Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 2 በሆነ ግዜ በሆነ ሰዓት ገዳም ተገኝቻለዉ ቤተክርስቲያንዋ ዙርያሁን በዛፎች ተከባለች ጭር ያ | 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

ቀን 2
በሆነ ግዜ በሆነ ሰዓት ገዳም ተገኝቻለዉ ቤተክርስቲያንዋ ዙርያሁን በዛፎች ተከባለች ጭር ያለ ዝምታ ጊዜዉን ተረክብዎል ሁሉም ሚጓዘዉ በእርጋታ እና የሚግባቡት በጥሞና ነዉ የሆነ ሚጨንቅ ስሜት አለዉ እኔ ጥሎብኝ ዝምታ ሲሆን ይጨንቀኛል ምክንያቱም ከጭንቅላቴ ጋር መጋፈጥ ያስፈራኛል ሆ
የመጣዉበትን ቀን ሁሉ ቁጭ ብዬ መራገም ጀመርኩ አብሶ ስልኬ ናፍቆኛል ብዙ ብዙ ነገር አሁን በአጠገቤ የሚያልፉት ገዳመዉያን ማስበዉን ቢያቁ ኖሮ ምን ያህል ከንቱ መሆኔንበየትኛዉም መስፈርያ ለክተዉ ይጨርሱይሆን
እህተ ገብርዬል እህተ ገብርዬል መንገድ ላይ
ከኔ ዉጭ ማንም የለም ማንን ነዉ ብዬ ጋር ገባኝ ምነዉ ልጄ ወዴት ኤድሽ እረገይ በስማም መንፈሳዊ ስሜን ሁሉ ረስቻለዉ አምላኬ በዉስጤ አማተብኩ።

ቀን 5
እንዴት ነዉ ልጄ ለመድሽዉ ይመስገን
እማሆይ እየለመድኩት ነዉ በጣም የሚገርመኝ እፍኝ የማትሞላ ባቄላ ለነብሳቸዉ ማቆያ አፋቸዉ ላይ ያረጉና ሙሉ ቀን ቀጥ ብለዉ ከነ ወዛቸዉ ቅዳሴቸዉን ፀሎታቸዉን ሳያዛብ ያደርሳሉ። ወዛቸዉ ፊታቸዉ ላይ
ያለዉ እርጋታ በጣም ያስቀናኛል እኔ ከነሱ ይበልጥ እየበላዉ እየተኛዉ ይርበኛል ይደክመኛል ከእንቅልፌ ሁሉ እማሆይ ናቸዉ ለፀሎት የሚያነሱኝ ብቻ ወደ ፈጣሪ
መቅረብ ስጋዊ ሕይወት ትቶ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ መታደል መፅናት መመረጥ ነዉ እኛ አለማዊ ሰዎሆች በቀን .ሶስቴ ሆዳችንን እየሞላን እራሳችንን እየተንከባከብን የነሱን ጫፍ አንደርስም ያሁ አመዳም ነን ከንሱ ጋር መቀመጥ በራሱ ሰላም አለሁ አለማዊ ሰዎች ስንባል በጭንቅላታችን ሰዎችን እያማን በአፋችን የሚንቀረጥፍ ሰዉ በላዎች ነን።

ቀን 8
እዉነት እማሆይ ግን እናንተ ምትኖርት ሕይወት በጣም ከባድ ነዉ ይቅርታ ያድርጉልኝ እና
መጀመርያ ደግፍየዉ ነበር ግን ደግሞ ብዬ ዝም ስል እማሆይ ፈገግ ብለዉ እያዩኝ ነዉ በዉስጤ ስንት ነገር እያሰብኩ ስንት ቀን በርግግያለዉ አምላኬ ይቅር በለኝ
በዛ መንገድ አስቤዉ አይደለም ብይ ይቅርታን እሻለዉ ለንሳዓ የወሰድኩት ፆም ፀሎት ስያደክመኝ ምነዉ በቀረብኝ በየትኛዉ አጥያቴ ነዉ ብዬ እራሴን እንደ ፃዲቅ ለመቁጠር ያምረኛል ሰዉ አልገደልኩ ብዬ አጥያትን ከአጥያት ለማመዛዘን ሞክራለዉ አምላክ
ዘንድ ትልቅ ትንሽ ብሎ ነገር የለዉም ደግሞ ሰዉ አልገደልኩ ብዬ እራሴን መካቤም ከገደለዉ እኩል ያስቆጥረኛል።
ቀን 10
አንድ ቀን ጥዎት ከፀሎት መልስ አባን ቁጭ ብለዉ አያዋቸዉ እና እሳቸዉ ጋር ደርሼ መስቀል ተሳልሜ አጠገባቸዉ ቁጭ ብዬ በዉስጤ ብዙ ነገር እያሰብኩ ነበርም የሆነ ፀፀት ባዶ መሆን እየተሰማኝ ነበር ከዛ አባም አይ ልጄ እንደዛ አይሰማሽ ሲሉኝ በረገኩ ዉስጤን ማወቃቸዉ አስደነገጠኝ ጭምር ሁሉም ሰዉ ፈጣሪ በአሰበዉ መንገድ ነዉ ሚጓዘዉ በትናት መፀፀትም መሐዘን ዛሬን አይቀይረዉም ዋናዉ ሳይረፍድ ወደ አምላክ መመለሱ ነዉ ደግሞ ልጅ ልምከርሽ ሁሌም ነገ ላይ ሆነሽ ማታፍሪበቲን ነገር ዛሬ
ላይ አድርጊ ሴት ነሽ ብዙ ነገር ይጠብቅሻል ፈጣራ ይባርክሻል የአብራክሽን ልጅ ስታገኚ ለልጆችስ ምን አይነት ሰዉ እንደነበርሽ ለመናገር ትናትህሽን ከጥቁር አሻራ ማንፃት አለብሽ ምክንያቱም ትናትህ ምን አይነት ሰዉ ነበርኩ ልትያቸዉ።


ይቀጥላል


ከመንገደኘዋ ማስታወሽ የተቀነጨበ…


@leywo