Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፤ አልጋ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፤ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ ሀሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡

ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡ መንገድ የሚከፈተው ኅሊናህ ውስጥ ነው፡፡ አስቀድመው በኅሊና መንገድ ወደ ጨረቃ የሄዱ ሰዎች በኋላ በመንኮራኩር መንገድ ለመሄድ አልቸገራቸውም፡፡

ዳንኤል ክብረት
"ኅሊና እና መንገድ"

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@Kezimkezia