Get Mystery Box with random crypto!

ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

የቴሌግራም ቻናል አርማ kezimkezia — ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!
የቴሌግራም ቻናል አርማ kezimkezia — ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!
የሰርጥ አድራሻ: @kezimkezia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.50K
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው።
Any comment @jer21

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-07 20:44:40
ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia
1.9K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 05:36:42 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው!

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው፡፡ አንዱ ክንፍ እውቀት ነው፡፡ ሌላኛው ተግባር ነው፡፡ ሰዎች ለመለወጥ የሚቸገሩበት አንደኛው ምክንያት ከእውቀት እጦት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በማታውቀው ነገር ዙሪያ እንዴት ትለወጣለህ? ይሄ ቦታ አልተመቸንም ብንል የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ሄደን ምን ያጋጥመናል? ካላልን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁሉ እውቀት ኖሮን ደግሞ ባለንበት ቁጭ ብንል ተለወጥን ማለት አይደለም። አሁን እንደውም ትልቁ ሽወዳ ያለው አንዳንዴ ብዙ ስለለውጥ ስናውቅ የተለወጥን ይመስለናል፡፡ ከእሱ ደግሞ አለማወቅ ሁሉ ይሻላል፡፡

እውቀት ብርሀን ነው፡፡ ካወክ በራልህ ማለት ነው ፡፡ ቤት ውስጥ መብራት ባይኖር ምንም ማድረግ አትችል ይሆናል፡፡ ግን ቤት ውስጥ መብራት ቢኖር ስቶቩን ለኩሶ ፣ እቃውን አውጥቶ ፣ ድስቱን ጥዶ ምግብ አብስሎ አያበላህም፡፡ ነገር ግን አንተ እንድትሰራ በር ይከፍትልሀል፡፡

ስለዚህ እውቀትን እና ተግባርን ማቀናጀት ነው ለውጥ የሚፈጥረው! ምንድን ነው መለወጥ የምንፈልገው? እሱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እሱንም መለየት እና ማድረግ ነው፡፡ ጓሮህን ከሆነ መለወጥ የምትፈልገው እንዴት መለወጥ እንደምትችል ማወቅ አለብህ፡፡ ከዛ እጅህን ሰብስበህ መነሳት አለብህ፡፡ ጓሮህ ተቀየረ ማለት ነው፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@Kezimkezia
2.1K views02:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 20:10:06 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፤ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ ሀሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡

ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡ መንገድ የሚከፈተው ኅሊናህ ውስጥ ነው፡፡ አስቀድመው በኅሊና መንገድ ወደ ጨረቃ የሄዱ ሰዎች በኋላ በመንኮራኩር መንገድ ለመሄድ አልቸገራቸውም፡፡

ዳንኤል ክብረት
"ኅሊና እና መንገድ"

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia
2.1K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 21:14:32 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

"የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበትም!"

መነሻ ሃሳብ :- " ማታ ማታ - ገጽ 110

"ማሰብ ተፈጥሯዊ ባህሪህ ቢሆንም በማሰብ ላይ ያለህ ብስለት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ካንተ የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥምህ ለሃሳቡ በምትሰጠው ምላሽ(ግብር) ነው።

እምትወደው ሰው የግድ ባንተ ሃሳብ የሚስማማ ወይም አንተ የምትወደውን ብቻ የሚወድ መሆን የለበትም። እንደዛ አይነት ሰው ከፈለግክ ያንተን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የሀሳብና የፍላጎት ወዛደር እንጂ አሳቢን አታገኝም።

የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር በመውደድ አይደለም መዋደዱ የሚገለጸው። ካንተ ለተለየ ነገር ሁሉ ጥላቻ ከሆነ ምላሽህ በትክክል ማሰብ መቻልህም ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በሃሳብ መፋለስ የልዩነት እንጂ የጥላቻም ያለመዋደድ መንስኤም ሆነ ምልክት አይደለም። አንተ ራስህ በየቀንና በየሰአቱ የምታስባቸው ሃሳቦች ልዩነት አላቸው፤ ግን አቻችለሀቸው እየኖርህ ነው። ታድያ የሰውን ልዩነት ማቻቻልስ እንዴት ያቅትሀል...…?

ለራሳችን ጥያቄ ሰተነው እንጨርስ!

የሀሳብ ልዩነቶችን ለምን በስድብ እናጣጣቸዋለን።

ሰዎች እኛ ያልደገፍነውን ስለደገፉ ለምን እንዲያፍሩ እናደርጋቸዋለን?"

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@kezimkezia
2.4K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 21:05:34
ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተቃቀፍ ተሳስመው አንዱ የቋጠረውን ስንቅ በጋራ ሊመገቡ ተቀመጡ። ይኸንን ትዕይንት ለአፍታ የተመለከተው የክርስቲያን ልዑል ወደ ሁለቱ ሰዎች ተጠግቶ ስለትውውቃቸው ጠየቃቸው።

መመገባቸውን ሳያቋርጡ አንዱ ቀና ብሎ ፦

"ካለዛሬ አይቼው አላውቅም ..." አለው።

"ምናልባት የአንድ ሀገር ልጆች ትሆኑ ...?" ሲል ጠየቀ ልዑሉ።

"ሀገሩንም አላውቅም ..." አለ ሰውየው አሁንም መመገቡን ሳያቋርጥ።

"ታዲያ ለምንድ ነው እንዲህ ዓይነት ፍቅር ያሳየኸው...?" አለ ልዑሉ በፍፁም ግርምት ተሞልቶ።

"በእኔ መንገድ ላይ ሲጓዝ ስላገኘሁት ነው" አለው።

ልዑሉም ተደንቆ ዝም ብሎ አልሄደም። በዚያ ቦታ ለሱፊዎች ማረፊያ የሚሆን ትልቅ አዳራሽ ሰራ። ዛሬ አዳራሹ ዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የሱፊዎች መፍለቂያ "ዩኒቨርስቲ" ሆኗል።

ጥበብ ከጲላጦስ

ሰው መሆን እኮ እንዲህ ነው፤ በሀይማኖት ተለያይቶ ፣ በደም ሳይተሳሰሩ ፣ በባህል ሳይገናኙ ፣ ነገር ግን መረዳዳት ፣ አብሮ መብላት ፣ እንደሰው ተያይቶ አብሮ ችግርን መካፈል ማለት ነው። ባጠቃላይ በፍቅር ለመኖር ሰው መሆንና እንደ ሰው ማስተዋል ብቻ በቂ ነው።

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia
2.3K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 21:01:23 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

እኔ ትንሽነቴን አልረሳም፤ ማወቄም አያመፃድቀኝም። ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው። ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ፤ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።

Unknown

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@kezimkezia
2.3K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 19:54:25 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ታገሱ!

የሰዎች ሁኔታና የነገሮች እልህ አስጨራሽነት እጅግ ፈታኝ የሆነበት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጸለዬ፤ “ፈጣሪ ሆይ እባክህን ትእግስትን ስጠኝ፤ ይህንን የለመንኩህን ትእግስት ደግሞ አሁኑኑ እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” ይህ ሰው ፈጣሪ ትእግስትን እስከሚሰጠውም መታገስ አልቻለም፡፡

ትእግስትን እንማረዋለን እንጂ አንቀበለውም፡፡ ትእግስትን የመማሪያው ብቸኛ መንገድ ደግሞ እልህ አስጨራሽ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፍና አስቸጋሪ ሰዎችን ችሎ መንገድን በመቀጠል ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ስንጀምር የሚፈታተነን ነገር ቀስ በቀስ እየደከመ ይሄዳል፡፡

አያችሁ እኛ አመለካከታችንን በመለወጥ በልጠንና ተሽለን እንገኛለን እንጂ ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታዎችና ሰዎች እስከወዲያኛው ድረስ ከአካባቢያችን አይጠፉም፡፡ ትእግስት ባጣንና እልኸኛ በሆንን ቁጥር ውስጣችን ያለውን የትእግስት መጠን አለአግባብ ስለምናቃጥለው ቀስ በቀስ በጥቃቅን ሁኔታዎችና አመላከከታቸው እጅግ አናሳ በሆኑ ሰዎችም ሳይቀር መፈተን እንጀምራለን፡፡ ሁሌም መታገስን ምረጡ!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia
2.4K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:58:11 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፤ ድንገተኛ ወጪዎች፤ የገንዘብ እጥረት፤ የጉዳዮች መጥመም፤ የሰዎች ክህደት፤ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፤ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፤ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፤ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል!

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Kezimkezia
2.4K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:32:37
የጎዳና ተዳዳሪው ቢል ሬይ ለሳራ የዳይመንድ ቀለበቱን ሲመልስላት።
2.5K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 12:31:51 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ

አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያዋ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ ሽማግሌ ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለው ሲለምኑ ትመለከታለች።

ሳራ ወደ ሽማግሌው በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን ሽማግሌው ከጎናቸው ባስቀመጡት የፕላስቲክ ኩባያ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ትቀጥላለች።

ሳራ ከምንግዜውም በላይ በህይወቷ ደስተኛ ነበረች፤ ከምትወደውና ከምታፈቅረው ጓደኛዋ ጋር በትዳር ለመጣመር የቀናት ዕድሜ ቀርቷቸዋል።

ለእሷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያለው ፍቅረኛዋ እጅግ ውድ የሆነ ዳይመንድ የቃል ኪዳን ቀለበት ገዝቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ካቀረበላት እና በደስታ እሺ ካለችው ጊዜ አንስቶ ህይወቷ በሀሴት ተሞልቷል።

ምሽት ላይ እንደተለመደው በስስት የምታየውን የዳይመንድ ቀለበት ስማ ለመተኛት ቦርሳዋን ከፈተችው፤ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፤ ቀለበቱ በቦታው አልነበረም።

ቦርሳዋን የከፈተችው መንገድ ዳር ቁጭ ብለው ለሚለምኑት ሽማግሌ ገንዘብ ለመስጠት ብቻ እንደነበር አስታውሳ የሽማግሌው ገንዘብ መሰብሰቢያ ኩባያ ውስጥ ቀለበቱን አብሮ እንደገባባት ጠረጠረች።

ለእጮኛዋ ስልክ በመደወል ሁኔታውን አጫወተችው፤ እጮኛዋም ሲከንፈ መጣ።
ተያይዘው በልመና ወደ ሚተዳደረው ሽማግሌ ቦታ ሄዱ፤ ሽማግሌው ግን በቦታው አልነበሩም።

"በእርግጥ ውድ የሆነ ቀለበት አግኝቶ እንዴት ተመልሶ በቦታው ሊቀመጥ ይችላል" የእጮኛዋ ግምት ነበር።

በቀጣዩ ቀንም በተመሳሳይ ከእጮኛዋ ጋር ሽማግሌው ተቀምጠው ወደ ሚለምኑበት ቦታ ሄዱ፤ አሁንም አልነበሩም። "በቃ ጦስሽን ይውሰድ ከእንግዲህ እርምሽን አውጪ" ነበር የእጮኛዋ መልስ።

በሦስተኛው ቀንም ሳራ ለእጮኛዋ ደውላ ወደ ሽማግሌው ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው። እጮኛዋ በመገረም "6 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት ችግረኛ እና በረንዳ የሚያድር ሰው እጅ ገብቶ አገኘዋለሁ ብለሽ እንዴት ታስቢያለሽ?" ነበር ያላት። ሳራም "በቃ የዛሬን ብቻ እንየው፤ ሰውየው ከሌለ እርሜን አወጣለሁ" አለችው።

እጮኛዋም የሳራን ፍላጎት ለመሙላት ተስማምቶ ጉዞዋቸውን አቀ፤ ሽማግሌው በቦታው ተቀምጦ ሲለምን አገኙት።
ሳራ በደስታ ተዋጠ፤ አላውቅሽም ብሎ እንዳይሸመጥጠኝ የሚል ስጋት እንደዋጣት ወደ ሽማግሌው ተጠጋች።

አባት ያስታውሱኛል? በማለት ጠየቀች። ሽማግሌው ቢል ሬይ ሀሪስ ይባላ፤ ቀና ብሎ ተመልክቷት "አላወቅኩሽም ልጄ" ሲል መለሰላት።

ሳራም "ከ3 ቀን በፊት ከቦርሳዬ ገንዘብ አውጥቼ ሳስቀምጥ ሌላ ዕቃ አብሬ አኑሬ ነበር ?" ስትል ጠየቀቻቸው?

"የጣት ቀለበት ነው?" አሉ ሽማግሌው።

"አዎን አባት!" አለች ሳራ።

ቢል ቀለበቱን ጠቅልሎ ካስቀመጠበት ኪሱ በማውጣት "አንድ ቀን እንደምትመለሺ አውቅ ነበር" በማለት ከሰጣት ብኋላ "ቀለበቱን ያገኘሁት ዕለት ትክክለኛ ወይም አርቴፊሻል ቀለበት መሆኑን ለማወቅ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወስጄው ነበር፤ እነሱም ትክክለኛ መሆኑን ነግረው $4,000 ዶላር ሊገዙኝ ጠይቀውኝ ነበር። በእርግጥ ኑሮውን በበረንዳ ለሚያሳልፍና በልመና ለሚተዳደር 4ሺህ ዶላር ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ነገር ግን እኔን ለመርዳት ብላ በስህተት ቀለበት የጣለችን ሴት ንብረት መንካት አልፈለግኩም። በመሆኑም በጥንቃቄ አኑሬው የአንቺን መምጣት ስጠባበቅ ነበር።" ሲል መለሰላት።

ሳራ ዳርሊንግ እና እጮኛዋ የመልካሙን ቢል ሬይ ሀሪስ ታሪክ ከታች ቀለበቷን ሲሰጣት ከሚታየው ምስል ጋር በማያያዝ በሶሻል ሚዲያ (Facebook) ለጠፉት፤ ከታሪኩም ጎን ለጎን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ አካውንት ከፈቱ። በቢል ሬይ ቀናነት እጅጉን የተደሰቱ አያሌ ግለሶቦች የዕርዳታ እጃቸውን ይዘረጉ ጀመ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ 260,000$ ዶላር ተሰበሰበለት።

በአሁን ሰዓት ቢል ከበረንዳ አዳሪነት ወጥቶ የቤት ባለቤት ነው፤ ተጨማሪ የመጦሪያ ገንዘብም አገኘ።

ወድቆ የተገኘ ሁሉ አይወሰድም። በተለይ በኢትዮጵያን ባህል ነውር ነው። ባለቤቱ ጠፋብኝ ብሎ ሊመጣ ይችላልና ልክ እንደ አደራ እቃ በጥንቃቄ አስቀምጦ ፈላጊው እስኪመጣ መጠበቅ ያስፈልጋል። በትንሹ ስትታመን፤ ፈጣሪ ደሞ በብዙ ይሰጥሀል።

ምንጭ :- ከፌስቡክ

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@Kezimkezia
2.7K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ