Get Mystery Box with random crypto!

የአና ማስታወሻ The diary of young girl ሐሙስ መስከ-26/1943 gc ውድ ኪቲ የ | 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

የአና ማስታወሻ
The diary of young girl
ሐሙስ መስከ-26/1943 gc

ውድ ኪቲ
የ<ሚስጥራዊ መደበቂያ> ነዋሪዎች የእርስ በርስ ግንኙነት ከእለት ወደ እለት እየሻከረና እየቆረፈደ መሄዱን ቀጥሏል።በምግብ ጠረቤዛው ዙሪያ ስንገናኝ እንኳን ደፍሮ አፉን የሚከፍት የለም-(የያዝነውን ምግብ ለመጉረስ ካልሆነ በቀር ) ምክንያቱም ምንም ነገር ከአፍሽ ወጣ ማለት ወይ አንድ ሰው ታስቀምጫለሽ ወይ ደግሞ ጨርሶ ባላሰብሽው መንገድ ይተረጎምብሻል።
ለጭንቀትና ለድብርት ፍቱን ማስታገሻ ነው የሚባልለትን ቫሌሪያን ኪኒን በየቀኑ መቃም ከጀመርኩ ጥቂት ቀናት አለፉኝ።እንደው ቢቸግር እንጂ ምንም ጥቅም የለውም ።የዛሬውን በመጠኑ ያስታግስልኝ እንጂ ነገ የባሰ ጭንቀት ውስጥ ከመግባት አያድንም። አንድ ጥሩ ሳቅ መሳቅ የምችልበት ዕድል ባገኝኮ ከአስር ቫሌሪያን ኪኒኖች የበለጠ ይረዳኝ እንደነበር አውቃለሁ ።ግን ምን ዋጋ አለው ኪቲ -ሁላችንም ሳቅ ረስተናል ማለት ይቻላል።
ያንቺው አና
።።።።።።።።።፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨።።።።።።።።።።።።
አና ፍፁም ተስፈኛ ታዳጊ ነች፤ናዚ ከሰውነት ተራ ወጥቶ ፍፁም ለጆሮ የሚያሰቅቅ ግፍ በሚፈፅሙበት ወቅት የሰው ልጅ መልካም እንደሆነ አና ታምን ነበር።
እንዲህም ብላ ነበር
"የሆነው ሁሉ ሆኖ አሁንም ቢሆን ሰዎች ከስር መሰረታቸው ጥሩ ናቸው ብዬ አምናለሁ።"
አና በሰዎች እምነት ነበራት ግን እንዴት?
ጥበበኛ ናት ጥበብ ደግሞ ያፋቅራል...
የአናን ድንቅ እይታ በሌላ ጊዜ ላስቃኛችው እሞክራለው ፤ለመግቢያ ያክል እነሆ...


@leywo