Get Mystery Box with random crypto!

📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የሰርጥ አድራሻ: @leywo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

ማንበብ የስብዕና ልህቀትን ያጎናፅፋል!!
ማንበብ ምክንያታዊ እና የሰላ አእምሮን ያንፃል!!
በዚህ ቻናል
👉የስነ ልቦና ምክሮች
👉ግጥሞችና ወጎች
👉ሳይንስና ፍልስፍና
👉ከመፅሐፍ የተቀነጨቡ አስገራሚ ፅሁፎች እና ታሪኮች ይቀርባሉ።
ወዳጆዎን የዚህ የንባብ ማዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በመጋበዝ ቻናሉን ይደግፋ።
ማንኛውም አስተያየት @FiyametaGelay ላይ ይላኩልን
Creator -kalkidan

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-28 10:58:09 #ፀሐይ_ላይ_ተሰጥተው_ከበረዶ_አገር_ስንዴ_ልመና!


ኢትዮጵያ ብቻዋን በመጠን ከዮክሬን ሁለት እጥፍ የምትበልጥ አገር ናት! በህዝብ ብዛትም እንደዛው! በወጣት ቁጥርማ ኢትዮጵያ አጠገብ አትደርስም! ዪክሬን ከዓመት እስከአመት በከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ቅዝቃዜና በከፍተኛ ሙቀት የምትጨነቅ አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ከዓመት እስከዓመት ለኑሮም ይሁን ለእርሻ እጅግ ምቹ የአየር ንብረት አላት! ይሁንና ዩክሬን ከዓለማችን ከፍተኛ የእህልና ወዘተ ምርት አምራች አገራት አንዷ ዋናዋም ናት!

እንግዲህ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ድፍን የአፍሪካ ባለስልጣን አንገቱን በከረቫት አንቆ እንደዝንጀሮ ፀሐይ ሲሞቅ ስለኒዩክሌርና ምናምን ሲዘባርቅ ይከርምና ከዚች ከአፍሪካ ጋር ስትነፃፀር በአጉሊ መነፅር እንኳ ከማትታይ አገር ስንዴና ዘይት ይማፀናል! ሰሞኑን ከሩሲያ ጋር በተፈጠረው ጦርነት አፍሪካ ከዳር እዳር በኑሮ ውድነት የሚናጥበት አንዱ ምክንያትም ይሄ ነው! ወጉን ሲያሳምሩት ታዲያ "ምዕራባዊያኑ ራሳችንን እንዳንችል የሸረቡብን ሴራ" ይሉሀል! ድህነት ምርጫ ነው! መሰልጠን ወይም ሞት ብሎ የተነሳ አገር በማንም ሴራ ተገቶ አያውቅም! የአስራ ሶስት ወር ፀሀይ ላይ ተሰጥተን በድህነት ሙቀጫ የምንወቀጥ ስጦች ነን?ምንድነን?

@leywo
120 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:57:35 ጥያቄ """"""""""""""" ለሰላም መዘመር እምነቴ ነው ላለኝ ለዛ ባለ ጦማር ጥያቄ ነበረኝ። የተናገርከው ቃል ፅንፍ እውነት ካለበት ብዕር ይጣላል ወይ ጠመንጃ ለማንገት ብላችሁ በሉልኝ። ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) @leywo
131 views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:56:13 ሀዘን፣ ጭንቀት፣ ድብርት፣
ቁጣ፣ ፀፀት፣ጥላቻ  ....


መጥፎ አይደለሁ።


አሁን ላይ የሚሰማህ ይህ ከሆነ
ይህ ስሜት ስህተት አይደለም።





@leywo
128 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:54:54 #they_dont_care_about_us
#The_people_must_stop_the_war

... ተመልከት ከንጉሡ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ድሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም።ከላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫወት... እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ "ግፋ በለው!" ሲል የኖረ ነው። መንግሥቱ ኃ/ ማርያም ያንን ሁሉ የድሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው!? "ዙንባብዌ" ተንደላቆ ይኖራል። የኦነግ መሪዎችን ተመልከት ...…ወያኔዎችን ተመልከት ...ምን ሆኑ ? ኢትዮጵያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ! ሚስኪን ወጣቶች! በፖሮፓጋንዳ ያበደ አለማስተዋል ነው። ወጣት አልዋጋም ካለ ....መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲች ብለው #ስንጥር አያነሱም። ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ ! ስንት 'ጂኒየሶች!' እንኳን ጦርነቱ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል። ከዚህ ከበከተ እንቶፈንቶ ራቅ ! ተማር ! ተማር ! ተማር ! አሁንም ተማር ! ማንም መሃይም መተኮስ ይችላል ! መግደል ጀብዱ አይደለም÷ ጅብም ሰው ይገድላል። ታይፎይድም ÷ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት ; አገር ሸርፎ ከመሸጥ እኩል ነው። ለምንድን ነው የምትሞተው !? ለምንድነው ወጣት የሚሞተው !? ...ሊታረድ እንደሚነዳ በሬ የማይረባ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ ይወስዱታል። ወጣቱም ብልጥ የሆነ ÷ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ ÷ የመጠቀ አድርጎ ራሱን ያያል ÷ ሲስተሙ ነው እንደዚያ የሚያደርግህ። ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ ....አለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው።ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ። ፈሳሽ ውሃ ነው ÷ ቅርፅ የለውም ። አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል ÷ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ....ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን ። በስልጣን ከፍ ያሉት እያጋጩ 'ችርስ' የሚባባሉብን"

#አሌክስ አብርሃም
ከዕለታት ግማሽ ቀን ገፅ 132-133

@leywo
140 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:28:03
Every human being have obligation to his child to built-up his competent or dissolutions his plucky mindset....!
Every Father's
Every Mother's
At All Every Family can make his child with good mindset..then our generation become bloomer more and more than stars that shine on the sky....
And Finally
Your will .........then...like diamond build your capability .....heat resistivity !........
.
.
.
... Phineas Abate
Italians writer

picfromNoname ...!
153 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:14:22 "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!"

አንዳንዴ የሆነ ቦታ ላይ የምንፈልገው ነገር ይኖራል ከእርሱ ውጪ ምንም ነገር የሌለ ይመስለናል ፤ አልተሳካም ማለት በቃ አለቀልን መንገድ ላይ መቅረታችን ነው ፣ የእኛ ነገር አበቃ ተበላሸ ይመስለናል ግን ደግሞ ከአጠገቡ ሌላ ትልቅ እድል ትልቅ ህይወት ተቀምጦ ይጠብቀናል የፈጣሪ አላማ እኮ ሁሌም ለእኛ የሚበጀውን መስጠት ነው እንጂ ፈፅሞ ሊጥለን አይፈቅድም የአንዱን በር ሲዘጋብን ሌላውን ወለል አድርጎ እየከፈተው ነው ስለዚህ አትቁም ዞር ዞር ብለህ ተመልከት ይሄ ተዘጋ እንግድያው ያ ተከፍቷል በል መቼም አትቁም!
ተመኘን

@leywo
150 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:00:21 እንደ ጲላጦስ ከደሙ ነፁ ነኝ ሲሉ
እንደ ይሁዳ ስሜ ሸጥኳቸዉ።
ቃሊና

ይዬ ነዉ ገበያዉ

@leywo
137 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:00:38 #ምሬት

ምሬት ሲበዛ ሰዉ መኖር ይደክመዋል፡፡ ፍቅር ሲበዛ ደግሞ መኖር መኖር ያሰኘዋል...ነገን ይናፍቃል፡፡ በዚህ እልህ አስጨራሽ የምድር ኑሮ ይብዛም ይነስም ምሬቶቻችን አያሌ ናቸዉ፡፡

ከእንጀራና ወጥ ጀምሮ እስከ ሃገር ብዙ ነውጦች በልባችን ይከሰታሉ፡፡ ልባችን ብዙ ሲበጠበጥና ማረፍ ሲሳነዉ እዚህም እዚያም እያለ ያስቸግራል...ልብ ማስቸገር ከጀመረ ደግሞ እንደህፀን ልጅ በል ተዉ! ብለን በቀላሉ አንገታዉም፡፡

ልብ አሸባሪ ነዉ...በሚያየዉና በሚሰማዉ እያንዳንዱ ነገር ይሸበራል...ቀን እየገፋ ሲመጣ በህይወት የሚሰለችና ቶሎ የሚመረር ልብ በየቦታዉ እየበዛና፣ እየጨመረ፣ እየፈላ ይመጣል፡፡

የምሬት ዋናዉ መድሃኒት ብዙ ነገሮችን ማሳለፍ ይመስለኛል፡፡ ባየነዉና በሰማነዉ ነገር ሁሉ ልባችን እየተራገመና ደማችን ከፍ እያለ ከሄደ ብዙ የህይወት አቅጣጫችንን ማበላሸት እንጀምራለን፡፡

እራሳችን ያወላገድነዉን ኑሮ ደግሞ ማንም ሊያቃናልን አይችልም፡፡ አንድ ሰዉ እንደተናገረዉ “መንገድ ላይ በሚጮህብህ ዉሻ ላይ ሁሉ ድንጋይህን አትወርውር” እንዳለዉ በያንዳንዱ ቅፅበት ያለንን ማንነት አላፊ አግዳሚዉ ባወራዉ ላይ ሁሉ መሳተፍ እፈልጋለሁ ካልን ትልቅ ኪሳራ ዉስጥ እንገባለን፡፡

እንደኛ እንጀራ ለመብላት ደፋ ቀና በሚል ህዝብ መካከል ምሬቶቻችንን ብንዘረግፈዉ አዉርተን ዝንት አለም አንጨርሰዉም፣ ነገር ግን መልካሙን፣ ተስፋ የሚሰጥበትን፣ ብሩሁን ከዚህ ጨለማ ዉስጥ ሻማችንን አብርተን እንፈልግ!

#እኔው_ነኝ_ወንድማችሁ.!

@leywo
146 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:00:38 እንደምን ዋላቹ ቤተሰቦች ደስየሚል የበአል መዳረሻ ይዘንላቹ መጥተናል ብሩህ ቀን ይሁንልን መልካም ቆይታ

ውስጥህ_ያለው_ውስጣዊው_ሰው

አንተ እና ሃሳብህ አንድ እና የማትነጣጠሉ ብትመስሉም፣ አንተ ውስጥ ሌላ “ውስጣዊ ሰው” አለ፤ አንተን እና ሃሳቦችህንም የመሾፈር አቅም አለው።

ከአንተ ጋር ደባል ሆኖ አእምሮህን የሚያሽከረክረው አካል አለ። ይህንን ሰው አስወግደህ፣ አንተ በራስህ አእምሮህን መቆጣጠር ስትጀምር፣ አዲስ እና ሰፊ በር ትከፍታለህ። ይሄ ሰፊ በር ወደ ፈጣሪነት፣ ወደ ጉብዝና፣ ወደ ደፋርነት፣ ወደ ንቃት የሚያስገባ በር ነው።

ምን ይሆን የሚለውን በቀጣይ ክፍል ይጠብቁን?
መልካም የበአል መዳረሻ ይሁንልን


@leywo
146 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:49:48 ጥያቄ
"""""""""""""""
ለሰላም መዘመር
እምነቴ ነው ላለኝ
ለዛ ባለ ጦማር
ጥያቄ ነበረኝ።
የተናገርከው ቃል
ፅንፍ እውነት ካለበት
ብዕር ይጣላል ወይ
ጠመንጃ ለማንገት

ብላችሁ በሉልኝ።

ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)

@leywo
149 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ