Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው!

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው፡፡ አንዱ ክንፍ እውቀት ነው፡፡ ሌላኛው ተግባር ነው፡፡ ሰዎች ለመለወጥ የሚቸገሩበት አንደኛው ምክንያት ከእውቀት እጦት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በማታውቀው ነገር ዙሪያ እንዴት ትለወጣለህ? ይሄ ቦታ አልተመቸንም ብንል የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ሄደን ምን ያጋጥመናል? ካላልን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁሉ እውቀት ኖሮን ደግሞ ባለንበት ቁጭ ብንል ተለወጥን ማለት አይደለም። አሁን እንደውም ትልቁ ሽወዳ ያለው አንዳንዴ ብዙ ስለለውጥ ስናውቅ የተለወጥን ይመስለናል፡፡ ከእሱ ደግሞ አለማወቅ ሁሉ ይሻላል፡፡

እውቀት ብርሀን ነው፡፡ ካወክ በራልህ ማለት ነው ፡፡ ቤት ውስጥ መብራት ባይኖር ምንም ማድረግ አትችል ይሆናል፡፡ ግን ቤት ውስጥ መብራት ቢኖር ስቶቩን ለኩሶ ፣ እቃውን አውጥቶ ፣ ድስቱን ጥዶ ምግብ አብስሎ አያበላህም፡፡ ነገር ግን አንተ እንድትሰራ በር ይከፍትልሀል፡፡

ስለዚህ እውቀትን እና ተግባርን ማቀናጀት ነው ለውጥ የሚፈጥረው! ምንድን ነው መለወጥ የምንፈልገው? እሱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እሱንም መለየት እና ማድረግ ነው፡፡ ጓሮህን ከሆነ መለወጥ የምትፈልገው እንዴት መለወጥ እንደምትችል ማወቅ አለብህ፡፡ ከዛ እጅህን ሰብስበህ መነሳት አለብህ፡፡ ጓሮህ ተቀየረ ማለት ነው፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን

@Kezimkezia