Get Mystery Box with random crypto!

ሥቃዬ ጊዜያዊ መሆኑን ንገረኝ ነገ እፎይ እንደምል እባክህ አብሥረኝ ይህም ያልፋል በለኝ በራሱ | 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

ሥቃዬ ጊዜያዊ መሆኑን ንገረኝ
ነገ እፎይ እንደምል እባክህ አብሥረኝ
ይህም ያልፋል በለኝ በራሱ እልም ይላል
እንደነፋስ በንኖ እንደፀሀይ ይጠልቃል»
በልና ንገረኝ ይመጣል እፎይታ
ሁሉን የሚያስረሳ የሰላም ሸለብታ
ደጋግመህ ንገረኝ ልቤ ስትል ላንተው
ይህም ያልፋል በለኝ እንደ ትናንትናው
ጥሎኝ እንደ ጠፋው ነቅሎ ሰቀቀኑን እንዳረጀው ውጋት እንዳፈጀው ሐዘን
ሰማይ እንደሚደምቅ በኮከቦች ፍካት
ሌት ቀን እንደሚሆን በተፈጥሮ ዑደት ፥ ነፋስ ያነጠፉት ሣር ቀና እንደምትል
ብሶት ይሁን ቁጣ በለኝ ይህም ያልፋል

ግሬስ ኖልክሮዌል


@leywo