከትለን የምንኼድ እኛ’ማ ሊደረግልን የሚችል ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ይኾን?

ከእንግዲህ ወዲህ በእኛ ላይ የሚፈረደው ፍርድ እንደከዚህ በፊቱ “አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ” የሚል አይኾንምና (ዘፍ.3፡19)፡፡ “ምድርን ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይሏን አትሰጥህም” የሚል አይደለምና (ዘፍ.4፡12)፡፡ ይህን የመሰለ ሌላ ፍርድም አይደለምና፡፡ ታዲያ ምንድን ነው? በውጭ ወዳለው ጨለማ መጣል! መቼም ቢኾን መች በማይፈታ እስራት መታሰር! በማያንቀላፋ ትል መበላት! ጥርስ ማፋጨት ባለበት ጽኑ ፍርድ መጣል (ማቴ.25፡30)

ይህም እጅግ ምክንያታዊ ነው፡፡ እንዴት ቢሉ አንድ ክርስቲያን ታላቅ የኾነ ጸጋን (ልጅነትን) ተቀብሎ ሳለ በዚያ በተቀበለው ጸጋ መነሻነት [ወይም ለተቀበለው ጸጋ እንደሚገባ] ብልጫ ያለው ሕይወትን የማያሳይ (የማይኖር) ከኾነ፥ የሚያገኘው መከራም የዚያን ያህል ታላቅ ነው፤ የሚቀበለው ቅጣትም እጅግ ጽኑ ነው፡፡

አንድ ጊዜ ኤልያስ ሰማይን ከፍቶ ዘግቶ ነበር፡፡ ያን ያደረገው ግን ዝናብ እንዲዘንብና እንዳይዘንብ ለማድረግ ነበር፡፡ ለአንተ ግን ሰማይ የተከፈተው ዝናብ እንዲዘንብ ወይም እንዳይዘንብ እንድታደርግበት አይደለም፤ ወደዚያ እንድትወጣበት ነው እንጂ፡፡ ወደዚያ እንድትወጣ ብቻም አይደለም፤ ፈቃደኝነቱ ካለህ ሌሎች ሰዎችንም ወደዚያ እንድትመራበትም ጭምር ነው እንጂ፡፡ አየህ! ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ ገንዘቡ ከኾነው በጸጋ ይህን ያህል ድፍረትና ኃይል ነው የሰጠህ!

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
101 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:08:19 _<<የሚጠቅምህን_ብቻ_ተመልከት!!!!!>>_

➾"በአንዲት ገዳም የሚኖሩ የበቁ አባት ነበሩ። አንድ ወጣት ወደሳቸው ይመጣና አባቴ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እፈልጋለሁ ይህን አስቤ የእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሆንኩ ነገርግን በዛም እንዳልቆይ የወንድሞቼ ሀሜት አሉባልታ ከቤቱ እንድርቅ አረገኝ ምን ላድርግ አባቴ?

አባም ሲያዳምጡት ቆዩና አይ ልጄ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ማሰብህ መልካም ነበር ነገርግን እዛው አጠፋክ የሰዎች ሀሜትና አሉባልታ ሊያርቅህ አይገባም ነበር ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የሚጠቅምህ የእነሱን ትችት መመልከት ሳይሆን የእራስህን ኃጢአት መመልከትህ ስለሆነ።በል ተነስ ሂድና የማይጠቅምህን ትተህ የሚጠቅምህን ብቻ ተመልከት ብለው አሰናበቱት።"

➾እኛም ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር እንዳንቀርብ የሚያረገን ይሄ ነው።የሚጠቅመን ትተን የማይጠቅመንን መመልከታችን።የእራሳችንን ኃጢአት ትተን ስለነ እግሌ ማውራታች የእራሳችን ነውር በስራችን አርገን ሌላውን መኮነናችን እግዚአብሔርን ቀረብነው ብለን የምንገፈትረው ጥቂት አይደለንም።

➾አስተውሉ ስንት የአገልግሎት ጊዜ ያትን በማይጠቅም ሀሜትና አሉባልታ አቃጥለናል? ስንት የጸሎት ሰዓትን ስሌላው በማውራት ጨርሰናል? ስንቶቻችንስ የሚጠቅመንን ባለማወቃችን ለቤቱ ቀርበን ለጌታው እርቀናል?

➾ወደእግዚአብሔር እንድንቀርብ የሚያደርገን ሌላውን መኮነናችን ሳይሆን የእራሳችንን ኃጢያትን መመልከታችን ነው። የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ሲያጠይቅ "እኔ መላእክትን ከሚያይ ሰው ይልቅ ኃጢያቱን በሚያይ ሰው እቀናለሁ። ምክንያቱም መላእክቱን ስላየ ብቻ የጸደቀ የለም ኃጢያቱን ስለተመለከተ ግን የጸደቀ አለ።" በማለት ግልጽ ያደርግልናል።

➾የማይጠቅመንን ትተን የሚጠቅመንን እንድንመለከት እግዚአብሔር ይርዳን!!!

መልካም ምሽት ይሁንልን
86 views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:14:19


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችኹ

"ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ።

እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ፡፡"

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ

277 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:14:19
“....እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ....”

".....ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ...."

ማሕሌተ ጽጌ

እንኳን ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም (ኪዳነምህረት) #በዓለ_ትንሣኤ_ወዕርገት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

መልካም በዓል ይሁንልን።
83 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:14:19 https://telegra.ph/የእመቤታችን-የቅድስት-ድንግል-ማርያም-ዕርገት-08-21
85 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:14:19 https://telegra.ph/ድንግልማ-በእውነት-ተነሥታለች-08-22
84 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:12:37 የአባቶቼን ርስት አልሰጥም pinned «የነሐሴ ኪዳነ ምሕረት ሥርዓተ ማኅሌት »
17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ