Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ 'የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበት | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

"የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበትም!"

መነሻ ሃሳብ :- " ማታ ማታ - ገጽ 110

"ማሰብ ተፈጥሯዊ ባህሪህ ቢሆንም በማሰብ ላይ ያለህ ብስለት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ካንተ የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥምህ ለሃሳቡ በምትሰጠው ምላሽ(ግብር) ነው።

እምትወደው ሰው የግድ ባንተ ሃሳብ የሚስማማ ወይም አንተ የምትወደውን ብቻ የሚወድ መሆን የለበትም። እንደዛ አይነት ሰው ከፈለግክ ያንተን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የሀሳብና የፍላጎት ወዛደር እንጂ አሳቢን አታገኝም።

የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር በመውደድ አይደለም መዋደዱ የሚገለጸው። ካንተ ለተለየ ነገር ሁሉ ጥላቻ ከሆነ ምላሽህ በትክክል ማሰብ መቻልህም ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በሃሳብ መፋለስ የልዩነት እንጂ የጥላቻም ያለመዋደድ መንስኤም ሆነ ምልክት አይደለም። አንተ ራስህ በየቀንና በየሰአቱ የምታስባቸው ሃሳቦች ልዩነት አላቸው፤ ግን አቻችለሀቸው እየኖርህ ነው። ታድያ የሰውን ልዩነት ማቻቻልስ እንዴት ያቅትሀል...…?

ለራሳችን ጥያቄ ሰተነው እንጨርስ!

የሀሳብ ልዩነቶችን ለምን በስድብ እናጣጣቸዋለን።

ሰዎች እኛ ያልደገፍነውን ስለደገፉ ለምን እንዲያፍሩ እናደርጋቸዋለን?"

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@kezimkezia