Get Mystery Box with random crypto!

Injibara University

የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University I
የቴሌግራም ቻናል አርማ injiuniversity — Injibara University
የሰርጥ አድራሻ: @injiuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.73K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-11-09 18:34:21
የፌደሬሽን ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ፣ የአማራ ክልል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ፡፡
////////////////////////
በጉብኝቱ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ሲመሰረት የነበረውን የተማሪ ቅበላ አቅም እና ትምህርት የጀመረባቸውን ፕሮግራሞች፤ አሁናዊ ገጽታዎች ማለትም አረንጓዴ ልማት፣ የእንስሳት ምርምር ጣቢያ፣ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ምቹ የሥራ ከባቢ የተፈጠረባቸው የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ እና ህፃናት ማቆያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስላለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለጎብኝዎቹ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ዩኒቨርሲቲው ባከናወናቸው ተግባራት እና ባዩት ነገር መደነቃቸውን የገለጹት የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ አደረጃጀት ኃላፊ ዶ/ር አወቀ ዩኒቨርሲቲው የረጅም ጊዜ ግብ አስቀምጦ በጥራት ማህበረሰቡን ለማገልገል በሀገር ደረጃ እና ከዚያ በላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን የማድረግ ሥራ ሰርቷል ብለዋል የተሻለ አመራር እና የአካዳሚክ ስብስብ እንዳለበት የተከናወኑት ተግባራት ማሳያ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራም ከማስፈፋቱ ጋር ተያይዞ ያለው የግንባታ ፕሮጀክት ማስፋፊያና የተማሪ ቅበላ አቅም መጨመሩ፤ ከመንግስት የልማት ስትራቴጅ ፖሊሲ ጋር እንዲተሳሰር ሆኖ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች መከናወናቸው ዩኒቨርሲቲው ለሀገር በሚጠቅም መንገድ እየሠራ በመሆኑ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በጉብኝቱ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ አደረጃጀት ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር)፣ ዘሃራ ኡሞድ የፌደሬሽን ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ እና የብልጽግና ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ሌሎች የፌደራል፣ የክልል እና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም
1.8K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 20:03:05
1.8K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 20:03:04
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የተቀላቀሉ አዳዲስ መምህራን በግብርና ምርምር ሥራዎች ላይ የመስክ ጉብኝት አደረጉ፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው የተቀላቀሉ ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መምህራን በአዊ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች እየተሰሩ ያሉ የግብርና ምርምር ስራዎችን (የስንዴ፣ የአገው ድንች፣ የእንስሳት መኖ እና የባቄላ) ተመልክተዋል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና፣ ምግብ እና ዓየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ሀብታሙ አድማስ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የጉብኝቱ ዓላማ ወደ ዩኒቨርሲቲው የተቀላቀሉ ልምድ ያላቸው መምህራን በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች እየተሰሩ ያሉ የግብርና የምርምር ስራዎችን ተመልክተው ግብዓት እንዲሰጡና በቀጣይ የተሻሉ የምርምር ስራዎችን እንዲሰሩ በማሰብ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው በዳንግላ ወረዳ ጉምድሪ ቀበሌ በስንዴ፣ በአገው ድንች፣ በእንስሳት መኖ ዙሪያ፣ በባንጃ ወረዳ አካይታ ቀበሌ በስንዴ እና ቢራ ገብስ እንዲሁም በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ችባ ችባሳ ቀበሌ በባቄላ ሰብል ዙሪያ የተለያዩ ምርምሮች እየተካሄዱ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መከካል ብርሃኔ መከተ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው አዲስ ቢሆንም በርካታ አኩሪ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው የግብርና ምርምር ስራዎችም አበረታች ደረጃ ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ብርሃኔ አያይዘም በቀጣይ ምርምር ስራዎች ከእርሳቸው የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ሌላው የጉብኝቱ ተሳታፊ አማረ አለምነው (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲውን በላይ እንዳገኙት ጠቅሰው በተለያዩ ቦታዎች በርካታ የምርምር ስራዎች መጀመሩን አድንቀው ከእርሳቸው ሙያ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ጥቅምት 26/2015 ዓ.ም
1.8K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 20:00:20
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሠራተኞች በጤና ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናው ሁሉም ሴት ሠራተኞች ስለማህፀን ጫፍ ካንሰር ያላቸውን ግንዛቤ በመጨመር ለቅድመ መከላከል እና መቆጣጠር የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም
በሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) በአሁኑ ሰዓት በሴቶች ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ያለውን የማህፀን በር ካንሰር የተመለከተ ሥልጠና መዘጋጀቱ ሴት ሠራተኞች ስለበሽታው ምንነት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማሽቻሉም በላይ በሽታው ከተከሰተ በኋላ የሚያስወጣው የህክምና ወጪ ከባድ በመሆኑ ቅድመ- መከላከል ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ደብሪቱ ምናየሁም በበኩላቸው ሴቶች ለዚህ በሽታ ተጋላጭ በመሆናቸውም ስለበሽታው ምንነትና መከላከያ መንገዶች በቂ እውቅና ኖሯቸው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ሥልጠናው መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
በማህፀን በር ካንሰር ምንነትና መከላከያ መንገዶች (Prevention & Control challenges, Risk factors of cervical cancer, Prevention measures, Screening, Treatment modalities) እና መሰል ይዘቶች ላይ ዋና ትኩረቱን ያደረገው ይህ ሥልጠና በዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን በሆኑት ዳንኤል አዳነ (በክሊኒካል ሚድዋይፈሪ ረዳት ፕሮፌሰር) እና የውብ ምርት ሻረው (በክሊኒካል ሚድዋይፈሪ ረዳት ፕሮፌሰር) አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡
ለ5 ቀን የተሰጠው ሥልጠናው በስኬት ተጠናቋል፡፡፡፡
1.6K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 19:56:57
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔቱ ያለፈውን የሴኔት ስብባሳ ቃለጉባኤ ማጽደቅ፣ የ2015 ዓ.ም አካዳሚክ ካሌንደር ማጽደቅ እና የተጓዳኝ ስታፍ(adjunct Staff) መመሪያን መመልከት የሚሉት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

በዚህም መሰረት ያለፈውን ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ በሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በኩል ተዘጋጅቶ በሦስቱም ፕሮግራሞች ማለትም የቀረበውን የመደበኛ፣ የተከታታይ ትምህርት እና የክረምት መርሐ ግብር የትምህርት ካሌንደር በመመልከትና በመወያየት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በመጨረሻም በግብርና ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የተጓዳኝ ስታፍ መመሪያን በሚገባ ተመልክቶ አጽድቋል። መመሪያው በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል፡፡

ጥቅምት 25/2015 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
1.4K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 09:47:23
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ከፍተኛ ማዕረግና ልምድ ካላቸው መምህራን ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱ ዩኒቨርሲቲው የተሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት እንዲወጣ ልምድ ያላቸው መምህራን ሚና ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና ም/ፕሬዝዳንቶች በዩኒቨርሲቲው ከሚገኙ አዲስ እና ነባር ረዳት ፕሮፌሰር እና በላይ ማዕረግ ካላቸው መምህራን ጋር በመማር ማስተማር፣ በምርምርና እና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ስለዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ገፅታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የእንጅባራ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) ለአዳዲስ መምህራን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ስለ ዩኒቨርሲቲው ርዕይ፣ የትኩረት መስኮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በ2015 ዓ.ም 7 ኮሌጆች አንድ ትምህርት ቤት እና አንድ ኢንስቲቱዩት በመያዝ በመደበኛ፣ ተከታታይ ትምህርት እና በክረምት መርሐ ግብር እስከ ከ20ሺ የሚደርሱ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ “ከተባበርን እንችላለን” በሚል መርህ በጋራ ለለውጥ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አዕምሮ ታደሰ (ዶ/ር) ድህረ ምረቃን ጨምሮ በከፍተኛ ሁኔታ የትምህርት ፕሮግራም ማስፋፊያ እንደተደረገም አስታውቀዋል፡፡
የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) እንደገለጹት ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምር ስራዎች ለመሥራት ከፍተኛ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን(ዶ/ር) በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኙ መምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲፈጠርላቸው የቢሮ እና የተለያዩ አገልግሎቶች እንዲሟሉ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጥቅምት 24/2015ዓ.ም
1.2K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 09:42:31
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እና የአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተካሄደ።
መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የወርክሾፑ ዓላማ የተቋሙን ርዕይ ለማሳካት በጤናው ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ከአጋር አካላት ጋር በጋራ መሥራት ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።

በውይይት መድረኩም በአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዶ/ር ግዛቸው ይስማዉ ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዳባት ምርምር ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር ተስፋሁን ይልማ እና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሜጫ ምርምር ማዕከል አስተባባሪ በሆኑት በዶር ሙሉሰው አንዷለም አማካኝነት የውይይት መነሻ ነጥቦች፣ ስለ ሜጫ እና ዳባት የምርምር ማዕከላት ተሞክሮዎች በዝርዝር ቀርበዋል።

በቀረበው ተሞክሮ ላይ የውይይት መድረኩን የመሩት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ለከፈተው የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙያዊና ቁሳዊ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰው የውይይት መድረኩን በማዘጋጀቱም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አያይዘውም በወርክሾፑ የቀረበውን ተሞክሮ አድንቀው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲም የጤናውን ዘርፍ አንድ የትኩረት መስክ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አብርሐም አማረ የወርክሾፑ ዓላማ በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የማህበረሰቡን ችግር መሰረት አድርጎ መፍትሄ ለማበጀት የተካሄደ ዉይይት መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም የምርምር ማዕከሉ እዉን ለማድረግ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ለመስራት መታቀዱን አስረድተዋል።
ጥቅምት 22/2015፤ ባህር ዳር
1.1K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 09:35:21
ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ኃላፊዎች የአመራርነት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና በመንግስት ደንቦችና አዋጆች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ የሚጨምር መሆኑም ተገልጿል።

የሥልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) አንድ ተቋም የሚገነባው በቁሳዊና ሰብአዊ ኃብት ጥምረት በመሆኑ በተቋማችን ውስጥ ያለንን የሰው ኃብት አቅም መገንባት የተቋሙን ርዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የሰው ኃብት አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ሰራተኞች በመንግስት አዋጆች፣ ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ያላቸውን አቅም በመገንባት መብታቸውን እንዲጠይቁና ግዴታቸውን አውቀው ለህግ መከበር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ከማድረግ ባሻገር የተቋሙን ርዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች በሚገባ ተገንዝበው ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ ማስቻል ላይ ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ተገልጿል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ፣ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ 1064/2010 ፣ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ አፈፃፀም መመሪያ ጥቅምት 5/2011፣ የመንግስት ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ደንብ ቁጥር 77/1994 ፣ የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ትግበራና የአፈፃፀም ምዘና እና መሰል ይዘቶች በስፋት ተዳሰዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የሰው ኃብት ሥራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ጥላሁን እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰላም ሚኒስቴር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብራቱ ካሳ ናቸው፡፡
ጥቅምት 22/2015 ዓ.ም
976 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 15:23:44
ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ፦
3.3K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 21:25:30
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰው ኃይል ለማፍራት እና ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የጋራ ስራዎችን ለመስራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የአዊ ዞን እና መተከል አጎራባች አካባቢዎች ሰላም እንዲመለስ የህዝብ ለህዝብ መድረኮችን ማመቻቸቱ አስታውሰው ስምምነቱ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመተከል እና አካባቢው ከሚገኙ ተቋማት ጋር የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ለመስራትም በር ከፋች ሲሆን
ከስምምነቱም ባሻገር በሁለቱ ተቋማት በኩል ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) የስምምነቱን ዋና ዋና ጉዳዮች ካብራሩ በኋላ የአዊ እና መተከል አካባቢ ህዝቦች በጋራ አብረው የሚኖሩ በመሆናቸው በጤና፣ በትምህርት እና በሰላም ጉዳይ በጋራ ለመስራት ስምምነቱ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳት ሃይማኖት ዲሳሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዛሬው እለት የተደረገው የጋራ መግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዩኒቨርሲቲዎች በተሰጣቸው ተልዕኮዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በስልጠና፣ በትምህርት፣ በልማት እና በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
3.5K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ