Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

እኔ ትንሽነቴን አልረሳም፤ ማወቄም አያመፃድቀኝም። ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው። ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ፤ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።

Unknown

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

@kezimkezia