Get Mystery Box with random crypto!

ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewaleshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል?

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-12-29 21:18:28 #ብዛት_ሳይሆን_ጥራት!

ከብዙ ጓደኞች ይልቅ አንድ የልብ የሆነ ወዳጅ ልብን ይሞላል ህይወትን ያቀናል ! ያለ አግባብ ከሚጠፉ ብዙ ምሽቶች እና ከባከኑ ብዙ ቀናት በአግባቡ የተጠቀምንበት አንድ ቀን መንገዳችንን ለማቅናት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ! የነገሮችን መጠን በጥቅማቸው በሚሰጡን ዋጋ እንጂ በብዛታቸው ልንለካቸው አይገባም !

ብዛት ሊያጠፋ ይችላል ጥራት ግን ያለመልማል !

መልካም አዳር ተመኘው።
@manyazewaleshetu
581 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 10:25:52 በፅናት ቁም !

ያመንክበትን ትልቅ እና መልካም ነገር ለማሳካት ስትታገል ብዙ ነቀፌታ ይደርስህ ይሆናል ብዙም ግዜ ልትወድቅ ትችላለህ እንቅፉት ሊበዛ ልትደክም ትችላለህ ነገር ግን ፅናት ካለህ ታግሰህ ከታገልህ እመነኝ በስተመጨረሻ ድል ያለችው በእጅህ ናት !

መልካም ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
307 viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 21:12:49 ደስ ይበልህ!

እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት። ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! በፈተና ደስ ይበልህ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
611 viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 13:04:05 ማንም የማይነግርህ ብዙ አለህ !

ማንም ሰው ከማንነትህ አውርዶ ዝቅ እንዲያደርግህ እና ያለህን የተሰጠህን በረከት ሁሉ እንደሌለህ እንደጎደለህ እንዲሰማህ እንዲያደርግህ አትፍቀድለት ፈጣሪ ብዙ ድንቅ ስጦታዎችን ሰጥቶህ ሳለ ምንም እንደሌለህ የሚያሰሙህን ሰዎች አትስማ !

የተባረከ ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
1.2K viewsedited  10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 21:23:30 ወሳኝ ፀሎት!

ፈጣሪ ሆይ 'መቀየር የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል እርዳኝ፤ መቀየር የምችላቸውን እንድቀይር ድፍረቱን ስጠኝ ከሁሉ በፊት ግን ሁለቱን መለየት እንድችል ማስተዋሉን ስጠኝ።' እርካታ የሞላው ህይወት ለመኖር ወሳኝ ፀሎት ነው።

የሚያረካ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
208 viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 20:40:48 ገንዘብን ተጠቀሙበት በራሱ መልካም ነው። ነገር ግን ፍቅርን ከገንዘብ ለማግኘት አትሞክሩ። ምክንያቱም ፍቅር የውስጣችሁ ነው። የውስጠኛው ህልውና ነው እግዚአብሔርንም ከገንዘብ ዘንድ አትፈልጉት። እርሱ ከአለማት ሁሉ በላይ የላቀና ያለፈ ነው። እያንዳንዱ ነገር በእናንተ የህልም መጠን ሳይሆን በገዛ ራሱ አቅም ተጠቀሙበት። በዚህም ጊዜ ጤናማ ሰው ናችሁ። ጤናማ መሆን ደግሞ ቅዱስ መሆን ነው።
*
@manyazewaleshetu
748 viewsedited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 20:32:38 ራስህን መጉዳት አቁም!

ፀሀይ ስትጨልም ስራ አቁማ አይደለም፤ ሌላኛውን የመሬት ክፍል ልታበራ ዞር ብላ ነው። እናቱ ገበያ የሄደችበት ልጅ እናቱ ከሞተችበት ልጅ እኩል ያለቅሳል፤ ግን እኮ መመለሷ አይቀርም።

ህይወትን በቀጥታ እየተረጎምክ ራስህን መጉዳት አቁም! የተወሳሰቡና ግራ ያጋቡህን ነገሮች ተረጋግተህ በተለየ መንገድ ለማሰብ ብትሞክር ብዙ እንቆቅልሽ ትፈታለህ። ኑሮ፣ ስራ፣ የፍቅር ግንኙነት የፈተና ድንጋይ ሲወረውሩብህ አንተ ሰብስበና ተዓምረኛ ቤት ስራበት!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
870 viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 09:48:03 ግዜህን ጠብቀው !

እያንዳንዷን ደቂቃ እና ሰዓትህን በአግባቡ ተጠቀምባት ፣ ካለፈ በኋላ ወይኔ ለምን ማለቱ አያዋጣም ምክንያቱም ልንመልሰው አንችልም ስለዚህ ከዛሬዋ ቀን ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ራስህን በደንብ ንገረው ያለ አግባብ የሚባክን ግዜ የለም !

የተባረከ ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
1.3K viewsedited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 12:50:22 አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-

"የእርጅና ወራት ሳይመጣ በጉብዝና ወራት ፈጣሪህን አስብ!" የተባልከው እውነት ነው::
-
በፍቅር አምላክህን ካላሰብከው በህመም ታስበዋለህ::
-
ነፃ በሆንክ ሰዓት ያልጠራኸውን በእስር ስትወድቅ ተጠራለህ::
-
በጤና ያፈለከውን ስትታመም ትፈልጋለህ::በሰላም ያላዋራኸን አዳጋ ሲያጋጥምህ ታዋራለህ::
-
ሰዓቱ ደርሷል::አሁንም የመዳንህን እድል አታባክነው::በምድር ቅዠት ተኝተህ የአምላክህን መንግስት አትለፈው::
-
ምድር እንደሆነች ከጊዚያዊ እርካታ ውጪ የምትሰጥህ አንዳች የላትም::የሰጠችህንም ነገር አንድ በአንድ ቆጥራ ስትሞት ትቀበልሃለች::
-
ማንም ሰው ሊነጥቅህ የማይቻለውን መንፈስህን ብቻ ፈልገው::ነፃ የምትወጣው በእርሱ ነው::
-
አምላክህን ብትውደው ጊዜ እና ትኩረትህን በሰጠኸው ነበር::ድምፁን ለመስማት እና የአብሮነት ጊዜን ለማሳለፍ በተመኘህ ነበረ::
-
ነገሩ የማያውቁት አገር አይናፍቅም ሆኖል::በአለም አስትዳደግ አምላክህን እንድትረሳ ተደርጏል::ጠረኑ: ደግንቱ: ውበቱ: እርዳታው እና ቸርነቱ ጠፍቶሃል::አለም አታልሎህ ውስዶሃል::
-
እርሱ ግን ይወድሃል እና መቼም አይተውህም::ብትጠላው አይጠላህም::ህጉን ብታፈርስም አያፈርስህም::
-
ጠባዩ ሙሉ ፍቅር ነውና እስከ መጨረሻው ያፈቅርሃል::በፍቅር ካልሰማኸው በህመም ቢሆን እንድትቀርበው ይስብሃል::
-
አደጋ ላይ የጣለህ ስለማይወድህ ሳይሆን ልብህን እንድትሰጠው ፈልጎ ነው::በፍቅር እምቢ ስትለው በመከራ ከሰማኸኝ ብሎ ነው::
-
እስቲ ደስስስ ይበለው ስማው::ልብህን ወደ እርሱ መልስ::የቀድመ የአባት እና የልጅ ፍቅራችሁን አድስ::እስቲ አንተ በትራህ አምላክህን ደስስስስ አሰኘው::ልቡን አብራላት::የፍቅር: የይቅርታ እና የሰላም ሰው ሁንለት::
-
መልካም_ዕለተ-ሰንበት
-
አርባምንጭ አብራችሁን
ለመሄድ በ0987209020 ይደውሉ!
1.9K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 12:50:21
1.6K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ