Get Mystery Box with random crypto!

📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የሰርጥ አድራሻ: @leywo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

ማንበብ የስብዕና ልህቀትን ያጎናፅፋል!!
ማንበብ ምክንያታዊ እና የሰላ አእምሮን ያንፃል!!
በዚህ ቻናል
👉የስነ ልቦና ምክሮች
👉ግጥሞችና ወጎች
👉ሳይንስና ፍልስፍና
👉ከመፅሐፍ የተቀነጨቡ አስገራሚ ፅሁፎች እና ታሪኮች ይቀርባሉ።
ወዳጆዎን የዚህ የንባብ ማዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በመጋበዝ ቻናሉን ይደግፋ።
ማንኛውም አስተያየት @FiyametaGelay ላይ ይላኩልን
Creator -kalkidan

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:13:42
ሀገር ሴት ናት በወንድነት ወኔ የጠነከረች በሴትነት ብልሀት ከፍ ያለች ፀንታ የምትኖር #ኢትዮጵያ ትቅደም
ብዙ ቢባልም ሁሉም የአዳም ፍጥረት እርስ በእርሱ በፍቅር ይኑር !
ፀሎትና ክብር ከእኛ አይለይ!

ሀሴት በአምላክ
74 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:17:59 ሰላም ሰላም ውድ የመጽሀፍት አለም ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያችሁን እኛ እንደተለመደው ወደ እናንተ የሚያደርሱንን መንገዶች በመጥረግ እና በማሰናዳት የበለጠ ለመቅረብ ስንሰራ ቆይተናል እነሆ አሁን ጊዜው ደርሶ በቅርቡ በድምጽ የተቀረጹ ግጥሞችን ውድድር ለማካሄድ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ፍላጎት እና አቅሙ ያላችሁ በሙሉ ትመዘገቡ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ለመመዝገብ ነጻና የግጥም ባለቤት መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ አላማችን መማማር እና ያላችሁን አቅም ለብዙሀን ተደራሽ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርም ስለሚኖረን በተሻለ ስራ መቅረብ የተሻለ እድል ያስገኛል:: ማበረታቻ የሚሆን ሽልማት ለአሸናፊዎች የምንሸልም ይሆናል::

አሸናፊው የሚለየው በአድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው ሲሆን ውድ የመጸሀፍት አለም ተከታታዮቻችንም በዚህ ድምጽ መስጠት ላይ እንድትሳተፉ በትህትና እንጠይቃለን በእኛ በኩል ምንም አይነት የድምጽ አሰጣጥ አይኖርም::

የግጥሙ ይዘት:- ከፓለቲካ እና ሃይማኖት ጉዳዮች ውጪ!!!

''አስተማሪ አነቃቂ እና መልካም ሀሳቦችን የያዙ/ የሰነቁ ጽሁፎች ይበረታታሉ''

ርዝማኔ :- 2-4 ደቂቃ

ለመመዝገብ :- @BooksWorlddd_bot ''ግጥም 1'' እያላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ?

የምዝገባ ቀናት :- ከሰኞ 23 - ረቡዕ 25 ድረስ !

አቀራረብ:- በድምጽ በመቅረጽ

ሽልማት

1. 1GB internet pkg
2. 500MB internet pkg
3. 250 internet pkg

#ሼር @Books_worldd #ሼር @Books_worldd

ለአስተያየት እና ምዝገባ @BooksWorlddd_bot !

መወያያ ግሩፕ @books_worlddd

ስፖንሰር

@SUPER_SPORTETH
@SoccerManiaET
@StatsZone_ET
113 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:48:37
I love positive energy

@leywo
44 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:43:25 የአና ማስታወሻ
The diary of young girl
ሐሙስ መስከ-26/1943 gc

ውድ ኪቲ
የ<ሚስጥራዊ መደበቂያ> ነዋሪዎች የእርስ በርስ ግንኙነት ከእለት ወደ እለት እየሻከረና እየቆረፈደ መሄዱን ቀጥሏል።በምግብ ጠረቤዛው ዙሪያ ስንገናኝ እንኳን ደፍሮ አፉን የሚከፍት የለም-(የያዝነውን ምግብ ለመጉረስ ካልሆነ በቀር ) ምክንያቱም ምንም ነገር ከአፍሽ ወጣ ማለት ወይ አንድ ሰው ታስቀምጫለሽ ወይ ደግሞ ጨርሶ ባላሰብሽው መንገድ ይተረጎምብሻል።
ለጭንቀትና ለድብርት ፍቱን ማስታገሻ ነው የሚባልለትን ቫሌሪያን ኪኒን በየቀኑ መቃም ከጀመርኩ ጥቂት ቀናት አለፉኝ።እንደው ቢቸግር እንጂ ምንም ጥቅም የለውም ።የዛሬውን በመጠኑ ያስታግስልኝ እንጂ ነገ የባሰ ጭንቀት ውስጥ ከመግባት አያድንም። አንድ ጥሩ ሳቅ መሳቅ የምችልበት ዕድል ባገኝኮ ከአስር ቫሌሪያን ኪኒኖች የበለጠ ይረዳኝ እንደነበር አውቃለሁ ።ግን ምን ዋጋ አለው ኪቲ -ሁላችንም ሳቅ ረስተናል ማለት ይቻላል።
ያንቺው አና
።።።።።።።።።፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨።።።።።።።።።።።።
አና ፍፁም ተስፈኛ ታዳጊ ነች፤ናዚ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ፍፁም ለጆሮ የሚያሰቅቅ ግፍ በሚፈፅሙበት ወቅት የሰው ልጅ መልካም እንደሆነ አና ታምን ነበር።
እንዲህም ብላ ነበር
"የሆነው ሁሉ ሆኖ አሁንም ቢሆን ሰዎች ከስር መሰረታቸው ጥሩ ናቸው ብዬ አምናለሁ።"
አና በሰዎች እምነት ነበራት ግን እንዴት?
ጥበበኛ ናት ጥበብ ደግሞ ያፋቅራል...
የአናን ድንቅ እይታ በሌላ ጊዜ ላስቃኛችው እሞክራለው ፤ለመግቢያ ያክል እነሆ...


@leywo
51 views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:26:03 ሥቃዬ ጊዜያዊ መሆኑን ንገረኝ
ነገ እፎይ እንደምል እባክህ አብሥረኝ
ይህም ያልፋል በለኝ በራሱ እልም ይላል
እንደነፋስ በንኖ እንደፀሀይ ይጠልቃል»
በልና ንገረኝ ይመጣል እፎይታ
ሁሉን የሚያስረሳ የሰላም ሸለብታ
ደጋግመህ ንገረኝ ልቤ ስትል ላንተው
ይህም ያልፋል በለኝ እንደ ትናንትናው
ጥሎኝ እንደ ጠፋው ነቅሎ ሰቀቀኑን እንዳረጀው ውጋት እንዳፈጀው ሐዘን
ሰማይ እንደሚደምቅ በኮከቦች ፍካት
ሌት ቀን እንደሚሆን በተፈጥሮ ዑደት ፥ ነፋስ ያነጠፉት ሣር ቀና እንደምትል
ብሶት ይሁን ቁጣ በለኝ ይህም ያልፋል

ግሬስ ኖልክሮዌል


@leywo
103 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:22:22 .ለመታረቅ የመጀመሪያ ሁን

ብዙዎቻችን በአንድ ወቅት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ወይም በደረሰብን በደል ምክንያት ለረጅም ጊዜ እናቄማለን። የምታረቀው ያስቀየመን ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል እራሱ መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀን ብቻ ነው ብለን ድርቅ እንላለን።

አንዴ ጤንነቷ ጥሩ ያልሆነ የማውቃት ሴት ከወንድ ልጇ ጋር ለሰባት አመታት እንደማይነጋገሩ ነገረችኝ። " ለምን ?" ብዬ ጠየኳት። ከልጇ ጋር በሚስቱ ምክንያት አለመግባባት እንደነበረና እሱ ካልደወለ ላለመደወል እንደወሰነች ነገረችኝ። አንቺ የመጀመሪያው ብትሆኚስ ?" ብዬ ጠቆም ሳደርጋት " አይሆንም " እሱ ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት !" አለችኝ። እሷ ከምትደውል ሣታገኘው ብትሞትም ምንም እንደማይመስላት ነገረችኝ። ከተወሰነ የማበረታቻ ንግግር በኋላ ሀሣቧን ለውጣ እሷ የመጀመሪያዋ ለመሆን ተስማማች። ስትደውልለት ልጁ በመደወሏ በጣም እንደተደሰተ ነገረችኝ። ቀጥሎም ለጥፋቱ ይቅርታ ጠየቃት። ይቅርታውን ስላልጠበቀች እጅግ ተገረመች።

በአብዛኛው አንዱ ደፍሮ የመጀመሪያውን እርምጃ ሲራመድ ሌለኛውም የበለጠ ይቀርብና ሁሉም አሸናፊ ይሆናል። ቂም ይዘን ስንቆይ በአእምሯችን ውስጥ ቀላሉን ነገር ወደ ከባድ እና ውስብስብ እንለውጠዋለን። አቋማችን ከደስታችን በላይ አስፈላጊ ይመስለናል። አይደለም !

ሰላማዊ ሰው መሆን የምትፈልግ ከሆነ ትክክል መሆን ደስተኛ ከመሆን እንደማይበልጥ እየተረዳህ ትመጣለህ። ደስተኛ ለመሆን ያለፈውን መርሣትና ለመታረቅ የመጀመሪያ መሆን ትልቅ ሚና አለው። አንተ የመጀመሪያው መሆንህ ስህተት መሆንህን አያሳይም። ነገር ግን ሁኔታዎችን ወደ መልካም ይለውጣል።

ያለፈውን ስትተው ሰላምህ ፣ ለመታረቅ የመጀመሪያው ስትሆን ደግሞ ሰዎችም ለስለስ ብለው ይቀርቡሃል። እንዲያውም የበለጠ ሊቀርቡህና ስትፈልጋቸው የበለጠ ሊደርሱልህ ይችላሉ። ግን በሆነ ምክንያት እንደዚያ ባያደርጉም ችግር የለውም። ቢያንስ ቢያንስ የድርሻህን ስለተወጣህ ውስጣዊ እርካታ ይሰማሃል። በእርግጠኝነት ደግሞ ራስህን ሰላማዊ ሁነህ ታገኘዋለህ።

ከ፦ ቀላሉን ነገር አታካብድ መጽሐፍ
የተቀነጨበ

ሊነበብ ሚገባ ምርጥ መፅሐፍ


@leywo
104 viewsedited  19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:08:53 ግንዛቤ ወርቃማ ቁልፍ

አንድ ሰው በግንዛቤ ውስጥ ከሆነ አይስገበገብም:ሊቀናም አይችልም ግንዛቤ ወርቃማ ቁልፍ ነው::

ከቁጣ ነፃ መውጣት ገፅ/87

@leywo
89 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:29:26 ጥያቄ """"""""""""""" ለሰላም መዘመር እምነቴ ነው ላለኝ ለዛ ባለ ጦማር ጥያቄ ነበረኝ። የተናገርከው ቃል ፅንፍ እውነት ካለበት ብዕር ይጣላል ወይ ጠመንጃ ለማንገት ብላችሁ በሉልኝ። ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) @leywo
117 viewsedited  13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:21:45 ቀን 2
በሆነ ግዜ በሆነ ሰዓት ገዳም ተገኝቻለዉ ቤተክርስቲያንዋ ዙርያሁን በዛፎች ተከባለች ጭር ያለ ዝምታ ጊዜዉን ተረክብዎል ሁሉም ሚጓዘዉ በእርጋታ እና የሚግባቡት በጥሞና ነዉ የሆነ ሚጨንቅ ስሜት አለዉ እኔ ጥሎብኝ ዝምታ ሲሆን ይጨንቀኛል ምክንያቱም ከጭንቅላቴ ጋር መጋፈጥ ያስፈራኛል ሆ
የመጣዉበትን ቀን ሁሉ ቁጭ ብዬ መራገም ጀመርኩ አብሶ ስልኬ ናፍቆኛል ብዙ ብዙ ነገር አሁን በአጠገቤ የሚያልፉት ገዳመዉያን ማስበዉን ቢያቁ ኖሮ ምን ያህል ከንቱ መሆኔንበየትኛዉም መስፈርያ ለክተዉ ይጨርሱይሆን
እህተ ገብርዬል እህተ ገብርዬል መንገድ ላይ
ከኔ ዉጭ ማንም የለም ማንን ነዉ ብዬ ጋር ገባኝ ምነዉ ልጄ ወዴት ኤድሽ እረገይ በስማም መንፈሳዊ ስሜን ሁሉ ረስቻለዉ አምላኬ በዉስጤ አማተብኩ።

ቀን 5
እንዴት ነዉ ልጄ ለመድሽዉ ይመስገን
እማሆይ እየለመድኩት ነዉ በጣም የሚገርመኝ እፍኝ የማትሞላ ባቄላ ለነብሳቸዉ ማቆያ አፋቸዉ ላይ ያረጉና ሙሉ ቀን ቀጥ ብለዉ ከነ ወዛቸዉ ቅዳሴቸዉን ፀሎታቸዉን ሳያዛብ ያደርሳሉ። ወዛቸዉ ፊታቸዉ ላይ
ያለዉ እርጋታ በጣም ያስቀናኛል እኔ ከነሱ ይበልጥ እየበላዉ እየተኛዉ ይርበኛል ይደክመኛል ከእንቅልፌ ሁሉ እማሆይ ናቸዉ ለፀሎት የሚያነሱኝ ብቻ ወደ ፈጣሪ
መቅረብ ስጋዊ ሕይወት ትቶ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ መታደል መፅናት መመረጥ ነዉ እኛ አለማዊ ሰዎሆች በቀን .ሶስቴ ሆዳችንን እየሞላን እራሳችንን እየተንከባከብን የነሱን ጫፍ አንደርስም ያሁ አመዳም ነን ከንሱ ጋር መቀመጥ በራሱ ሰላም አለሁ አለማዊ ሰዎች ስንባል በጭንቅላታችን ሰዎችን እያማን በአፋችን የሚንቀረጥፍ ሰዉ በላዎች ነን።

ቀን 8
እዉነት እማሆይ ግን እናንተ ምትኖርት ሕይወት በጣም ከባድ ነዉ ይቅርታ ያድርጉልኝ እና
መጀመርያ ደግፍየዉ ነበር ግን ደግሞ ብዬ ዝም ስል እማሆይ ፈገግ ብለዉ እያዩኝ ነዉ በዉስጤ ስንት ነገር እያሰብኩ ስንት ቀን በርግግያለዉ አምላኬ ይቅር በለኝ
በዛ መንገድ አስቤዉ አይደለም ብይ ይቅርታን እሻለዉ ለንሳዓ የወሰድኩት ፆም ፀሎት ስያደክመኝ ምነዉ በቀረብኝ በየትኛዉ አጥያቴ ነዉ ብዬ እራሴን እንደ ፃዲቅ ለመቁጠር ያምረኛል ሰዉ አልገደልኩ ብዬ አጥያትን ከአጥያት ለማመዛዘን ሞክራለዉ አምላክ
ዘንድ ትልቅ ትንሽ ብሎ ነገር የለዉም ደግሞ ሰዉ አልገደልኩ ብዬ እራሴን መካቤም ከገደለዉ እኩል ያስቆጥረኛል።
ቀን 10
አንድ ቀን ጥዎት ከፀሎት መልስ አባን ቁጭ ብለዉ አያዋቸዉ እና እሳቸዉ ጋር ደርሼ መስቀል ተሳልሜ አጠገባቸዉ ቁጭ ብዬ በዉስጤ ብዙ ነገር እያሰብኩ ነበርም የሆነ ፀፀት ባዶ መሆን እየተሰማኝ ነበር ከዛ አባም አይ ልጄ እንደዛ አይሰማሽ ሲሉኝ በረገኩ ዉስጤን ማወቃቸዉ አስደነገጠኝ ጭምር ሁሉም ሰዉ ፈጣሪ በአሰበዉ መንገድ ነዉ ሚጓዘዉ በትናት መፀፀትም መሐዘን ዛሬን አይቀይረዉም ዋናዉ ሳይረፍድ ወደ አምላክ መመለሱ ነዉ ደግሞ ልጅ ልምከርሽ ሁሌም ነገ ላይ ሆነሽ ማታፍሪበቲን ነገር ዛሬ
ላይ አድርጊ ሴት ነሽ ብዙ ነገር ይጠብቅሻል ፈጣራ ይባርክሻል የአብራክሽን ልጅ ስታገኚ ለልጆችስ ምን አይነት ሰዉ እንደነበርሽ ለመናገር ትናትህሽን ከጥቁር አሻራ ማንፃት አለብሽ ምክንያቱም ትናትህ ምን አይነት ሰዉ ነበርኩ ልትያቸዉ።


ይቀጥላል


ከመንገደኘዋ ማስታወሽ የተቀነጨበ…


@leywo
119 viewsedited  13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:31:12 የዛሮቼ ንግስት

ጠማማው ዕድሏ ገጣሚ ላይ ጥሏት
ምጥ ቢያታግላትም
ካዋላጇ ጀርባ ጣሯን በስንኞች ከማሳመር ውጪ
አይዞሽ አላልኳትም፡፡
ያኔ ሰድባኛለች...
በስቃይዋ መሀል ግጥም ለመሰደር
ቃላቶችን ሳምጥ ተጠይፋኛለች፡፡
ዳሩ ምን ያደርጋል
ከርሞ እንደማዘኗ ዘመን ሳያርመኝ
ዛሬም በንዴቷ ቁስል ያለበት ስንኝ መፃፌ ገረመኝ፡፡
የጥበብ ዛሮቼን እያራገፍኩባት
እሷን ቢከፋትም
እንደ ሴትነቷ ፡ እንደ እናትነቷ
ፅፌ አልጨረስኳትም፡፡
ጌታነህ ደጉ
@leywo
113 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ