Get Mystery Box with random crypto!

📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የቴሌግራም ቻናል አርማ leywo — 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗
የሰርጥ አድራሻ: @leywo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

ማንበብ የስብዕና ልህቀትን ያጎናፅፋል!!
ማንበብ ምክንያታዊ እና የሰላ አእምሮን ያንፃል!!
በዚህ ቻናል
👉የስነ ልቦና ምክሮች
👉ግጥሞችና ወጎች
👉ሳይንስና ፍልስፍና
👉ከመፅሐፍ የተቀነጨቡ አስገራሚ ፅሁፎች እና ታሪኮች ይቀርባሉ።
ወዳጆዎን የዚህ የንባብ ማዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በመጋበዝ ቻናሉን ይደግፋ።
ማንኛውም አስተያየት @FiyametaGelay ላይ ይላኩልን
Creator -kalkidan

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 19:46:25
.
.
"አንዳንድ ነገሮች ለመጻፍ አስቸጋሪ ናቸው።
አንድ ነገር ካጋጠመህ በኋላ፣
ለመጻፍ ትሞክራለህ እና ወይ ከሆነው በላይ ድራማዊ ታደርገዋለህ ወይም ከሆው በታች ታሳንሰዋለህ።
የተሳሳቱ ክፍሎችን ታጋናቸዋለህ ወይም አስፈላጊ የሆኑትን ችላ ትላቸዋለህ። በማንኛውም ሁኔታ ፣ በጭራሽ ሊሆን በፈለከው መንገድ አድርገህ አፅፈዉም።"

Sylvia Plath, The Unabridged Journals
of Sylvia Plath
(FB page #Books_and_Gleam)

join and share
31 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 17:34:27 | 6 |

እኔ ምልሽ



እናንተ የህልም አለም ሰዎች ግን ስለኛ ምን ታስባላችሁ?

ስለ እነማን?

ስለ እኛ የእውነት ስለምንኖረው?

ኮንፊደንሳችሁ ይገርመናል

እንዴት

ራሳችሁን “የእውነት የምንኖረው” ትላላችሁ



@leywo
52 views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 17:28:59
ጥሩ ጓደኛ ልክ እንደ መስታወት እና ጥላ ነው መስታወት አይዋሽም ጥላ መቼም ትto አይሄድም !

@leywo
46 views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 17:11:50
የሴት "ሱሰኛ "ይሉኛል "ድንቄም" ሴት ልጅ ክብርዎን ስጠብቅ ነዉ
የሚያምርባት ይሉኛል ክብረ ቢሳች ግን እንሱ ናቸዉ አስመሳዬች ውጫቸዉ ሌላ ዉስጣቸዉ ሌላ ከንቱዎች ወሬ ብቻ!.… ,ስጠጣ እራሴን እረሳለዉ ወደሆነ አለም መጓዝ ጀምራለዉ ዉስጤ ደስ ይለዋል .………?
በቃል
50 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:59:30 ለጤዛ ተዋደቅን...

እድሜያችን ሰባ ነው ቢበዛ ሰማኒያ፣
ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ፣
አንዱ ከአንዱ ፅዋ ጥቃት የቀመሰ፣
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ፣
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ፣

መንገዱን ሸንሽኖ በአጋም እሾህ ቅጥር፣
ወገን እየለየ ባሰለፈን ቁጥር፣
ጤናችን ሲሸረፍ፣
ቀናችን ሲዘረፋ፣
የት ሸሽተን እንትረፍ፣

በዶፍ ዝናብ ሀገር ለዜዛ ተዋድቀን፣
ሰላም እንደራበን ደስታ እኔደናፈቀን፣
ትግላችን ሰልፋችን ያበቃል አንድ ቀን፣

#በእውቀቱ_ስዩም

@leywo
59 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:33:02 አንዳንዴ እግዚአብሄር ምርጥ ናቸዉ ያልናቸዉን ፕላኖች ሳይቀር ለጥቅማችን ሲል ያስቀራቸዋል፡፡

#ቶሚ_ደንዲ

መልካም ቀን




@leywo
67 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:29:36



ሁሌ'ም ደስ የመሰኘት ፍላጎትህ
ደስታ ቢስ ያደርግሀል።



@leywo
114 views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:51:53 የዜግነት ቀብር
(በላይ በቀለ ወያ)
አብረን እንዘምር
.
.
የዜግነት ቀብር፣ በኢትዮጵያችን በዝቶ
ታየ ግፍ ጥላቻ ፣ ዳር እስከዳር ጎልቶ
ለበቀል ለበደል ፣ ለህዝቦች ባርነት
በአረመኔዎች እጅ ፣ ታርደናል በአንድነት
መሠረተ በቀል፣ ፍቅር እያዘመረን
ህዝቦች ነን በሴራ፣ ጅምላ የሚቀብረን
ድርቅ የርሀብ መድረክ፣ ጦርነት ማያጣት
የተፈጥሮ ገብያ፣ ሒያጅ መጪው ሚሸጣት
እንጠብቅሻለን፣ ሞተን በየተራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ፣ እኛ ለአንቺ እንፍራ!

ቀ ላ ል➘➘➘
@leywo

♡ ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
በላይ በቀለ ወያ

በጣም ያሳስበኛል በላይ ያለበት ሁኔታ እባካይሁ አየነው የምትሉ ካላችሁ አሳውቁን ከስር በምታገኙት ሊንክ
118 views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:13:47
፡ እኔ እምኖረው በራሴ ህግ ነው……አለምን መምሰል አልፈልግም…የወሸት ከመወደድም የእውነት መጠላትን እመርጣለው…ከማንምም ምንም አልጠብቅም…ለዛም ይመስለኛል ቢከፋኝም ደስተኛ የሆንኩት…



@leywo
113 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:40:00
#የተለያዩ_ኢትዮጵያዎች

ይህ ዘገባ “ኢትዮጵያውያን ብዙ እንደሆኑ” ያሳያል። መገለጫዎቹ አካላዊና ፅንሰ-ሀሳባዊ በመሆናቸው የተነሳ፣ ኢትዮጵያን ሀሳብም፣ ቦታም አድርጓታል፡፡ በቦታነት ሲታይ፣ ምቹ የሆኑ አካላዊ ባህሪያትን በማጣመር የተንጣለለ የመሬት ስፋት ነው። ከዚያም ግዛተ አጼ በመሆን የጽሑፍ ፊደላትንና ሥነ ጽሑፍን፣ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን ያፈራ መንግሥት ሆነ።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ባህሪያት በቀላሉ ሊመላከት የማይመች በጣም ሰፊ ትርጉም አላት። ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ የሚነሳው ቃሉን ከግብፅ በስደቡብ ለሚኖር ማንኛውም ሰው እንደ አጠቃላይ መጠሪያነት በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ ከሰሃራ በስተደቡብ ያለውን ሀገር የበለፀገ ባህሪና ማንነት ለመግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች አጠጋግተው ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ ሀሳቡ በጥንታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ መገኘቱ የእምነት ስሜትንና ከመለኮታዊው ዓለም ጋር ላለው ደመ ነፍሳዊ ቅርበት እማኝ ሊሆን ይችላል።

እነዚህ የተለያዩ ኢትዮጵያዎች፣ በአፍሪካ ቀንድ ተራራማ ቦታዎች ላይ በመሰባሰብ፣ የረጅም ጊዜ ኃይማኖታዊና ክርስቲያናዊ የእምነት ትውፊት ያላት ትልቅና ጠቃሚ የሆነችውን ሀገር ባህልና ማንነትን ለመመስረት ችለዋል። ይህ ቁርኝት በሂደት አንዲት ልዩ የክርስቲያን ቤተ እምነትንና ከየትኛውም የዓለም ክፍል የተለየ ክርስቲያናዊ ቅርጽን አስገኝቷል። የጥንት ግሪኮች ኢትዮጵያውያን ኃይማኖታዊ ሥርዓቶችንና ልማዶችን በመፍጠር ረገድ ያላቸውን የፈጠራ ችሎታ የጠቆሙት “ሊመጣ ስላለው ነገር ትንቢታዊ ብልጭታ ተገናኝቷቸው ይሆን?” ያስብላል፡፡

#ኦርቶጵያ መጽሐፍ

*
134 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ