Get Mystery Box with random crypto!

የዛሮቼ ንግስት ጠማማው ዕድሏ ገጣሚ ላይ ጥሏት ምጥ ቢያታግላትም ካዋላጇ ጀርባ ጣሯን በስንኞች | 📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗

የዛሮቼ ንግስት

ጠማማው ዕድሏ ገጣሚ ላይ ጥሏት
ምጥ ቢያታግላትም
ካዋላጇ ጀርባ ጣሯን በስንኞች ከማሳመር ውጪ
አይዞሽ አላልኳትም፡፡
ያኔ ሰድባኛለች...
በስቃይዋ መሀል ግጥም ለመሰደር
ቃላቶችን ሳምጥ ተጠይፋኛለች፡፡
ዳሩ ምን ያደርጋል
ከርሞ እንደማዘኗ ዘመን ሳያርመኝ
ዛሬም በንዴቷ ቁስል ያለበት ስንኝ መፃፌ ገረመኝ፡፡
የጥበብ ዛሮቼን እያራገፍኩባት
እሷን ቢከፋትም
እንደ ሴትነቷ ፡ እንደ እናትነቷ
ፅፌ አልጨረስኳትም፡፡
ጌታነህ ደጉ
@leywo