Get Mystery Box with random crypto!

ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewaleshetu — ማንያዘዋል እሸቱ (Manyazewal Eshetu)
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewaleshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.10K
የሰርጥ መግለጫ

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል?

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-12-07 16:37:28 #ለመቅበር_ነው

ልብ በይ ሰብሮ የሄደ ለመቅበር ነው ሚመለሰው።

አትሸወጂ ደጋግመሽ በቂ እድል ሰተሺው ነበር ግን እሱ ምን አረገ ደጋግሞ ልብሽን ሰበረው ደጋግሞ ህይወትሽን አበላሸው አንቺ አንቺን የማትመስይ ፍፁም ሌላ ሰው ሴት አደረገሽ!!

አሁን እድል ለእሱ ሣይሆን ለራስሽ ስጪ አንቺ አንቺን ምታፈቅሪበት ጊዜ እና ስዓት ነው።

የተባረከ ቀን ተመኘን
@manyazewaleshetu
280 viewsedited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 18:58:11 #እኔ_እችላለሁ

ለራስህ እንዲህ ብለህ ንገረው አይምሮህ መሬት ነው የዘራህበትን ነው የሚያበቅለው።
1. እኔ ልዩ ነኝ! እኔ ድንቅ ነኝ!
2. እኔ እችላለሁ!
3. በጎ አሳቢ አይምሮ አለኝ!
4. የጀመርኩትን የህይወትና ጉዞ በድል እጨርሳለሁ!
5. ስኬታማም፤ ደስተኛም፤ መንፈሳዊም ነኝ!

ይሄን ለራስህ መንገር ወይ ድምፅ አውጥተህ ማንበብ ብቻ ስሜትህን ይቀይረዋል፤ ቀንህን ስለ ድክመትህ፣ ስለ ጭንቀትህ፣ ስለ ችግርህ በማሰብ አትጀምር! ምክንያቱም ጭንቀትና ችገር ከዘራህ ጭንቀትና ችግር ነው ምታጭደው፤ አይምሮህ ውስጥ አሪፍ ነገር ዝራ ወዳጄ!

መልካም አዳር ተመኘው
@manyazewaleshetu
1.0K viewsedited  15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 12:13:22 #አስታውሱ

አንድ ቀን ወደሁዋላ ዞራችሁ ስትመለከቱ ምንያህል በማይረቡ ነገሮች ላይ አብዝታችሁ ስትጨነቁ አንደነበር ታስተዉላላችው።

አትጨነቁ አልላችውም ግን ሁልግዜ ይህን አስታውሱ እናንተ ካላችሁበት ምንም ሁኔታ,ነገር እና ፈተና ትበልጣላችሁ ምክንያቱም ብቻችሁን አይደላችሁ ፈጣሪ አብሯችሁ አለ።

መልካም ቀን
@manyazewaleshetu
807 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 12:13:17
መሸነፍ ምንም አይጠይቅም!
826 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 18:27:10 #ወደ_ፈጠረህ_ቅረብ¡

ሁል ጊዜ ወደ ፈጠረህ ወደ አምላክህ ቅረብ ምክንያቱም ሰዎች የሚፈልጉህ የተሻልክ ስትሆን ነው ፈጣሪ ግን የሚፈልግህ የተሻልክ ሊያደርግህ ነው።

መልካም አዳር ተመኘውላቹ
@manyazewaleshetu።
1.6K viewsedited  15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:24:29 አበቃልኝ አትበል !

በዚህ ደስ የሚል የሚያምር ጠዋት ነቅተሀል ፤ ማታ ስትተኛ ዛሬ እንደምትነቃ ማረጋገጫ አልነበረህም ነገር ግን ተስፋ ነበረህ ነገ ይሄን አደርጋለው ብለህ ያቀድኸው ነገር ነበር ! እናም ነቅተህ የማድረግ እድል ገጥሞሀል ስለዚህ ዛሬ ያነቃህ ዛሬ እድል የሰጠህ ፈጣሪ አብሮህ ነበር አሁንም አብሮህ አለ ከዚህም በኋላ አብሮህ ነው እስካለህ ድረስ እስከጠየቅኸው ድረስ እስከለፋህ ድረስ መቼም አይተውክም !

የተባረከ ሰኞ ተመኘን
@manyazewaleshetu
546 viewsedited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 21:33:56 ተስፋ መቁረጥ የለም!

ወዳጄ ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው።

ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ 'አንተ ስትጨርስ እሱ ይጀምራል!' ተስፋ መቁረጥ የለም ወዳጄ!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@manyazewaleshetu!
653 viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 13:27:33 ጥሩ ጎናቸውን አሳያቸው !

ሰዎችን ከልብህ ማቅረብ ከፈለግህ ብዙ ወቀሳ አታብዛባቸው ! ሁሉም ሰው የራሱ ጥያቄ አለው ራሱን በብዙ መንገድ ይወቅሳል ስለዚህ የሚያበረታው የሚደግፈው ይፈልጋል እንጂ በቁስሉ ላይ ይባስ የሚጨምርለት አይሻም !

መልካም ሰንበት ተመኘን
@manyazewaleshetu
1.3K viewsedited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 09:39:08

ሰው ህልም ነው አሉ - ታይቶ ማይጨበጥ
ኪዳኑን አፍርሶ - በሌላ ሚለውጥ

ሰው አፈር ነው አሉ - ታጥቦ የማይጠራ
እድፍ የሞላበት - ከጭቃ የተሰራ
*
ሰው ሸክላ ነው አሉ - ድንገት ተሰባሪ
ወድቆ ለመነሳት - ምን ይሉኝን ፈሪ
*
ሰው ቅጠል ነው አሉ - ጠውላጊ ደራቂ
የሱን እልፍኝ ዘግቶ - የሰውን አድማቂ
*
ሰው ዝንብ ነው አሉ - ከክፉም ከደጉ ከሁሉ አራፊ
መዘዝን ሰብሳቢ - በሽታን ጠላፊ
*
ሰው እሳት ነው አሉ -ለብልቦ ሚያቃጥል
በ አይን ተጋርፎ - በግልምጫ ሚጥል
*
ሰው ጊንጥ ነው አሉ - መርዛም ተናዳፊ
በምላሱ ልሶ - የሰውን ስም አጥፊ
*
ሰው ጅብ ነው አሉ - ሆዳም እራስ ወዳድ
አንዴ ካስቀመጡ - አላየንም ሲወርድ
*
ግና ሰው ብርቱ ነው አሉ - ስለ ሁሉ ታጋሽ
ተቀማጩ አይሰማው - ለ አምላኩ ግን አልቃሽ
418 views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 21:44:11
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሰይፍ ፋንታሁን አምለሰት ሙጩ ሰራዊት ፍቅሬ ደረጄ ሃይሌ ይፈለጋል ፊልም ተለቁዋል ከስር ሊንኩን ነክተው ይመልከቱ
https://t.me/Adey_Abol_Duka21
https://t.me/Adey_Abol_Duka21
707 views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ