Get Mystery Box with random crypto!

ኢ🇪🇹 ዞ 🇪🇹ፕ🇪🇹 ሳይኮሎጂ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezobe — ኢ🇪🇹 ዞ 🇪🇹ፕ🇪🇹 ሳይኮሎጂ ኢ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezobe — ኢ🇪🇹 ዞ 🇪🇹ፕ🇪🇹 ሳይኮሎጂ
የሰርጥ አድራሻ: @ezobe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 748
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት
እና ሀሳብ
@Abrsha8
ላይ ያናግሩኝ

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-25 15:22:59 ኦላይ ስራ ለመስራት ምትፈልጉ በሙሉ ሁነኛ ድርጅት አግኝተናል በሊንኩ እየገባቹ ተመዝግባቹ ስሩ
https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r0675862937
519 viewsአብርሃም, 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 11:12:31 Channel name was changed to «ኢ ዞ ፕ ሳይኮሎጂ»
08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 10:37:13 እምነትህ ከተግባርህ ጋር ያነሳሃል!
፨፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨፨
እንደ ማንኛውም ስኬታማና ደስተኛ ሰው በእነዚህ ሁለት እሳቤዎች ተማመን።
አንድም "በመንም ሁኔታ ነገ ከዛሬ የተሻለ ይሆናል፤"
ሁለትም" እኔም እርሱን የማድረግ አቅም አለኝ።"
አዎ! ጀግናዬ..! ማድረግ ትችላለህ!
ማነው እንዳትችል የሚያደርግህ?
ማነው ከፊትህ የሚቆመው?
ማነው እሳቤህን የሚያሳንሰው?
ማነው እምነትህን የሚያውከው?
ማንስ ነው ከእራስህ በላይ ስላንተ አቅም የሚያወራው?
አዎ! ማነው? ምንድነው?
አንድ እውነት አስታውስ! ሁሌም መስቀለኛ መንገድ ላይ ነህ፤ በፈለከው የመጓዝ ምርጫም አለህ። ሁሌም ቢሆን የመምረጡ ነፃነት ያንተና ያንተ ብቻ ነው። ቦሃላ በምርጫህ ምክንያት ለምታጣውና ለሚደርስህ ነገር ማንም ተጠያቂ አይደለም። ሰዎች የሚነግሩህን አለመቻልህን ሙሉ በሙሉ የማመን፣ ተቀብሎም ቁጭ የማለት መብት አለህ። እራስህ የሚሞግትህን መቻልና የማድረግ አቅምም አምነህ፣ ተቀብለህ እርሱ ላይም የመስራት ምርጫ አለህ። የትም ብትሔድ፣ በየትኛውም ሁኔታ ሙሉ ምርጫ አለህ።
የሚጠቅሙህን ፅሁፎችና መፅሀፍት የማንበብና ያለማንበብ ምርጫ፤
አርፍዶ የመነሳትና በሌሊት የመንቃት ምርጫ፤
በመንፈሳዊነት የመመላለስና በአለም ባህር የመዋጥ፣ የመስጠም ምርጫ፤
ህልምህን መኖርና የሌሎችን ህልም የማሯሯጥ ምርጫ።
አዎ! ጥሩ መራጭ እራሱ ላይ የሆነ ነገር የሚጨምርለትን፣ ወደ ብቁነት የሚወስደውን፣ የስኬታማ ሰዎች ምርጫ ይመርጣል። ምርጫውን ከሃሳብ ከፍ ያደርገዋል። በእምነትና ተግባር ይደግፈዋል።
አዎ! ጀግናዬ..! እምነትህ ከተግባርህ ጋር ያነሳሃል፤ ያሻግርሃል። የሃሳብህ ልዩነት ፈጣሪነት ተግባርህ ላይ በጉልህ ይታያል። ከምንም ብትጀምር መዳረሻህ ከፍ ካለ የማትደርስበት ምክንያት የለም። የተደጋገም ስኬታማ የአዕምሮ ምግብ ያስፈልግሃል። እለት እለት መድረስ የምትፈልገውን ቦታ በምናብህ ተመልከት፤ እዛም እንደደረስክ እራስህን አሳምን፤ ህልምህን የምትኖረው የከፍታውን፣ የእድገቱን ሂደት በማጣጣም ነው። እራስን መመዘን (Self evaluation) ዘወትር ያስፈልግሃል፤ ከትናንተ ዛሬ የተሻልክ መሆንህን ማወቅ፣ ሂደቱን ማስቀጠል የስኬትህ ቁልፍ ነው።
አዎ! ሁሌም ቢሆን ማንንም የማያስወቅስ፣ እርሱን በመምረጥህ ብቻ የምትደሰትበት፣ ሂደቱ የሚያረካህ፣ ስሜትህን የሚያረጋጋ ምርጫ ምረጥ፤ ተጠቃሚነትህን አስቀድም።
ብሩህ ጣፋጭ ቀን ይሁንልን!
@ezobe
3.6K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 11:29:10 ሌላ አስደሳች ቀን!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ደግሞ ሌላ አስደሳች፣ ግሩም ቀን፣
ተወዳጅ፣ ተሸላሚ፣ ተስፋን ፈንጣቂ ውብ ቀን፣ ዛሬ፤
ለዛሬ ቸር አምላክ ይመስገን!
ቀናችንን በፍካት እንጀምራለን፤
በደስታ እንቀበላለን፤
እኛን መርጣ መጥታችና፤
አዲስ ሌላ ነገር ልትጨምርልን፣ አዲስ እስትንፋስ ልታስጎነጨን ተከስታለችና።
አዎ! ጀግናዬ..! ሌላ አስደሳች፣ በተስፋ የተሞላች፣ የአበበች፣ የፈካች ቀን።
ተመስገን!
ምን ልዩ ያደርጋታል?
ምንስ የተሻለች ያደርጋታል?
ቀድሞ ታይታ አታውቅም፤ ድጋሜም አትከሰትም፤ ዛሬ ዛሬ ብቻ ነች፤ ለእርሷ የሚሰማን ስሜትም ተሰምቶን አያውቅም ዛሬ ብቻ ተሰማን፣ ድጋሜም አይሰማንም።
በዚህ ሒደት ስንት ቀናት አለፉ? እጅግ ብዙ፣ አያሌ ቀናት አለፉ፣ ትዝታቸውን ይዘው፣ ስሜታቸውን ሸሽገው።
አዎ! ዛሬ ታልፋለች፤ ባዶዋን፣ ያለ ትርፍ እንድታልፍ ግን አታድርጋት ከልብህ አጣጥማት፤ ወደ ውስጥህ አስገባት፤ ዛሬ እንደኖርክ፣ ዛሬ እንደተደሰትክ Feel አድርገው፤ ከልብህ ይሰማህ። ዛሬ የድንቆች ሁሉ ድንቅ ስጦታ ነች፤ ይህቺን ድንቅ ስጦታ ከድንቅ አመምላክ በቀር ሌላ ማንም ሊሰጠን አይችልም። እኛን መርጦ ሰጠን፤ ለዛሬ አበቃን። በመስጠቱ አይዘንብን፣ አይከፋብን፣ አይፀፀትብን በምትኩ በደስታችን ይደሰት፣ በስራችን ይኩራ፣ በስኬታችን ሌላ ብዙ አስደሳች ቀናት ያክልልን፣ ይጨምርልን።
አዎ! ዛሬን ከተደሰትክ፣ ዛሬን ካጣጣምክ ነገን ታያታለህ፣ በተስፋ ጠዓሟ ይሰማሃል።
ዛሬን ካረከስክ፣ የአምላክህን ስጦታ ካሳነስክ ለነገህ ምንም ዋስትና የለህም። ስንተ በተሰጠው፣ በሚጨመርለት ሌላ አዲስ ቀን በምስጋና የሚሰክር ሰው እያለ ላንተ ለአማራሪው፣ ለነቃፊው፣ ለተቺው ማን ሌላ ቀን የሚጨምርልህ ይመስልሃል? ማንም!
መቼም ዛሬን ሳትኖር፣ ዛሬን እያማረርክ ለነገ ተስፋ አይኖርህም፣ ምናልባትም ከፊትህ ያለው ነግ በይበልጥ የምታማርርበት፣ የምትበሳጭበት የተሻለ ምክንያት ይዞልህ ይመጣ ይሆናል። ያኔም ምሬትህን ትቀጥላለህን?
አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ፣ ከትናንትም ከነገም የተሻለች እንደሆነች አስበህ ተደሰት፣ ደስ ይበልህ። ሌላ ምክንያት አትፈልግ የዛሬን እስትንፋ ስለተነፈስክ፣ ንጋቷን ስላየህ፣ የጠራውን ሰማይ መመልከት ስለቻልክ፣ በጤና ስለ ነቃህ ብቻ ደስ ሊልህ ይገባል። በደስታህ ምክንያት ካንተ በላይ ስኬታማ ሰው ኬትም አይገኝም።
አስደሳች ውብ ቀን ማሳለፍ ጀምረሃል፤
ቀንህን በምስጋና አሃዱ ብለሃል፤
ንፁውን አየር ማጣጠሙን ተክነህበታል፤
እንግዲህ ከዚህ በላይ ደስታ፣ ከዚህ በላይ እርካታ ከወዴትስ ይመጣል።
ተመስገን!
ለዛሬ ውብ ቀን!

@ezobe
3.3K views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 15:38:31 እምነትህ አይነስ፣ ምስጋና አይለይህ!
፨፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨
የምታጣው ከሌለህ የምታገኘው ላይ አተኩር፤
የሚቀርብህ ከሌለ የሚጨመርልህን ተመልከት፤
ሳትጠቀም ከምታጣው ተጠቅመህ የሚቀርብህ ይሻላል፤
አዎ! የማያልቅ የሚመስል ንብረት ይኖርህ ይሆናል፣ የማይሸረፍ ባለበት የሚቀጥል ጊዜ ያለህ ይመስልህ ይሆናል፣ አብረውህ ያሉ ሰዎች እስከ መጨረሻው አብረውህ የሚቆዩ ሊመስልህ ይችላል፤ ጤናና ጥንካሬህም ባለበት የሚቀጥል ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን እንዳሉህ ማመንህ አንድ ነገር ሆኖ ኋላ ስታጣቸው እንዳይቆጭህ ዛሬ ላይ ሆነህ አመስግንባቸው፣ ተጠቀምባቸው፣ ያንተ መሆናቸውን አሳይ፣ በእነርሱ በኩል ብዙ እንዳገኘህ መስክር።
አዎ! ከሌሉ የሉም! ዛሬ የተጨመረልህ ውብና ሙሉ ቀን ሁሌም ላይኖር ይችላል፣ የምታጣበት ጊዜ መኖሩ ግድ ነው። ዛሬን ባየህ ቁጥር የሚቀሩህ ነገዎች እያነሱ ይሔዳሉ፣ ያንተም አቅም ይቀንሳል፣ ተፈጥሮ ስራዋን ትሰራለች፣ ለምንም ነገር እንደዛ ያባከንከውን ጊዜ ስትፈልግ ታጣዋለህ፣ አመስግነህለት የማታውቀው ውዱ ጤናህ ሌት ከቀን አምላክህን እንድትማፀን ሊያደርግህ ይችላል።
አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም ሲኖር ያምራል፤
ምስጋናውም ከልብ ሲሆን ደስ ይላል፤
ልመናው ከአንጀት ሲሆን ምላሽ ያገኛል፤
ዛሬ የተቸገርክ ሊመስልህ ይችላል፣
ዛሬ አስከፊ ቀን ሊመስልህ ይችላል፣
ዛሬ ሰቆቃ እንደበዛ፣ ረሃብ እንደበረታ፣ ምድር እንደተጎዳች ሊሰማህ ይችላል፣
ነገር ግን በዚህ እንዲበቃ አምላክን ካልተማፀንክ፣ ባለው ነገር ካላመሰገንክ ከዚህም የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል አስታውስ።
አዎ! ፈጣሪ መቼም ፍጥረቱን ጥሎ አያውቅም፤ ለከፋው አውሬም አሳልፎ አይሰጥም ነገር ግን በግማሽ ልብ እያማረርክ በሌላው የአምላክህን ማዳን ብትጠባበቅ አውሬዎች መሃል እራስህን ታገኘዋለህ። ያኔ ትልቁ እምነትህ ይፈተናል እንደሚያድንህ ካላመንክ የአውሬዎች መዓድ ትሆናለህ፣ ቀረጣጥፈው ከመንገድ ያስቀሩሃል፣ ክብርህን ሳታይ ከአለም ይለዩሃል። በድንቅ አድራጊው አምላክ ካመንክ፣ ስላለህበትም ምስጋና ካልተለየህ ግን ከአውሬው መንጋጋ ፈልቅቆ ያወጣሃል፣ ጉዳትህን፣ ስብራትህን ሽሮ ከሰው ፊት ያቆምሃል፣ ባለህ ስለተደሰትክ ሌላ ይጨምርልሃል፣ በእርሱም ስላመንክ የእምነትህን ፍሬ ይመግብሃል።
አዎ! የሚያሳጣህ ነገር ከሌለ ስላለህ ከልብህ አመስግን፤
የሚቀንስብህ ከሌለ በተደረገልህ ዘሬን የማየት፣ በህይወት የመኖር ተዓምር ደስ ይበልህ፤
ብታጣ እንኳን ማጣትህን በበጎ ቁጠረው፤
ቢጎድልብህ እንኳን መጉደሉን በመልካም ተመልከተው። ዋናው ነገር ትናንት ኖሮህ ዛሬ ማጣትህ ሳይሆን፣ ዛሬን ብታጣ ነገም ማግኘት መቻልህ ነው። እምነት ነገሮችን ይቀይራል፣ መንገዱን ያሳምራል፤ ምስጋናም ያለውን ይባርካል ሌላም ይጨምራልና ሁሌም እምነትህ አይነስ፣ ምስጋና አይለይህ።
ብሩህ ቀን ይሁንልን

@ezobe
1.8K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 16:00:34 እያንዳንዱ ቀን የተለየ አንተን ይፈልጋል!
፨፨፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨፨፨
ውስጣዊ ጥማት፣ የልብ ምኞት፣ ጥልቅ የስኬት ረሃብ በፍፁም አያስተኛህም።
በየእለቱ መጠጥ አምጣ ይልሃል፤
በእየቀኑ ወደ ምኞትህ ቅረብ ይልሃል፤
እለት እለት ህልምህን እንድትኖር ይታገልሃል፤
ጥምሙ እንድትቆርጥለት በየአቅጣጫው የሚጠጣ ፍለጋ ያማትራል።
አዎ! ጀግናዬ..! አንድን ነገር መፈለግህ ካልቀረ ከልብህ፣ ከውስጥህ ፈልገው፤ በእርግጥም እንደሚገባህ እመን፤ ስለሚገባህም የማገባህን፣ የሚጠበቅብህን ታደርጋለህ። በግዴለሽነት የምትተወው፣ ከሆነ ይሁን ካልሆን ችግር የለውም የምትለው አይደለም፤ አዎ! በደምብ ችግር አለው ለዛው ዘላቂና መሰረታዊ ችግር፤ ህይወትህን የሚቀይር ነገር፣ ፍላጎትህን የሚያሟላ ነገር ትተህ እንዴት ችግር ላይኖረው ይችላል። ችግርማ አለው፤ ህልምህን ሳይኖሩ ማለፍን የሚበልጥ ችግር የለም፤
የእራስን ደስታ ሳያጠጥሙ መሔድን የመሰለ ችግር ኬት ይመጣል።
አዎ! ጀግናዬ..! ፍላጎትህን ችላ አትበለው፤
ህልምህን አትናቀው፤ ዋጋ ስጠው፤
ስሜትህን አትግደል፤ አዳምጠው፤
አምሮትህን አትግፋው፤ ለማሳካት ታገል፤
ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ነውና የምትፈልገውን ነገር ከልብህ ፈልገው።
የትም እየው የት ቀልብህን ከገዛ፣ እንደሚቀይርህ ካመንክ በፍፁም ጭራውን አትልቀቅ፣ ወደኋላ አትበል ተከተለው ለእርሱም ብለህ በእየቀኑ እራስህ ላይ ዋጋ እየጨመርክ ተጓዝ፤
አለምን ወደራስህ አቅርብ።
አዎ! በተለየ ፍላጎት ስትሞላ እያንዳንዱ ቀን የተለየ አንተን ይፈልጋል፤ ከትናንት የተሻለ፣ መንፈሱ የጠነከረ፣ ስሜቱ የማይረበሽ፣ ስኬትን በይበልጥ የተራበ፣ ለፍላጎቱ ሲል የሚታገል፣ እንቅልፍ የማይተኛ፣ አርቆ የሚያስብ፣ ዛሬን የሚኖር ነገን የሚያልም። ስለዚህ የቀናቶችህን ፍላጎት አማላ፤ እለት እለት የተሻልክ ሆነህ ቅረብ።

@ezobe
2.3K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 09:37:41 .....
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል።
.
አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡
.
ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡
.
የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡
.
ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡
.
“ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau
.
“የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts
.
“ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ”
.....

@ezobe
3.1K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 18:24:51 #ከድንጋይ_ፈላጩ_ተማር

በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው። አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ለመንገስ ትዕግስት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው።

ከውጤታማዎቹ የኤን ቢ ኤ ቡድኖች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ሳን አንቶኒዮ ስፐርስ ከማህበራዊ ቀራፂው ከጃኮብ ሪስ ወስዶ በተጨዋቾቹ ሎከር ላይ የሰቀለው አንድ ጥቅስ አለ፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤ ሁሉ ነገር ምንም ለውጥ የማያመጣ በሚመስለኝ ጊዜ ሄጄ የማየው አንድ ድንጋይ ፈላጭ አለ፡፡ ይህ ፈላጭ ድንጋዩን በድንጋይ መፍለጫው መቶ ጊዜ ይመታዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ድካም ውስጥ ግን ምንም የመሰንጠቅ ምልክት ድንጋዩ ላይ አይታይም፡፡ በመቶ አንደኛው ምት ግን ድንጋዩ ለሁለት ይሰነጠቃል፡፡ እኔ ግን ድንጋዩን የሰነጠቀችው 101ኛዋ ምት ብቻዋን ሳትሆን መቶ አንዱም ምቶች በአጠቃላይ ተደማምረው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡”



@ezobe
2.4K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 14:42:34 አስተሳሰብን መቆጣጠር

አስተሳሰብን መቆጣጠር ማለት ወደ እኔ የሚመጣውን ወይም በውስጤ የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ወፍጮ” በመሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡

ጤና ቢስ አመለካከቶችን ለማስወጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. በሕይወትህ የምታሰላስላቸውን ሃሳቦች ለይተህ እወቅ፡፡

ለማንነትህና ለሕይወትህ አላማ የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህንን ለይተህ ስታውቅ በሃሳቦች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብህ ጥርት ባለ መልኩ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡

2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አታስተናግዳቸው፡፡

የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሮህ ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለጤናማ አመለካከትህና ላስቀመጥከው የሕይወት ከፍታና ደረጃ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ ተቃወመው፡፡ ይህንንም ልምምድ የዘወትር አድረገው፡፡

3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማ አስተሳሰብ ቀይር፡፡

ከዚህ በፊት በውስጥህ ያስተናገድካቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር አለብህ፡፡ ከአእምሮህ ክፉውን ሃሳብ አስወጥተህ በጤናማው ካልተካኸው ሌላ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም፡፡
@ezobe
2.9K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ