2022-09-19 17:59:18
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር (Ethiopian Midwives association) ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር (Ethiopian Midwives association) ሁለት መቶ ሺ ብር ግምት ያላቸው ለሚድዋይፍ ሀኪሞች የተግባር ልምምድ ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ እንደ pelvic anatomy, Delivers set, States cope, Birth simulation እና መሰል ቁሳቁሶች ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ድጋፍ አድርጓል፡፡
መስከረም 9/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የክትትልና ምዘና ክፍል ኃላፊ አቶ በለጠ በልጉ ኮሌጁ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ሊገጥመው የሚችለውን የተግባር ልምምድ መሳሪያዎች እጥረት ለመቅረፍ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አብርሃም አማረ እና የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ ዳንኤል አዳነ አንድ በሚያደርግ የጋራ ንግግራቸው የተደረገላቸው ድጋፍ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር በዘርፉ ብቁ ምሩቃን ሆነው እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በጤና ተቋማት በወሊድ ወቅት በእናቶችና ህፃናት ላይ ሊደርስ የሚችለውን የከፋ ጉዳት ለመቀነስ የሚያችል ዜጋን የማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመግለፅ ለተደረገላቸው መልካም ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ለማህበሩ ምስጋናቸውን ከማቅረብ በተጨማሪ በተለይ በጤናው ዘርፍ የተግባር ተኮር ትምህርትን ለማስፋፋት የእንደዚህ ዓይነት የተግባር መሳሪያዎች ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
3.1K views14:59