Get Mystery Box with random crypto!

GRACE_TUBE .♥.

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥. G
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesuslovingly142 — GRACE_TUBE .♥.
የሰርጥ አድራሻ: @jesuslovingly142
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.31K
የሰርጥ መግለጫ

🗣የማይረዱህ ሰዎች ስላላዩህ ላንተ ምንም የማይፈይዱልህ ስዎች አልፈውክ ስለሄዱ ግራ ልትጋባ አይገባም ከወደክበት ልትነሳ እግዚአብሔር አንተን ለማንሳት በማን አይን መታየት እንዳለብክ የሚያውቅ ጌታ ነው!!
ቢመችህም ባይመችህም ቦታው ቦታህ ካልሆነ መነሳትህ አይቀርም!!
በመጥፎ ሰዎች ትብታብ በተናጠች ሀገር ውስጥ በጎ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጉ
share @JESUSlovingly142

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-12 12:17:59 ልባዊ ፈገግታ የሰዎችን ልብ ይከፍታል ለሰው ልጅ ያለህን አክብሮት የምትገልፅበት አለም አቀፋዊ ቋንቋም ነው።ፈገግ በል

Share @JESUSlovingly142
561 views◦Mex Abrillo, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 12:14:16 አንዳንዴኮ በራሴ ቅንነት እራሱ እቀናለሁ

Share @JESUSlovingly142
565 views◦Mex Abrillo, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:43:38 ከ ፕሮሞሽን ውጪ ስለፈለጋቹት እርስ ልታወሩኝ ትችላለቹ አለሁ @Abrish_03
343 views◦Mex Abrillo, edited  19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:07:54 ተስፋ አትቁረጡ ትልቅ እና የተሻለ ነገር ጊዜ ይወስዳል::

Share @JESUSlovingly142
418 views◦Mex Abrillo, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:54:36 በከንቱ አትጨነቅ!
አንዳንዴ አንተ ስለተጨነክ ብቻ የማትቀይራቸው ነገሮች አሉ፤ ሸክላው ራሱን ከሚያውቀው በላይ ጠፍጥፎ የሰራው ሸክላ ሰሪው ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ ካንተ በላይ የሚያውቅህና የሚያስብልህ አምላክ አለህ! በከንቱ መጨነቅ አቁም!


Share @JESUSlovingly142
605 views◦Mex Abrillo, 14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 17:29:59 ዋጋ ያለህ ሠው ለመሆን ሞክር እንጂ ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር፡፡

Share @JESUSlovingly142
627 views◦Mex Abrillo, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 22:32:20 መከራችሁን አትጥሉት ስቃያቹን አትጥሉት ምክኒያቱም ወዴት እየወሰዳችሁ እንደሆነ ስለማታቁት ወዴት መስመር እያመጣቹ እንደሆነ ስለማታቁት። በስቃያችን እሪሪሪሪ እያልን ያለን ሰዎች ደሞ ሌሎች ሰዎች በምን ውስጥ እንዳሉ አናቅም ግን!

እልሀለሁኝ እኔይ የትናንት መከራ የዛሬ መከራ አይደለም የትናንት ቆሻሻ ማንነት የዛሬ ማንነት አይደለም በየቀኑ ከነቃን ከተነፈስን አዳዲስ እድል ይሰጠናል። 
ማንም ያሰበውን ህይወት የሚኖር የለም ሁላችንም ባልታሰበው ህይወት ነው እየኖርን ያለነው''ማነው ያሰበውን ህይወት ለመኖር መጨረሻው ድረስ የተጓዘው?'' ሁላቹም እራሳቹን ጠይቁ???

Share @JESUSlovingly142
480 views◦Mex Abrillo, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 17:07:52 አንዳንዴ ፍላጎት ያጣብህን ሰው አንተን እንዲፈልግ  ለማድረግ የምታባክነውን አቅም እና ጊዜ ሌላ አልምደህ ጥሩ ወዳጅነት ትመሰርትበታለህ!

በቃ ቀላል ባይሆንም የሄደውን ለመንገዱ ተወው ያኔ እኮ አንተም ሰላምህን ታገኛለህ!!!

    ምን ተረዳሁ መሰለክ አለሁልክ ያሉክ በጉድለትክ አልያም በሌላም ብቻ በሆነ ምክንያት ይተዉካል

እወድሀለሁኝ የሚሉክ በጊዜ ሂደት ፍቅራቸው ይጠፋል ወይንም በሌላ ሰው በሌላ ነገር ይተኩታል

ያላንተ ያሉህ ካንተ ውጪ ብዙ ከብዙኦች ጋር ይከውኑታል

ያንተ ብቻ ነኝ እስከመጨረሻው ያሉህ የብዙሁኦች ሆነው ታገኛቸዋለህ

በጣም ደግሞ የሚገርመጥ ታስፈልገኛለህ ይሉህና ባንተ መኖር እንዲኖሩ አንተን አሳልፈህ ስትሰጣቸው ደስታህን ምቾትህን ለነሱ ደስታና ለነሱ መቆም የተሻለ እንዲሆኑ በሚል ሁሉህን ትተህላቸው ባንተ እነሱ ይቆሙና በሚገርም ሁኔታ ወረተኞች ይሆናሉ ይቀየሩብካል መነሻቸውን ዋጋህን ያቀሉታል

የሀገሬ ልጅ ዛሬ ላይ በዚች ከንቱ አለም እነዚህ ነገሮች ምድር ላይ እስካለህ ድረስ ይቀጥላል አይቆምም እንዳይገጥምህም ማድረግ ይቻላል እምትጎዳው ግን አንተ ነክ ልሽሽ ልራቅ ብትል አይሆንም ነጥብ ጥለህ እነሱንም ሆነክ ታገኘው ይሆናል

የተሻለ እሚሆነው ህይወትህን ውደዳት ህይወትህን ኑር ማንንም አትጠብቅ ማንንም አታሳድ አንተ ባንተ ውስጥ የምትኖር ብቸኛው ሰው ነክ ራስክን አክብረው

በመጥፎ ሰዎች ትብታብ በተናጠችበት አለም ውስጥ በጎ ሰዎች አሉ ይሄን አትርሳ ሁሌም ከአንተ ከቤተሰብክ ከጓደኛክ ይልቅ በፈጣሪ በእግዚአብሔር ታመን በእርሱ እርግጠኛ ሁን ፍቃዱን ጠይቅ እርሱ ሁሉን በጊዜው ውብ አድርጎ ያዘጋጅልሀል

#አንተ ግን ማንንም አታስከፋ አታስቀይም ነጥቀህ እና በሌላው እንባ የራስህን አትገንባ ያለ ምንም ምክንያት መልካም ሰው ሁን ደግሞም ራስክ አክብር ህይወትህን ውደደው ህይወትህን ኑር ሌላው ለእግዚአብሔር ተወው።

Share @JESUSlovingly142
663 views◦Mex Abrillo, edited  14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 16:10:19 አንድ ምሽት ላይ ልክ ባለሱቁ ሱቁን ከመዝጋቱ በፊት አንድ ውሻ ወደ ሱቁ ይገባል። ውሻው በአፉ ዘምቢል ይዟል። ዘምቢሉ ውስጥ የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር እና ገንዘብ ተቀምጧል። ባለሱቁ ገንዘቡን ወስዶ እቃዎቹን በዘምቢሉ ውስጥ ያኖረዋል። ወዲያውኑ ውሻው ዘምቢሉን ይዞ ይሄዳል።

ባለሱቁ ስለገረመው የውሻው ባለቤት ማን እንደሆነ ለማወቅ ውሻውን ይከተለዋል።ውሻው ከአውቶብስ ፌርሜታ ቆሞ ይጠብቃል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ አንድ አውቶብስ ሲመጣ ውሻው አውቶብሱ ውስጥ ይገባል። ትኬት ቆራጩ እንደመጣ ወደፊት ጠጋ አለ የአንገት ቀበቶው ላይ ያለውን ገንዘብና አድራሻ ለማሳየት። ትኬት ቆራጩም ገንዘቡን ወስዶ ትኬቱን በአንገት ቀበቶው ውስጥ ያኖርለታል። የሚወርድበት ቦታ ሲደርስ ወደፊት ቀረብ ብሎ ጭራውን ያወዛውዛል መውረድ እንደሚፈልግ ለማመልከት። አውቶብሱ እንደቆመለትም ይወርዳል። ባለሱቁ እስከአሁን እየተከተለው ነበር።

ውሻው ከአንድ ቤት ደርሶ በሩን በእግሮቹ ያንኳኳል። ባለቤቱ ከውስጥ ወጥቶ ውሻውን በዱላ ይመታዋል። በዚህ ግዜ ባለሱቁ ተናዶ " ውሻውን ለምንድነው የምትመታው?" ብሎ ይጠይቀዋል። ባለቤቱም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል። "ከእንቅልፌ ቀስቅሶኛል። ቁልፉን ይዞ መሄድ ነበረበት።"

#ይህ የህይወት እውነት ነው።

ሰዎች ለአንተ የሚሰጡት ግምት ማብቂያ የለውም። ከዚህ በፊት የሰራሃቸው ጥሩ ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ። ትንሿ ስህተትህ ጎልታ ትወጣለች። ይህ የዚህ ቁሳዊ ዓለም ተፈጥሯዊ ገጽታ ነው በሚፈጠሩበህ እና በሚሰጡህ ግምት አትገረም ዝም ብለህ ህይወትህን ኑር።

Share @JESUSlovingly142
622 views◦Mex Abrillo, edited  13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 23:24:51 >አስተዋይ
>ቅን
>መልካም
>ደስተኛ
>ሩህሩህ
>ደግ ይሁኑ።

ከዚህ በላይ ምን ዉጤታማነት አለ?

  @JESUSlovingly142
416 views◦Mex Abrillo, 20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ