Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን! አንዳንድ ጊ | ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ

ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፤ ድንገተኛ ወጪዎች፤ የገንዘብ እጥረት፤ የጉዳዮች መጥመም፤ የሰዎች ክህደት፤ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፤ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፤ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፤ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል!

መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Kezimkezia