2022-08-04 19:10:44
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአዋሽ ባንክ እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት አደረገ፡፡
--------------------
ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ሰራተኞችን የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከአዋሽ ባንክ ጋር ተፈራርሟል፡፡
ከአዋሽ ባንክ ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት ሠራተኞች የቤት መስሪያ እና መግዣ፣ የቤት መኪና መግዣ እና የፍጆታ ብድር ለማመቻቸት የሚያስችል መሆኑን የአዋሽ ባንክ የባህርዳር ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ መሰረት አምበሉ ተናግረዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) በበኩላቸው ከአዋሽ ባንክ ጋር የተደረገው ስምምነት የዩኒቨርሲቲውን ሠራተኞች የብድር ተጠቃሚ በማድረግ ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ምቹ የሥራ ከባቢን መፍጠር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስምምነቱ ሰራተኞችን ለማቆየት እና ለመሳብ ትርጉም እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በግብርና ምርት እና ምርታማነት፣ በደን እና አካባቢ ጥበቃ፣ በትምህርት ዘርፍ ልማት፣ ምርምር እና ስልጠና ላይ ያተኮሩ አገር በቀል እና ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ይፋ ተደርገዋል
1) በቻይና ሀገር Changsha Jiarong) Agricultural science and Technology ተቋም 2) መሰረታቸውን በካናዳ እና በአሜሪካ ያደረጉ WE Forest the Hunger Project የተሰኙ ድርጅቶች
3) መሰረቱን ካናዳ ያደረገ Partners in Education Ethiopia “Partners” የተሰኘ ድርጅት
4) Ethiopian Commodity Exchange እና
5) ሳንኪታ ልደታ ተፋሰስን ለማልማት ያለመ ከአዊ ብ/ዞን ግብርና መምሪያ ጋር ስምምነት ተደርጓል
821 views16:10