Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተቃቀፍ ተሳስመው አንዱ የቋጠረውን ስንቅ በጋራ ሊመገቡ ተቀመጡ። ይኸንን ትዕይንት ለአፍታ የተመለከተው የክርስቲያን ልዑል ወደ ሁለቱ ሰዎች ተጠግቶ ስለትውውቃቸው ጠየቃቸው።

መመገባቸውን ሳያቋርጡ አንዱ ቀና ብሎ ፦

"ካለዛሬ አይቼው አላውቅም ..." አለው።

"ምናልባት የአንድ ሀገር ልጆች ትሆኑ ...?" ሲል ጠየቀ ልዑሉ።

"ሀገሩንም አላውቅም ..." አለ ሰውየው አሁንም መመገቡን ሳያቋርጥ።

"ታዲያ ለምንድ ነው እንዲህ ዓይነት ፍቅር ያሳየኸው...?" አለ ልዑሉ በፍፁም ግርምት ተሞልቶ።

"በእኔ መንገድ ላይ ሲጓዝ ስላገኘሁት ነው" አለው።

ልዑሉም ተደንቆ ዝም ብሎ አልሄደም። በዚያ ቦታ ለሱፊዎች ማረፊያ የሚሆን ትልቅ አዳራሽ ሰራ። ዛሬ አዳራሹ ዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የሱፊዎች መፍለቂያ "ዩኒቨርስቲ" ሆኗል።

ጥበብ ከጲላጦስ

ሰው መሆን እኮ እንዲህ ነው፤ በሀይማኖት ተለያይቶ ፣ በደም ሳይተሳሰሩ ፣ በባህል ሳይገናኙ ፣ ነገር ግን መረዳዳት ፣ አብሮ መብላት ፣ እንደሰው ተያይቶ አብሮ ችግርን መካፈል ማለት ነው። ባጠቃላይ በፍቅር ለመኖር ሰው መሆንና እንደ ሰው ማስተዋል ብቻ በቂ ነው።

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia