Get Mystery Box with random crypto!

GRACE_TUBE .♥.

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥. G
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥.
የሰርጥ አድራሻ: @jesuslovingly142
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.31K
የሰርጥ መግለጫ

🗣የማይረዱህ ሰዎች ስላላዩህ ላንተ ምንም የማይፈይዱልህ ስዎች አልፈውክ ስለሄዱ ግራ ልትጋባ አይገባም ከወደክበት ልትነሳ እግዚአብሔር አንተን ለማንሳት በማን አይን መታየት እንዳለብክ የሚያውቅ ጌታ ነው!!
ቢመችህም ባይመችህም ቦታው ቦታህ ካልሆነ መነሳትህ አይቀርም!!
በመጥፎ ሰዎች ትብታብ በተናጠች ሀገር ውስጥ በጎ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጉ
share @JESUSlovingly142

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-27 17:43:06 በህይወት እስካለህ ፊልም ታያለህ፡፡ህይወት ግን ፊልም አይደለችም፡፡ አንድ የፊልም ተዋናይ በሰባት ፊልም ላይ ሰባት ሴት ሊወድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰባት ፊልም ስለሰራ፡፡ አንተ ግን አንድ ህይወት ነው ያለክ፡፡ አንድ የ3 መኖር እድል ደጋግመክ መኖር አትችልም፡፡ህይወት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ያለህን አንድ እድል በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡"

share @JESUSlovingly142
437 views◦Mex Abrillo, edited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 11:55:10 አናውራ ነገር ለሰሚው አይገባው አንፅፈው ወዲ ከቃል አይግባባ
ወጌሻ አያሽለን አይለይ ስብራቱ
ሀኪም አያክመው የለም መድሀኒቱ እንዲው የምንገፋው እያልን ደና ነኝ አንዳንድ ህመም አለ ስንሞት የሚሻለን::

@JESUSlovingly142
763 views◦Mex Abrillo, 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 22:11:01
           ወዳጄ የአልጋ ልብስን ከበላያችን ለብሰን ምንተኛው እኮ ለምቾት ፤ ለጤና በመጨነቅ ነው እንጂ እንቅልፍ እኮ ተራቁተንም አናጣውም። ሰው መሆናችንም ካለ ልባስ ከሰው ዘንድ ያኖረናል፤ ግን የአስተሳሰባችን ልዕልና ሊጨምርና በነገራቶች ላይ መልካም አስተሳሰብ ፤ መልካም እይታ ፤ አመዛዛኝ እና ብሱል ስብዕና……ሲኖረን በተሻለ ምቾት/ተግባቦት ከማህበረሰቡ ጋር የመኖርን እድል እናገኛለን!!!

   share @JESUSlovingly142
445 views◦Mex Abrillo, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 13:48:36 ፍቅር ካለ ክህደት
መኖር ካለ መሞት
ማግኘት ካለ ማጣት
መጥገብ ካለ መራብ
ሀብት ካለ መደህየት
ቀን ካለ ጨለማ ይች አለም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ጥርቅም ነች
ሁሉም አላፊ ጠፊ ነውና ጠንካራ ሁን።

share @JESUSlovingly142
275 views◦Mex Abrillo, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 18:34:50 እንኳን ገፋቹኝ እንኳንም ጣላቹኝ ውድቆ
መቆምን ደግ አስተማርቹኝ ልኬን መጠኔን እንዳውቅ ያረጋቹኝ
እዳቅ መገፋቴ ነው ያንጊዜ ስናቅ እናንተ ንቃቹኝ
ስትተዉኝ ነው የሚያከብሩኝ ነው ጎኔ ያገኘውት
ለካስ አንዳዴ መገፋት መጣል መጥፎን አሽሾ ጥሩ ያመጣል አንዳንዴ ከቀረቡን ሰዎች መራቅ ህይወትን ሊባርክ ይችላል ብዙ ማዘን አያስፈልግም::

Share @JESUSlovingly142
580 views◦Mex Abrillo, edited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 12:05:35 እስከ መጨረሻው መውደድ

“በተቀየረብህ ሰው ምክንያት የሀዘን ኑሮ አትደግፉ ፣ ይህ ሰው ማስመሰሉ ደክሞት ወደ እውነተኛ ማንነቱ ተመልሷልና” የሚል አንድ አባባል ሰምቻለሁ።

የከዱን የሚመስሉን ሰዎች አብረውን የነበረ ቀን ነው የከዱን ፣ አሁን ግን ጊዜያችሁን አላባክንም ብለው ሄደዋልና ታማኝ የሆኑት ዛሬ ነው ። ብዙ ዘመን ከእኛ ጋር የኖሩት በጭምብል ተሸሽገው ነው፣
አሁን ግን መሸፈኛውን አውልቀው ገስግሰዋል ።

እስከ ዛሬ ሕመም አልባ በሽታ ነበሩ ፣ ዛሬ የሚጠዘጥዝ በሽታ ሆነዋል ።

እስከ ዛሬ ሌሎችን እያባረሩ እነርሱ ብቻ አጠገባችን ነበሩ ፣ አሁን ግን ራሳቸውንና መሰላቸውን ይዘው ሄደዋል ።

እስከ ዛሬ ድረስ አብረውን የሌሉትን አሉ እያልን እንታለል ነበር ፣ አሁን ሄደዋልና የሌለንን ነገር በትክክል አውቀናል ።

አስመሳዮች ከአጠገባችን የሄዱ ቀን ዳግም እንደ ተወለደ ሰው ዓይናችን ተገልጦአል ። እያየን የማናይ ነበርና አሁን ግን አጥርተን አይተናል ።

በሌለን ሺህ ከመዝለል ፣ በሌለን ምንም መጸለይ ይሻላል ። አሉ ብለን ከአምልኮ ያራቁን ሲሄዱ የለኝም ብለን እንድንጸልይ ያደርጉናል ።

አስመሳዮች ከአጠገባችን የሄዱ ቀን ጠባያቸው ተገለጠ እንጂ ያን ቀን ማስመሰል ጀመሩ ማለት አይደለም ። አጠገባችን ሳሉ አናያቸውም ፣ በሩቅ ያሉ ግን አልሰሜን ግባ በለው እያሉ ለእኛ ያዝኑልን ነበር ፤ ሲርቁን ግን ትክክለኛ ማንነታቸውን አየን ።

ሰዎች የከዱን ቀን መዘመር ፣ አስመሳዮች የሄዱ ቀን መሸለም ይገባናል ። ለሐሰተኛ ማንነታቸው ስንመጸውት ኑረን ለእውነተኛ ማንነታቸው መናደድ አይገባንም ።

የሰጡን ማደንዘዣ እስከ ነገ እንደሚበቃ እያወቁ ዛሬ በመሄዳቸው ጊዜያችን አትርፈዋል ፣ የዓይናችንን ብዥታ አሳውቀውናልና ልናመሰግናቸው ይገባል ።

አንድ ሰው፡- “ብዙዎች መጥተው ብዙዎች ሄደዋል ፣ አንድ ግን ቀርቷል” ብሏል ። እናንተስ የቀረላችሁ አንድ ማን ይሆን


Share @JESUSlovingly142
701 views◦Mex Abrillo, edited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 08:36:58 ||የአንድ ሰው ተወዳጅ በጉ ወደ ጥልቅ ገደል ይወድቅበታል፡፡ እሱ ምንም ያህል ቢሞክርም በፍፁም ሊያወጣዉ አልቻለም፡፡

ሰዉየዉም ግራ ይጋባል አማራጭም ያጣል ጥሎት ቢሄድ የጅብ እራት እንደሚሆን ያዉቃል ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ በሕይወት ለመቅበር ይወስናል።

በእንባ እየተራወጠ አፈር ከላይ ወደ በጉ ማፍሰስ ጀመረ፡፡ በጉም ሸክም ይሰማዋል ከዛን አርገፍግፎ በእግሩ ይረጋግጠዋል። ሰዉየዉ እንባዉ ሊቆምለት አልቻለም ተጨማሪ አፈር ማፍሰሱን ይቀጥላል፡፡ በጉም በዛዉ ልክ ሸክሙን እያርገፈገፈ በእግሩ መረጋገጡን ይቀጥላል፡፡ ሰዉየዉም ለመቅበር ጭነቱን በጨመረ ቁጥር በጉ በመረጋገጥ ደረጃዉን ከፍ እያደረገ ይሄዳል፡፡ ወደ ምሽት ላይ በጉ በማይታመን ሁኔታ አረንጓዴ የግጦሽ መሬት ላይ አረፈ።

ታሪኩን ወደ እራሳችን ችግር ቀየር አድርገን እንመልከተው!

Share @JESUSlovingly142
682 views◦Mex Abrillo, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 20:33:22 ባለትዳሮች ወደ መኝታቸው እያመሩ ነው፡፡ በድንገት ባልየው ከቤታቸው ጀርባ ያለውን አትክልት ቤት መብራት
እንዳላጠፋው ትዝ አለውና ተነስቶ ወደዛ አመራ፡፡

ነገር ግን አትክልት ቤቱ ውስጥ ሶስት ሌቦች ሰብረው ገብተው ተመለከተ፡፡

ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ እርዳታ ጠየቀ፡፡ ኦፊሰሩም "አሁን ሁሉም
ፖሊሶች ለስራ ወጥተዋል፤ ምንም ፖሊስ የለም፡፡ እንደተመለሱ
እልክልሀለው" አለ፡፡
ሰውዬው በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ከ ተወሰኑ ደቂቆች በሗላ መልሶ ደወለ፡፡

"አታስብ ኦፊሰር፤ ሶስቱንም ሌቦች ገደዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው፤ ምንም ፖሊስ መላክ አይጠበቅብሕም" አለው፡፡

ብዙም ሳይቆይ በሶስት የፖሊስ መኪና የታጨቁ ከ10 የሚበልጡ ፖሊሶች የሰውዬውን መኖሪያ ቤት ከበቡት፡፡ ኦፊሰሩም አብሮ ነበረ፡፡ ነገር ግን ሌቦቹ እንደተባለው ተገለው ተቆራርጠው ለውሻ ተሰጥተው ሳይሆን ከእነነፍሳቸው ሲሰርቁ ተያዙ፡፡

ኦፊሰር ፡- "ገድዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው ያልክ መስሎኝ"

ሰውዬው ፡- "አንተም አሁን ምንም ፖሊስ የለም፤ ሁሉም ስራ ወጥተዋል ያልክ መስሎኝ" አለው፡፡

#ጭብጥ :- ብዙ ግዜ አብዛኞቹ በህይወታችን ያሉ ሰዎች እኛ ስንፈልጋቸው
አናገኛቸውም፤ ነገር ግን በእኛ የውድቀት እና የመከራ ወቅት ያዘኑ መስለው ለማፌዝና ወደ ጥልቁ ስንወርድ ከንፈር ለመምጠጥ በዙሪያችን ይሰበሰባሉ፡፡
ታሞ አንድ ብርጭቆ ውሃ ያልሰጠነውን ሰው ሲሞት አፈር ለመጫንና
ንፍሮውን እየበላን "እንዲህ ነበር እሱ" እያልን የውሸት ድርሰታችን ለማንበብ አንጣደፍ፡፡

እውነት የምንላቸውን ሰዎች ከወደድናቸው፤ ስለ እነሱ የምናስብ ከሆነ ሰው በሚያስፈልጋቸው ወቅት ከጎናቸው እንሁን።

Share @JESUSlovingly142
590 views◦Mex Abrillo, edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 19:29:46 አንዳንድ ነገሮች ሲበለሻሹ ምነዉ 'በእልሜ" በሆነ እዉነታሁ  ሌላ በሆን ብለን እናልማለን "እልመኞች" ግን ሕይወት ከእዉነታዉ ጋር ፊት ለፊት ታጋፍጠናለች ቆይ ሰዉ ከራሡ ወዴት ይሸሻል…………!


ብቻ በዚ አለም ተስፋ ያረጉት ነገር ማጣት በጣም ከባድ ነዉ ግን የበለጠ ህመም የሆነሁ አማራጭ ማጣት ነዉ።
ልክ እኛ እንደፈለግነዉ ሁሉም ነገር ቢሆን ለአንድ ደቂቃ ጊዜ አላባክንም ነበር።

ማንም የ'ልብክን'ሕመም አያይልክም ለራሥ ትኩሳቱን ትሞቀዋለክ እንጂ አንተ ባንተ ውስጥ የምትኖር ብቸኛው ሰው ነክና።

Share @JESUSlovingly142
593 views◦Mex Abrillo, edited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 02:01:33 የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ!ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡

ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡
ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡

ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ!ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል?ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡
ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ!እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡

ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!”
በሚቀጥለውቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን – 20 ሚሊየን ብቻ!በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?”ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?

i(Africa’selites are lords of poverty!ያለው ማን ነበር?)
የማናጀሩፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው?የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ከወቅቱ ጋር ላይሄድ ይችላል ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ፡፡

share @JESUSlovingly142
159 views◦Mex Abrillo, 23:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ