Get Mystery Box with random crypto!

GRACE_TUBE .♥.

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥. G
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥.
የሰርጥ አድራሻ: @jesuslovingly142
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.31K
የሰርጥ መግለጫ

🗣የማይረዱህ ሰዎች ስላላዩህ ላንተ ምንም የማይፈይዱልህ ስዎች አልፈውክ ስለሄዱ ግራ ልትጋባ አይገባም ከወደክበት ልትነሳ እግዚአብሔር አንተን ለማንሳት በማን አይን መታየት እንዳለብክ የሚያውቅ ጌታ ነው!!
ቢመችህም ባይመችህም ቦታው ቦታህ ካልሆነ መነሳትህ አይቀርም!!
በመጥፎ ሰዎች ትብታብ በተናጠች ሀገር ውስጥ በጎ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጉ
share @JESUSlovingly142

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-05 23:44:08 No matter How depressed I am I always smile back to the people who smiles at me.

Share @JESUSlovingly142
553 views◦Mex Abrillo, edited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 23:36:56 ||የምትኖረው አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ ከኖርክ በቂ ነዉና ህይወትህን ዉብ እና ማራኪ አድርጋት!

  @JESUSlovingly142
566 views◦Mex Abrillo, edited  20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 17:16:35 *አመስግነው *
አንድ ስጋ የምትጠብስ ሴት ስጋውን መጥበሻው ላይ ትጥድና ታገላብጠዋለች ። ከዛ መብሰል አለመብሰሉን በሹካ ወጋ ወጋ አድርጋ  ታየዋለች ። ከበሰለ ታወርድና ለመዓድ ገበታ ላይ ታቀርበዋለች።

ፈጣሪም እኛን እውቀት ይሰጡናል ያበስሉናል ብሎ ባሰባቸው በተለያዩ ነገሮች ላይ ይጥደንና  ፍቅረኛ ማጣት ፣ ስራ ማጣት ፣ ገንዘብ ማጣት ... በተባሉ ሹካዎች ወጋ ወጋ አድርጎ መብሰል አለመብሰላችንን ያረጋግጣል። ችግር  ውስጥ ሆነን ካመሰገንን በስለናል ካማረርን ግን ይቀረናልና በተለያዩ ችግር ውስጥ ጥዶ ያገላብጠናል።

1 ካሜራ ማን እኛን ፎቶ ከማንሳቱ በፊት ፈገግ በል ቀና በል ትንሽ ወደ ቀኝ ምናምን እያለ ያስተካክለናል ከዛ ያነሳናል።

ፈጣሪም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን ሚያስተካክለው። መከራ ፈጣሪ እኛን ወደሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። ዳይመንድን ውድ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ አቆራረጡ ነው ። ዳይመንድን የምናውቀውን ቅርፁን ያስያዘውና ከተለያየ አቅጣጫ እንዲያንፀባርቅ ያደረገው አቆራረጡ ነው።

እኛንም ዛሬ እየቆረጡንና እያማረርንባቸው ያሉ ችግሮች ነገ እኛን ዉድና የሚያበራ ማንነት ባለቤት የሚያደርጉን ናቸው ። ማዕበል ሲነሳና ባህሩን ሲያማስለው ሁሉም እንስሶች ይሸሻሉ። ኤግል ግን በመሀሉ ገብቶ አሳ ይዞ ይወጣል ።

ወዳጄ eagle በችግር  ውስጥ እራስህን አንፅ። ሸክላ የምትሰራ ሴት እንኳን ሸክላዋን ሰርታ ስትጨርስ እንዲጠነክርላት በእሳት ነው ምትጠብሰው ። ዛሬ የሚጠብሱህ ችግሮች ማንነትህን ነው  የሚያጠነክሩልህ  ። ስለዚህ ስለሆነው ስለሚሆነው እየሆነ ስላለው ፣ ስለተደረግልህ ስላልተደረገልህ ፣ ስለ ሰጠህ ስለ ነፈገህ ነገር ሁሉ እሱን አመስገነው ። እንዲ በለው " ደስታንም  ሆነ መከራን ብትሰጠው ከኔ ይልቅ ለኔ አንተ ነህ ምትቀርበው " ለወዳጅዎ ሼር ያርጉላቸው

share @JESUSlovingly142
423 views◦Mex Abrillo, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 01:26:50 የሆነ ጊዜ ላይ መድሀኒት መፈለግ ታቆማለህ ድነህ ሳይሆን ህመሙን ለምደከው ነው

ደስተኛ ሆነክ ሳይሆን በሰባራ ልብ እንዴት መኖር እንደሚቻል ልምድ አስተምሮህ በዙሪያህ ያለው ሁሉ ያልታመመ አይደለም።ይሄን የሚወጡት ጥሩ መተወን የሚችል ብቻ ነው አንተም መጋፈጥ መቻል ከዛም መወጣት ትችላለክ።

Share @JESUSlovingly142
132 views◦Mex Abrillo, 22:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 23:25:53 መንገድህ ህልም በፈቺው

ሌባው ሌሊት ላይ አንዲት አሮጊት ቤት ዘሎ ገባ።

እሷም ኮቴውን ስትሰማ ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች።

«ልጄ ሆይ !
ይህን አስከፊ የስርቆት መንገድ እንድትመርጥ ያስገደደህ የኑሮ ሁኔታ እንጂ ስመለከትህ መልካም ሰው እንደሆንክ ያስታውቃል።
ስማ ልጄ !
እኔ በጣም ብዙ ገንዘብና ጌጣጌጥ ያለኝ ሰው ነኝ። ሀብቴን ሁሉ ይዘህ ብትሄድ አይደንቀኝም። ነገር ግን ከመሄድህ በፊት በድንጋጤ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝን ህልም እንድትፈታልኝ እፈልጋለሁ» አለችው።

ሌባውም «ይህች አሮጊት የምትናገረውን የማታውቅ ንክ ናት።
ህልሟን ሰምቼ ከፈታሁላት በኋላ ቤቷን ለቅቄ ወደ ሌላ የስርቆት ተግባሬ ብሰማራ ይሻለኛል» ብሎ ወሬዋን ማዳመጥ ጀመረ።

እሷም «በህልሜ በሆነ ትልቅ ወንዝ ዳር እየተራመድኩ እያለ ድንገት እግሮቼ ተንሸራተው ወንዙ ውስጥ ወደቅሁ።
ልክ እንደዚህ ድምጼን ከፍ አድርጌ በጣም እየጮህኩ "ኧረ ጀማማማል እርዳኝ !" ብዬ በተደጋጋሚ ተጣራሁ።
"ኧረ ጀማል እባክህን ቶሎ ውረድ" በማለት በድጋሜ ጮሁኩ»  አለችው።

ሌባውም «ለመሆኑ አሁን እንዲህ እየጮህሽ የጠራሽውን ጀማል ታውቂዋለሽ ?» ብሎ ከመጠየቁ የአሮጊቷ ልጅ ጀማል ከአንደኛው ፎቅ ላይ ሽመሉን ይዞ ከተፍ አለ።
በያዘው ሽመል የሌባውን ወገብ እንደ ገብስ ይፈትገው ገባ።
አሮጊቷም «ጀማልዬ በእጅህ እንዳይሞት በዚህ መጠን ከወቃኸው ይበቃል» አለች

ሌባው ምን ቢል ጥሩ ነው ...

«እኔ ማለት ሙቀጫ ውስጥ እንደገባ ቡና መወቀጥ የሚገባኝ ሰው ነኝ። ጀማል እባክህ ደህና አድርገህ ውቀጠኝ። አሁን እኔ ሌባ ነኝ ወይስ ህልም ፈቺ ??? እኔን ብሎ ህልም ፈቺ !! ጀማል አደራ ሳታቋርጥ ደህና አድርገህ ውቀጠኝ» አለው


ምጥን አስተምህሮ

አላማህን ከግብ ለማድረስ ግስጋሴህን የሚያሰናክሉ ነገሮች ላይ የጎላ ትኩረት ከመስጠት ተቆጠብ። ግብህን ለመምታት በምታደርገው እንቅስቃሴ ቀዳሚ ባልሆኑ ጉዳዮች ትኩረትህ የሚሰለብ ከሆነ መዳረሻህ ሳትደርስ ትሰበራለህ ! በእያንዳንዱ ተግባርህ አስተውል

Share @JESUSlovingly142
222 views◦Mex Abrillo, edited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 23:20:10 በሰላሳ

ጋሽ ስብሃት  አንዴ   የሆነ ሞል ውስጥ ብዙሀኑ ቤት ውስጥ ተሰቅሎ ያለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ብለው የሚሸጡትን የ ቦሊውድ አክተሩን ምስል ለሽያጭ ተሰቅሎ ያያሉ። ወደ ሻጩ  ጠጋ ብለው

"ስንት ነው?"  ብለው ጠየቁ?

ሻጭ  "3 ሺህ ብር"

ፈገግ አሉ ጋሽ ስብሃት።
 
ሻጭ  የተወደደባቸው ስለመሰለው ጋሼ ለእርሶ አስተያየት ይደረጋል።  በስንት ይወስዳሉ?

ጋሽ ስብሃት  "ይሁዳ ከነ  ነፍሱ 30 ብር አይደል እንዴ የሸጠው? እንዴት ለስዕል 3 ሺህ?"

Share @JESUSlovingly142
391 views◦Mex Abrillo, edited  20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 22:49:10 ረግተህ እስክትቆም በጎርባጣው ትፈተናለህ! በጎርባጣው መፈተንህ ደግሞ ምቹውን ለማግኘት ዋጋ ከፋይ መሆን እንደሚያስፈልግ ያስተምርሃል!!!

        #ጎርባጣው ላይ ላሉት ሁሌም እጅህን ችራቸው ምን አልባት የነርሱ ምቹ አንተ ልትሆን አልያም ልትመራቸው ትችል ይሆናል!!!

 share @JESUSlovingly142
439 views◦Mex Abrillo, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:10:19 °ሰውን በሰዋዊነት°

#ሰው ከስተቱ ይማራል፤ ከቆሻሻው ታጥቦ ይፀዳል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች መቼም ቢሆን አብሯቸው ካደገ ማንነት የፀዱ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተለውጠዋል ብለን ዳግም ዕድል ስንሰጣቸው ልክ  ቦታና ምቹ ጊዜን ጠብቀው ዳግም ልባችንን ያቆስሉታል፤ መጠገን እንዳንችል አርገው ይሰባብሩናል፡፡ ስለዚህ  በእነዚህ አይነት ሰዎች ስንከበብ ሁሌም  ንቁና ጠንቃቃ እንሁን  ። ብቻ ወንድሜ
☞ ፈጣሪ ይምርሃል የማይምርህ የሰው ልጅ ብቻ ነው። ፈጣሪ እኮ ይቅር በለኝ ስትለው ከነበርክበት የዘቀጠ ህይወት አፅድቶ ወደ እርሱ ያቀርብሃል። የሰው ልጅ ግን ከባድ ነው። ዛሬ ጥሩ ስትሆን ለማስመሰል ነው ይልሃል...ክፉ ከሆንክ የለመደው ነው ይልሃል። ላጠፋኸው ጥፋት ይቅርታውን ስትጠይቀው ባለፈ ማንነትህ ያሸማቅቅሃል!!
ፈጣሪ መልካምነትን በውስጣችን ያኑርልን። አሜን!!!

መልካሙን_ሁሉ_የምናስብበት_የምናደርግበት_የምንሰማበት_ጊዜ ይሁን

Share @JESUSlovingly142
806 views◦Mex Abrillo, edited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 22:26:27 ሳንማርበት ቀርተን ነው እንጂ
ሳያስተምረን የሚያልፍ ቀን የለም

Share @JESUSlovingly142
434 views◦Mex Abrillo, edited  19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:05:19 || በነፍስሽ ተማመኚ!

የሆነ ነገር ለምን እንደ ተከሰተ ለመረዳት በመሞከር ራስሽን እንደ እብድ ማሽከርከርሽን አቁሚ እና የተከናወነው ነገር ሁሉ ነፍስሽ ማድረግ የፈለገው ነገር እንደሆነ ብቻ ተማመኚ!

       
  @JESUSlovingly142
257 views◦Mex Abrillo, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ