Get Mystery Box with random crypto!

GRACE_TUBE .♥.

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥. G
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥.
የሰርጥ አድራሻ: @jesuslovingly142
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.31K
የሰርጥ መግለጫ

🗣የማይረዱህ ሰዎች ስላላዩህ ላንተ ምንም የማይፈይዱልህ ስዎች አልፈውክ ስለሄዱ ግራ ልትጋባ አይገባም ከወደክበት ልትነሳ እግዚአብሔር አንተን ለማንሳት በማን አይን መታየት እንዳለብክ የሚያውቅ ጌታ ነው!!
ቢመችህም ባይመችህም ቦታው ቦታህ ካልሆነ መነሳትህ አይቀርም!!
በመጥፎ ሰዎች ትብታብ በተናጠች ሀገር ውስጥ በጎ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጉ
share @JESUSlovingly142

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-16 20:54:03 የሆኑ ባልና ሚስት ወደ አንድ እንስሳት ማቆያ ፓርክ በአጋጣሚ ይሄዳሉ እንዳጋጣሚ አንድ ዝንጀሮ አብራው ካለች ጓደኛው ጋር እየተጫወተ የነበረ ዝንጀሮ አገኙ ።

የሰውየው ሚስት እንዲህ አለች “ምን አይነት ፍቅር ነው ! እንዲህም አይነት አለ እንዴ ? አለች በመገረም! "

ከዚያም ወዲያው ዞር ማለት እንደጀመሩ ሌላ አንድ ወንድና ሴት አንበሳ ጎን ለጎን ተለያይተው ተቀምጠው አዩና........ ሚስትየዋ “ፍቅር የሌለበት ምን አሳዛኝ ትዕይንት ነው አለች በማዘን "

ይህን የሰማው ባልተቤቷ እንዲህ አላት
“ያን ድንጋይ ወደ አንበሳይው ወርውሪና ተመልከቺ አላት ” እሷም ድንጋዩን አንበሳው ላይ ስትወረውር አንበሳው አንበሳይቱን ለመከላከል ሲጮኽ አየች

ባልየውም ከዝንጀሮዋ ጋርም ድገሚው አላት እሷም ለአንበሳው እንዳደረገችው ድንጋዩን ወደ ዝንጀሮው ስትጥል ወንዱ ዝንጀሮ ዘሎ ዛፍ ላይ ወጣና ራሱን ለማዳን ሴቷን ጥሎ ሄደ ።

ባሏም እንዲህ አላት “በምታይው ነገር አትታለይ ያየሺው ሁሉ ፍቅር አይምሰልሽ ፡፡ ብዙ ጊዜ ባዶ ልብን ለመደበቅ ሲባል የሚያታልል ገጽታ ወይም አስመሳይነት ይኖራል ፡፡

ሌሎች ደግሞ አሉ ዝምተኞች ፣ ልባቸው ግን ቅን የሆነ በአሁኑ ጊዜ ፣ እንደዝንጀሮው የሆኑ ብዙዎች አሉ ፣ ጥቂቶች ደግሞ እንደ አንበሳው የሆኑ አሉ።

share @JESUSlovingly142
173 views◦Mex Abrillo, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 20:50:02 ለህይወትህ እንደ ድል ያሉ ቃሎችን ተጠቀም ያኔ አሸናፊው አንተ ብቻ ነው እምትሆነው።

share @JESUSlovingly142
153 views◦Mex Abrillo, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 20:36:52 ‹‹አንድን ነገር የማትወደው ከሆነ ቀይረው፡፡ መቀየር ካልቻልክ አመለካከትህን ቀይር፡፡››

share @JESUSlovingly142
209 views◦Mex Abrillo, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 17:38:12 Work so hard

One day People who rejected you will search you on Google

Share @JESUSlovingly142
349 views◦Mex Abrillo, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:32:05 #ሴቶች ለሴት ጓደኞቻቹ ሼር
@JESUSlovingly142
23 views◦Mex Abrillo, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:14:37 ለእህቶቼ

በፍቅር እመኑ። ከአሥር ሰው ጋር አትጃጃሉ። በተለይ አንቺ፡ ሁሉንም ወንድ በስልክ አኩል አታስተናግጂ። ለሁሉም ወንድ ልብሽን ክፍት አድርገሽ አትጠብቂ። የምትወጂው ካለ፡ እሱን አስቀድሚ። እንደሚወድሽና ካንቺ ጋር ለመሆን እንደሚፈልግ ካረጋገጥሽ ከእሱ ጋር ቀጥይ። ከሚደውሉልሽና ከሚያወሩሽ ወንዶች መካከል ስሜት የሰጠሽ ከሌለ አጉል ግንኙነት አቁሚ።

እንዴት ሰው ትዳርን እያሰበ ከ10 ሰው ጋር ያወራል? የተስፋ ምልክት እየሰጠሽ ወንዶችን ለመጥፎ ውሳኔ አትጋቢዥያቸው። ብዙ ወንዶች የወደዱትን ብቻ ነው የሚያሳድዱት። ሴቶች ግን የሚወዱትን ለማግኘት በ 6 ወንዶች ይሰደዳሉ። አንቺ ግን መሰደድም ማሳደድም አይጠበቅብሽም። የወደድሽውን መፈለግ መብትሽ ነው። አንዱን መውደድ፣ አንዱን መምረጥ፣ አንዱን አልሞ መሞከር ያዋጣል። በንጹህ ልብ ለመውደድ ስትነሺ የፍቅር አምላክ አያሳፍርሽም። ማፍቀር መብትሽ ነው። መምረጥ መብትሽ ነው። መቆየት መብትሽ ነው። ነገር ግን ማስመሰልና ሁሉን ማስተናገድ ይጎዳሻል። ከሁሉም ያስቀርሻል። ከፍቅር ያጎልሻል።

ከተጠቀሙ ሼር ያድርጉ። ሌሎችም እንዲያደርጉኝ Invite ያድርጉ። መልዕክቶቼ ለብዙ ሰው እንዲደርስ እፈልጋለሁ።

share @JESUSlovingly142
74 views◦Mex Abrillo, edited  11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 21:38:02 ህይወት አጭር ናት ተጨንቀህ አታሳጥራት በትናንት ተፀፅተህ አታባክናት በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ የሰማይ ወፎችን የሚመግብ እግዚአብሔር ላንተ ያለውን አይከለክልም ትንሽ ታገስ በቅንነት ጠይቀው ፈፃሚው እርሱ እግዚአብሔር ነው።

share @JESUSlovingly142
275 views◦Mex Abrillo, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 00:13:14 አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው?  አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን አምላክ ይዘንላቸው።

share @JESUSlovingly142
680 views◦Mex Abrillo, 21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 18:59:18 || የበቀል ሁሉ ትልቁ በቀል ከእነሱ ዉጪ መኖር የማትችል የሚመስላቸውን ሰዎች እነሱ ከሄዱ በኃላ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንክ ማሳየት ነዉ።

Share @JESUSlovingly142
349 views◦Mex Abrillo, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 17:48:17 በህይወታችን አንድ አንድ ቀናት አሉ አለልክ በደስታ የሚያስፈነጥዙን ወይም አለልክ በሀዘን ስሜት ልባችንን የሚሰብሩ ግን በነዚህ ሁነቶች መሀከል ያለው አንድነት ሁለቱም አላፊ መሆናቸው ነው፡፡

#ደስታም ቢሆን ያልፋል
#ሀዘንም ቢሆን ያልፋል!!

share @JESUSlovingly142
426 views◦Mex Abrillo, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ