2022-10-06 18:30:50
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የተመደቡለትን ተማሪዎች መቀበል ጀመረ፡፡
ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!
አዲናስ!
በዛሬው እለት ከቻግኒ፣ ከጃዊ፣ ከዚገምና ጓንጓ ወረዳዎች 3,884 ተፈታኝ ተማሪዎች በሰላም ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት አዕምሮ ታደሰ (ዶ/ር) እና የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝደንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) በተማሪዎች ማደሪያ እና መመገቢያ አካባቢያ ያለውን ዝግጅት አድንቀ ተማሪዎች ግቢ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ አክብረው በመልካም ስነ ምግባር እንዲቆዩ አሳስበዋል፡፡
ተማሪዎችም በተደረገላቸው አቀባበል እና የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
መስከረም 26/2015 ዓ.ም፣ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
1.0K views15:30