2022-07-28 20:58:41
የኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃጂ ኢብሳ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ፡፡
አቶ ሃጂ ኢብሳ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ም/ፕሬዝደንቶች እንዲሁም የግንባታ ፕሮጀክት ባለሙያዎች በተገኙበት እየተከናወኑ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) ስለ ዩኒቨርሲቲው ገፅታ አጭር ገለፃ በማድረግ በ2014 ዓ.ም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አፈፃፀም አቅርበዋል፡፡
አቶ ሃጂ በቀረበው ገለፃ እና ባደረጉት ጉብኝት በዩኒቨርሲቲው ሥራ አፈፃፀም መደሰታቸውን በመግለፅ በቀጣይም ኤጀንሲው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲውም ከዋና መስሪያ ቤቱ እየተደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና የሚሆን የአካባቢውን ባህል የሚገልፅ የጋቢና ጭራ ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ በጉብኝቱ ለተሳተፉት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀጃው ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ለተጨማሪ መረጃ የሚከተሉትን የመረጃ መረቦች ይጠቀሙ!
ለቴሌግራም-https://t.me/injiuniversity
ለኢንስታግራም -https://www.instagram.com/injibara12
ለዌብ ሳይት- https://www.inu.edu.et/
ለፌስ ቡክ ገፃችን -https://www.facebook. Com/injibaruni
ለኢሜይል- injibarau@gmail.com
ለInstitution Email -injibarauniversity@inu.edu.et
ለትዊተር- Twitter (https://twitter.com/injibara_Inu/)
ለዩቱዩብ-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity
Explore Your Creative Potential.
1.9K views17:58