Get Mystery Box with random crypto!

ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewaleshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል?

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-12-25 12:49:51 እስክታጣ አትጠብቅ !

የመኖርህ ደህና የመሆንህ ጥቅም የሚገባህ ስትታመም ነው ! የተሰጠህ እድል ከምንም በላይ ትልቅ እንደሆነ የምታውቀው ለማጣት ስታጣጥር ነው !

በፊት ታማርርባቸው የነበሩ ነገሮች በሙሉ የሚያማርሩ እንዳልነበሩ የምታውቀው በጠና ስትያዝ ነው !

ነገር ግን ዋጋ ለማግኘት እና ባለህ ለማመስገን የግዴታ ማጣትህንና መቸገርህን ለምን ትጠብቃለህ ቆም ብለህ እስኪ ራስህን አስበው አሁን ያለህን ነገር በሙሉ ብታጣ ምን የሚፈጠር ይመስልኋል?

መልካም ሰንበት ተመኘን
@manyazewaleshetu
1.6K viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 20:25:16 የራስ መንገድ!

ሁልጊዜም የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም፤ መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ።

አየህ በህይወት ውስጥም የሚገጥሙህን ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች፣ አስቸጋሪ የሰው ፀባዮችን ሁሉ መቆጣጠር አትችልም፤ ያንተን ህይወት ግን እንዲወስኑት አለመፍቀድ ያንተ ምርጫ ነው ምክንያቱም የመርከብህ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
707 viewsedited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 11:48:19 መብራቱን አብራው!

አንድ ጊዜ በጎንደር ከተማ አንድን ስልጠና ለመስጠት በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተ የግል ልምምዴን ላካፍላችሁ፡፡ ያረፍኩበት ሆቴል ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ ስለነበረና አካባቢው በዛፎች በመከበቡ ምክንያት የራሱ ውበት ስላለው በዚያ ማረፍን እመርጣለሁ፡፡ በዚያ ባደርኩበት አንድ ሌሊት ግን አንድ ነገር ተከሰተ፡፡

ሌሊት ነቅቼ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ስላስፈለገኝ ከአልጋዬ ለመውጣት ተንቀሳቀስኩኝ፡፡ ከውጪ በመስኮት በኩል በመጋረጃው ሾልኮ የሚገባው ደብዛዛ ብርሃን ለእንቅስቃሴዬ በቂ ስለነበር ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ወደ መታጠቢያ ቤቱ በሚወስደው አቅጣጫ አንድ “እባብ” ተጋድሞ አየሁኝ፡፡ ከብርሃኑ ደካማነት የተነሳ ይህንን “እባብ” ቅርጹን እንጂ መልኩንና ሁኔታውን መለየት አልቻልኩም፡፡ በጣም ደነገጥኩ፣ በጣምም ፈራሁ፡፡

ወደኋላዬ በመሰብሰብ ሁለንተናዬን ትራሴ ላይ አገኘሁት፡፡ ብዙ አሰብኩኝ፡፡ ብዙ አወጣሁኝ፣ አወረድኩኝ፡፡ ትንሽ ጊዜ ካቃጠልኩኝ በኋላ፣ በመጨረሻ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ እንደምንም የእባቡን ክልል አለፌ መብራቱን ማብራት ነው፡፡ ትንሽ ከወላወልኩኝ በኋላ የፈጣሪዬን ስም እየጠራሁ፣ ጨለማውን ለማሸነፍ አይኖቼን አፍጥጬ፣ ጥግ ጥጉን ተራምጄ መብራቱን ልክ ሳበራው ለካ ያየሁት “እባብ” ማታ በድካም ስሜት ወደ አልጋ ስቸኩል የጣልኩት ቀበቶዬ ነበር፡፡

በዚህ ገጠመኜ የገባኝ ነገር ይህ ቀበቶ እባብ መስሎኝ በነበረበት ሰዓት፣ ልክ እውነተኛ እባብን ብጋፈጥ የሚሰማኝን የፍርሃት ስሜት ነው የሰጠኝ፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ልጮህ እችል ነበር፣ እዚያው አልጋዬ ላይ ሆኜ እስከሚነጋ አፍጥጬ ልጠብቅ እችል ነበር፣ ሰዎች ጋር ስልክ በመደወል ልበጠብጥ እችል ነበር . . .፡፡ በፍርሃት ተወጥሮና ታስሮ የነበረውን ማንነቴን ነጻ ያወጣው እውነቱን ለማወቅ መብራቱን ማብራቴ ነው፡፡

ለካ እይታ የእውነታን ያህል ጉልበት አለው፡፡ በሕይወታችን አንድ ነገር ባይኖርም እንኳን፣ እንዳለ ከቆጠርነውና ከፈራን ማንነታችንን አስሮ ሊያስቀምጠን እንደሚችል በሚገባ የተገነዘብኩት ያን ጊዜ ነው፡፡ መድሃኒቱ መብራቱን ማብራት ነበር፡፡

አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና ሆኖብኛል . . . ሳይሆንብኝ አይቀርም . . . አለብኝ . . . ሳይኖብኝ አይቀርም . . . ሊሆን ነው . . . መሆኑ አይቀርም ከሚሉት ምክንያት-የለሽ ፍርሃት የተነሳ ታስረው አመታት ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ፍርሃት፣ እምቅ ብቃታቸውን አፍኖ፣ ነጻነታቸውን ነፍጎ፣ የሌለውን ችግር እንዳለ አድርጎ፣ ያለውን ችግር ደግሞ እጅግ አግዝፎ በማሳየት ከሰው በታች ያደርጋቸዋል፡፡

መፍትሄው መብራቱን ማብራት ነው!!! መብራቱን ማብራት ማለት እውነታውን ለመጋፈጥ አይንን መግለጥ፣ ስለሁኔታችን ከበሰለ ሰው ጋር መወያየት፣ ምንም ነገር ቢሆን በፍርሃት ታስሮ ከመኖር እውነታውን ተጋፍጦ በነጻነት መኖር እንደሚመረጥ መገንዘብ ማለት ነው፡፡ አይህንን አትርሳ፣ መፍራት እስከምታቆም ድረስ መኖር አትጀምርም!

የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@manyazewaleshetu
568 viewsedited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 21:57:06
𝐈𝐭’𝐬 𝐨𝐤𝐚𝐲

ይህች ምስሉ ላይ የምታዪት ወጣት 𝐉𝐚𝐧𝐞 𝐌 ('#𝐍𝐢𝐠𝐡𝐭𝐛𝐢𝐫𝐝𝐞' ) ትባላለች በቅርቡ በተደረገው 𝐀𝐦𝐞𝐫𝐢𝐜𝐚'𝐬 𝐆𝐨𝐭 𝐓𝐚𝐥𝐞𝐧𝐭 ተሳትፋ ከሳይመን 𝐆𝐨𝐥𝐝𝐞𝐧 𝐁𝐮𝐳𝐳𝐞𝐫 ተበርክቶላታል።
𝐈𝐭𝐬 𝐨𝐤𝐚𝐲 በሚል ርዕስ ግለ ታሪኳን ታቀነቅናለች...

በፈገግታ የታጀበችው እንስት ከርቀት ስትታይ ምንም ችግር ያላያት ወይም የማታውቅ ትመስላለች .....ታምናላችሁ ከዚህ ፈገግታ ጀርባ  የሳንባ ፣ የአከርካሪ እንዲሁም የጉበት ካንሰር ተጠቂ ናት የመኖር እድልሽ ሁለት በ መቶ ነው ተብላ  ...𝐈𝐭'𝐬 𝐨𝐤 እያለች ታቀነቅናለች "#ምንም ማለት አይደለም" እንደማለት ነው።

ሁለት ፐርሰንት ዜሮ ማለት አይደለም ተስፋ አለኝ ትላለች።  ብዙ አነቃቂ ንግግሮችን ሰምታችሁ .. አይታችሁ አልያም አንብባችሁ.. ..ይሆናል የተኖረ ማነቃቂያና ጥንካሬ ከዚህ በላይ አለ ብዬ አላስብም ....እስኪ ቆም ብለን እናስተውል እኛ በስንት ነገሮቻችን ፈጣሪን አማረናል ..? እድል ፊቶን አዞረችብን ብለን ተስፋ ቆርጠናል..? መልሱ እናንተውጋ ይቆይ

እኔ በሷ ውስጥ ሶስት ነገሮች ጎልተው ታዩኝ

#ተስፋ ...በምንም አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆን ተስፍ ካለህ ነገን ታያለህ።

#ትልቁ ውበት ደግሞ... ከውስጥ የመነጨ እውነተኛ ፈገግታ እንደሆነና #ጥንካሬን አየሁ።

በግርድፉ ወደ እኛ ስናመጣው "#ደስተኛ ለመሆን ህይወት ፈተና አልባ እስክትሆን መጠበቅ አይገባንም  በችግሮቻችን መሀልም ሆነን ደስተኛ መሆን ይቻላል" ትላለች!

ተስፋ አለመቁረጥ ማለት መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል እውነታውን መጋፈጥ.... መቀየር የምንችለው ላይ አቅማችንን ማዋል ስንችል ነው። ብዬ አሰብኩ።

𝐇𝐚𝐧𝐚 𝐅𝐚𝐧𝐭𝐮

@manyazewaleshetu
736 viewsedited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 11:40:41 #የተሰበረ_እጅ/ልብ

አንድ ነገር አውቃለው የተሰበረ እጅ ሊሠራ ይችላል፤ የተሰበረ ልብ ግን ከቶ አይችልም ተነሽ እራስሽን አበርቺ የሰበረሽን ሰብረሽ እራስሽን አበርትተሽ እና ልብሽን አጠንክረሽ ጠግነሽ ወደስራ ግቢ።

ደካማ ነኝ አልችልም በቃ አበቃልኝ ማለትሽን እና የስንፍና ንግግርሽን አቁሚ አላበቃም ገና ነው አላለቀም አንተም እንደዛው።

መልካም ቀን ተመኘው።
@manyazewaleshetu።
848 viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 22:01:32 ጉዞ ወደ ለውጥ!

ድግስ ላይ ከቡፌው የምትፈልገውን የምግብ ዓይነት ሁሉ አንስተህ ስትጨርስ ምግቡን ፊት ለፊትህ አስቀምጠው አይንህ እንዲያየውና አፍንጫህ እንዲያሸተው ብቻ ቢደረግ አያበሳጭም?

በህይወትም ብዙ የሚጠቅሙ ነገሮች አንብበህ፣ ሰምተህ፣ በአይምሮህ ሰብስበህ ግን ተግባር ላይ ካላዋልከው አሪፍ ምግብ ሳይበሉ ዝምብሎ ከማሽተት በምንም አይለይም። ወዳጄ ከምትፈልገው ያስቀረህ አለማወቅ አይደለም፤ ያወከውን አለማድረግህ ነው። ዳይ ወደ ተግባር!

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
391 viewsedited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 20:48:39 ምርጫ !

ሁለት አማራጮች ፊትህ ቁጭ ተደርገው የቱን መወሰን እንዳለብህ ግራ የሚገባህ ግዜ አለ አይደል የቱን ልስራ ምን ልማር ማንን ላግባ መቼስ ይሁን የትኛውን ትምህርት ላጥና ...... ብዙ ከከባድ እስከ ቀላል የሆኑ ምርጫዎች ይቀርቡልሀል እናም አንድ ነገር ብቻ ልምከርህ ራስህን ብዙ አታስጨንቅ ፀልይ ፈጣሪህን ጠይቅ ከዛም በደንብ ትኩረት አድርገህ አስተውል ጥቅሙንም ጉዳቱንም ዝርዝር አድርገህ እይ ከዛ ቶሎ ወስን የሚመጣው ነገር ካለው በላይ አያስፈራህ !

መልካም ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
702 viewsedited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 21:52:03 መቸኮል አቁም!

ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! ሁሉም ነገር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ፤ በተለይ ደግሞ አትጓጓ! ለህይወት ጣዕም እንድታጣ ያደረገህ መጓጓት ነው።

ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ በቅርቡ መውጣቷ አይቀርም!

የተስፋ ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
569 viewsedited  18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 12:10:49 #በእጅ_ያለ_ወርቅ!

አንቺ ያስጠላሽ ህይወት ለሌሎች ህልማቸው ነው።
እህቴ ንቂ በእጅ ያለ ወርቅ እንደመዳብ አይሁንብሽ አመስግኚ አንተም ብትሆን ንቃ እንጂ።

መልካም ቀን ተመኘው።
@manyazewaleshetu
1.3K viewsedited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 12:10:34
እናንተ አእምሮ ውስጥ ያለውን
በእኔ አፍ እንዳወራው ከፈለጋችሁ
I’m sorry

እኔ የማውራው እውነቱን ነው! እውነት ደግሞ ይጎዳል! I’m sorry ግን ደግሞ ውሎ አድሮ ይጠቅማል!!
1.3K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ