Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @gazetaw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.02K
የሰርጥ መግለጫ

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም
ኢትዮጵያዊ ሆነን —የሚያግባባ አናጣም!
ዕወቂው ዐለሜ__‼
ኢትዮጵያዊ መሆን —የውርስ እንቁጣጣ
በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ!
(ታመነ መንግስቴ_አባ ወራው)
ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል ና ጥበብ እናወጋለን!
ጀበናዋ ተጥዳለች—ስኒዎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም!
ክህሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ።
ትውልድ❤

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 20:40:52
ጋዜጠኝነት ?

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

ኮቫች እና ሮዜንቴል "የጋዜጠኝነት መሠረቶች/The Elements of Journalism" በሚሰኝ መጽሐፋቸው ገጽ 17 እንደሚሉት፦

"የጋዜጠኝነት ተቀዳሚ ሚና ለዜጎች የነፃነትና ራስን ማስተዳደሪያ መረጃ መስጠት ነው/The Primary purpose of journalism is to provide citizens with the information they need to be free and self_governing."


https://t.me/Gazetaw
483 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:40:43
የገበሬ ልጅ ነኝ
102 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:22:02
ፈጣን የሥራ ማስታወቂያ


የሥራው ዐይነት፦የስልክ ግንኙነት ሠራተኛ(ኦፕሬተር)

ብዛት፦15

የትምህርት ደረጃ፦ዲፕሎማ እና ድግሪ ይበቃል።

ጾታ፦ሴት ብቻ

ለመረጃ፦+251955350735 ላይ ደውሉ

https://t.me/Gazetaw
428 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:45:50
የልቅ ስለ ወልዲያ ከተማ ላውጋችሁ

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

በሕይወቴ የወልዲያን ያህል ጓጉቸ ያየሗት ከተማ የለችም

ታሕሳስ 10 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ዕለተ ዕሁድ ረፋድ ወደዚያች ለወራት የተዘጋች ከተማ ስንገባ የተሰማኝን ደስታ ለመረዳት ለቀጣዮቹ አንቀጾች ዕድሜ ተከተሉኝ።

ገባን።ጎንደር በር ጸጥ ብላለች።ነዳን።ፒያሳ ደረስን።"ላል"የሚባል ሆቴል ፊት ለፊት የሰው ፍቅር የጠማቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተኮልኩለዋል።

የምስል መቅረጫችንን ሲያዩ ይበልጥ ፈነደቁ።ሲበዛ ነፃ ሰዎች ናቸው።መቅረጸ ድምጼን ደቅኘ"እኒያ ቄሱ፣ቄሱ አተረፉን"የሚለውን እስላም ወሎየ ጨምሬ ብሶታቸውን ሰማሁ።

ወዲያውኑ "እኒያ ቄሱ"ወደተባሉት አባት ደብር ነዳን።እሳቸው ኪዳነ ምህረት ቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ኖረዋል።በሗላ ስሰማ ብዙዎቹን ያስተማሩባት ደብር ናት።

አጫጭር ግን ወሳኝ ጥያቄዎቸን መለሱ።አቡነ ኤርምያስ ኢትዮጵያ ሰው ፈጥራ የማይደክማት ለም ማኅጸን መሆኗን እንድረዳ የጠቀሙኝ የሕይወቴ ተዓምር ናቸው።

ከዚያም ወዲህ ወልዲያን ተመላልሸባታለሁ።

ሀጂ ያሲን የሚባሉትን የአቡነ ኤርምያስ አቻ አባትም ቃለ_መጠይቅ አድርጌያቸዋለሁ።እሳቸውም የኢትዮጵያ ተስፋ ናቸው።

ወልዲያ የጉባ ላፍቶ ተራራን ተንተርሳ የየጁ መዲና ሆና የቆመች የፍቅር ሐውልት ናት።

በአሁናዊ አቋሟ ከተማ ለማለት ባታመችም ባላት ማኀበራዊ እሴት በቅርብ ዓመታት የሰሜን ኢትዮጵያ ጸሐይ እንደምትሆን ልቤ ይነግረኛል!

እውይ

https://t.me/Gazetaw
560 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:32:23 "እኔ መከላከያ ሮጠ፣ሸሸ ብየም ወጥቶኝም አያውቅም።አሁንም አይወጣኝም።የሰራውን ገድል ስለማውቅ።ታሪክ ሰርቷል።በሚገባ ከአማራ መሬት ላይ የትኛውም ብሔር ወድቋል።" የሚለው ሳተና ፋኖ ስለ መንግስት አካላት ክፉ መናገር አይወድም።

ጀግና እና ሞት እንደተቃቀፉ ነው።ከመይሳው ካሳ እስከ በላይ ዘለቀ፣ከሰላሌው ጀግና አቢቹ እስከ አሁኑ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ድረስ ሞትን ያልናቀ ሰው አገሩን አያስከብርም።ዋርካው ስለሞት እንዲህ ይላል፦

"ፈሪ ከሞት አይድንም  ያችው ሞት ከመጣች ከሶስት ክንድ ጉድጓድ የሚድን የለም።"

"መከላከያ የብቻው እዳ የለበትም" የሚለው ምሬ ወዳጆ ስለ ሕወሓት ሰሞነኛ ማዕበል ሲናገር"እሱም በሕዝብ ማዕበል ነው እየቀለደ ያለው።እኛም በተደራጀ ኃይል አገራችንን ነፃ እናወጣለን!"

ብሏል።

የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ልጆች ጀግና ሲጠሩ ዘመነ ካሴ፣መሳፍንት ተስፉ፣እስራኤል እሸቴ ወዘተ ብለው ምሬ ወዳጆ ማለታቸው አይቀርም።እኔም ይህንን ከአልውሐ ድልድይ እስከ ሆርማት ወንዝ፣ከጉባላፍቶ ተራሮች እስከ ግራ ካሶ ተራራ እየተስፈነጠረ ትውልዱን ከጥቃት የሚታደግ ወዶ ዘማች ሕይወት የዳሰስኩበትን ዝግጅት ለጊዜው አከተምኩ።

በድል ያገናኘን
174 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:30:45
የወሎው ዋርካ ምሬ ወዳጆ

(በታመነ መንግስቴ)

አጭር ነው።ወፍራም ነው።ልባም ነው።ደግ ነው።ጀግናም ነው።

"መተኮስ እንጅ መናገር አላውቅበትም።ራስህ ቆርጠህ ቀጥለው።"የሚሉት ቃላት የእሱ ናቸው።

ከሰሞኑ የራያ ተስፋ እሱ ነው።የፋኖነት አርማ ሆኗል።ስሙ ምህረት ወዳጆ ይባላል።ሲያቆላምጡት ምሬ ወዳጆ ይሉታል።"አባ ስበር"በሚሰኝ ቅጽልም ያሞካሹታል።"ዋርካው" ዋንኛ ቅጽል መጠሪያው ነው።

ከአምስት ወራት በፊት ወሎ በኮምቦልቻ እና ደሴ መካከል ቃለ_መጠይቅ አድርጌለታለሁ።አረጎ ገደል ላይ ሆነን የአሁኑን ፈርቸ ስለ መንግስት ዝንጉነት አነሳሁበት፦

"መንግስት ዘነጋ አልዘነጋ የራሱ እቅድ ይኖረዋል።ግን ሕዝብ ራሱን ማንቃት አለበት።ዝም ብለህ ከምትሞት ታግለህ መሞት ጽድቅ ነው"አለኝ።

"የአማራ ፋኖዎች ከተማ ለከተማ እየተዘዋወሩ ሕዝብ ያስቸግራሉ ይሏችሗል" አልኩት።መልሱ ውስጥ ቁጣ አልነበረም።የነበረውን ሐብት እንዴት ጥሎ ወደ ትግል እንደተቀላቀለ፣አገር ሰላም ቢሆን ኑሮ እና አኗኗርን እንዴት እንደሚያውቅባት ነገረኝ።

ምሬ ወዳጆ ተወልዶ ያደገው በራያዎቹ መዲና ቆቦ ከተማ ነው።የራያ ሰው የፍቅሩን ያህል ጠቡ መራራ ነው።ምሬ ወዳጆም የማረካቸውን የሕወሓት ተዋጊዎች ተንከባክቦ የማስቀመጡን ያህል ምሽግ ሲሰብር ምድር ያናውጣል።

ደግሞም ፋኖው እንደ ወንድ ልጅ መታሰር መፈታትን ያውቃታል።ከዓመት በፊት ወልዲያ ታስሮ በመጋቢት ወር 2013 ዓመተ ምህረት ተፈትቷል።

እንደተፈታ በመንግስት ላይ ቂም አልያዘም።"ስለ እነርሱ ተው"ሲል ጋዜጠኛው ስለ አማራ ክልል ባለስልጣናት ሲያነሳበት በዝምታ ያሳለፈው ልባም የልቅስ መከላከያን ያደንቀዋል።
161 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:44:58
ጦርነት የሚደላው ኦሮሞ


(ታመነ መንግስቴ ነኝ)


የአሁኗ ኢትዮጵያ ማለት ከሞላ ጎደል በአህመድ ኢብን አልግሀዚ እና በዐጼ ልብነ ድንግል መካከል ተጀምሮ በዘመዶቻቸው በቀጠለው የእርስ በእርስ ጦርነት የተፈጠረችው ቅጅ ናት።

ያኔም እንደ አሁኑ የውጭ ኃይላት በኢትዮጵያ ጉዳይ ተጋብዘው ገብተው ይበጠብጡ ነበር።ፖርቱጋል ንጉሱን፣ቱርክ ኢማሙን እየረዳች ታላቂቱ አገር ኢትዮጵያ ተበልታለች።


እንዲህ ያለውን ውጥንቅጥ በአግባቡ አጥንቶ የተጠቀመው የኦሮሞ ማኅበረሰብ "ምችሌ" በሚሰኘው የዘመኑ ገዳ መሪነት ከደቡብ ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ በጎጃም እስከ ዳሞት፣በወሎ እስከ ራያ፣በጎንደር እስከ ቤተ መንግስቱ፣በሸዋ ብዙ ቦታ ደርሷል።


ሰሞነኛውን የሁለቱ ሴማዊያን(አማራ ና ትግሬ)ን ከንቱ እልህ ተጠቅሞ የት ይደርስ ይሆን?

ታሪክ ይናገረው


https://t.me/Gazetaw
513 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:57:35
አክሱም እና ትግራይ

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)


የአክሱም ሥልጣኔ መበሻሸቂያ ሲሆን እንደማየት ቀፋፊ ነገር የለም።ከሁሉም በፊት የ3ኛው ክፍለ ዘመን የፋርስ(Persia/ኢራን) ነቢይ ማኒ የሚለውን እናንብብ፦

"በዓለም ላይ አራት ትልልቅ ንግስናዎች አሉ።የመጀመሪያው የባቢሎንና የፋርስ ንግስና ነው፤ሁለተኛው የሮም ንግስና ነው፤ሶስተኛው የአክሱማዊያን ንግስና ሲሆን አራተኛው ደግሞ የቻይናዊያን ነው።"


አክሱም በዘመኗ የዓለማችን ሶስተኛዋ ልዕለ ኃያል አገር ነበረች።

ይህ ማለት ግን አሁን የአክሱም ሐውልቶች ያሉበት የትግራይ ክልል ሕዝብ ብቻ ስልጣኔን አይገልጽም።


ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በየካቲት ወር 2014 ዓመተ ምህረት ያነጋገርኳቸው ከዘጠኝ በላይ መጽሐፍትን የፃፉት መጋቤ ምስጢር ስማቸው ንጋቱ እንደሚሉት ትግራይና የአክሱም ስልጣኔ ግዴታ ሊገናኙ አይችሉም።


እንደ እሳቸው አመክንዮ የአዲስ አበባ ረጅሙ ሕንፃ የኦሮሞ ይሆን ዘንድ ግዴታ አይደለም!


https://t.me/Gazetaw
673 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:51:30 የሙዚቃን አክሊል የደፋ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ

(ታመነ መንግስቴ ነኝ_የአፍሪካ ሕዳሴ ቴሌቪዥን አገልግሎት ዘጋቢ)

ኢትዮጵያዊያን ስለዚህ ድምጸ መረዋ ዜመኛ፣ገጣሚ እና አቀንቃኝ ምንም በሚባል ደረጃ አያውቁም።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሬዲዮ፣ቴሌቪዥን ወይም ጋዜጣ ስሙን አያነሱም ወይም ሙዚቃዎቹን አይጋብዙም።


የእሱን ስም ጎግል በሚሰኘው የእውቀት ባህር ውስጥ ጽፎ የፈለገ ሰው የረባ መረጃ አያገኝም።ሰውየው ግን በግሉ ዘጠኝ አልበም ከሌሎች ጋር ተጣምሮ አንድ የሙዚቃዎች ጥቅል ብቻቸውን እየተብሰከሰኩ ለሚያደምጡት አድናቂዎቹ አቃምሷል።


ዘፋኙ ዓለምን በሥጋ ከተለየ በሗላ ዘፈኖቹን "You Tube"በተሰኘው የድምጽና ምስል መጫኛ የሰቀሉ በሚሊዮኖች በተጎበኙ የኪነት ሥራዎቹ ብዙ ዶላሮችን ሸቅለዋል።

እሱ እንዲህም እንዲያም ነው!

የዛሬው የሰንበት ወግ እንግዳ የሙዚቃን አክሊል በልዩ አዚያዚያም ተሰጥኦው ደፍቶ በአገሩ ሰዎች ልቡና ላይ የነገሰው አክሊሉ ስዩም ነው።

አንድ የዚህን ጠቢብ የሙዚቃ ጣዕሞች በድረ ገጹ ዘግኖ ለአድማጮቹ ያጋራ ጦማሪ ስለዘፋኙ  በብቸኝነት አራት አጫጭር አንቀጾች ወርውሯል።

ጦማሪው አክሊሉ ስዩምን"Aklilu Seyum was one of the most talented singers and songwriters from Ethiopia" ብሎ ይገልጸዋል።

እንደተባለውም አክሊሉ ታላቅ እና ተራቃቂ ዘፋኝ ነው።ዜማው እንደ ቀትሩ የጣና ሞገድ ለስለስ ብሎ በአዕምሮ ግድግዳ ላይ ይንሸራሸራል።ዚያዜም በሙዚቃ መሳሪያዎች ብቻ የሚደመጥ ሙዚቃ እንጅ ግጥም ገብቶበት የሰው ድምጽ የታከለበት አይመስልም።በዜማ ጣዕሙ ሲሳካለት ለታዘበ "ሰውየው የት ተወልዶ ቢያድግ ከየትስ የዜማ ጣዕም ቢቀዳ ይሆን?" ብሎ ይጠይቃል።

ብቸኛው ስለ አክሊሉ ስዩም የተፃፈው ጦማር እንደሚለው ይህ ጥዑም ዜመኛ ተወልዶ ያደገው በዜማ መዲናዋ ጎንደር ከተማ ነው።ጎንደር የዜማ ከፍታ ናት።

"በቆሜ አራራዩን ያላንጎራጎረ
ደብረ ታቦር ተክሌን ያላስመሰከረ
በአንዳቤት ቁም ጽሁፍ መካን ያልሞከረ
ጎንደር በአንች ሞያ ያልተወዳደረ
መቼ እንደተማረ ይቆጠር ነበረ!?"

የሚባልላት የ17ኛው ክፍለ ዘመን የዐለማችን የልህቀት ማዕከል በተለይ በተለይ ዜማ ባህላዊ ሀብቷ ነው።ዛሬም "አረጀች" እየተባለች በምትታማው ጎንደር ከተማ የተገኘ ሰው ወደ ማታ ከአበቅ የለሽ እስከ እንየ ታከለ ፣ከባላገሩ እስከ አንድ ሌላ አዝማሪ ቤት ብቅ ቢል የዜማን ጣዕም ከእኒያ ጠቢባን አዝማሪዎቿ ይልሳል።

አክሊሉ ስዩም እንዲህ ሲያዜም ከአባቶቹ፣ከአያቶቹ፣ከቅደመ አያቶች የዘገነውን ጥበብ እየደጋገመ እንጅ አዲስ ነገር ፈጥሮ አይደለም።

እሱን የሚያስደንቀው ያንን የአብርሆት ዘመን የጎንደር ጥበብ ከአርባ አራቱ አድባራት ቀድቶ ለራሱ ሥራ በኪናዊ ለዛ አሟሽቶ ማቅረቡ ነው።

ለአፍታ በምናብ ሶስት ዓመታትን ወደ ሗላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ገነተ ልዑል ቤተ_መንግስት እንመለስ።በእዚያ የዚህ ዝግጅት ቀማሚ የጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰርቶ በእጅ የምትያዝ ትንሽየ ሬዲዮውን ጮክ አድርጎ ከፍቶ ይጓዛል።

አንድ በዕድሜ ጠና፣በአቋም ፈርጠም ያሉ ፊታቸው የሚያበራ ጎልማሳ አስቆሙት።በትዝታ እጅግ እጅግ ወደሗላ ተመልሰው ነጎዱ።የዚያኔው የጋዜጠኝነት ተማሪ ባለ ሬዲዮ እያያቸው የትዝታ ጎርፍ በላቸው።

"ጋሸ ምን ሆነው ነው?" አላቸው።

"ከአክሊሉ ስዩም ጋር በኤርትራ ምድር አብረን ነበርን።እንዴት ያለ መልካም ሰው ነበረ መሰለህ? ጓደኛየ ነበር።ከእነ ጋሻው አዳል፣'አንች ወረተኛ'ን ከሚዘፍነው ዘፋኝ ጋር ይዘፍኑልን ነበር።"እያሉ ይብሰከሰኩ ጀመር።

አክሊሉ "ይሻገራል ይሻገራል ልቤ
            ናፍቆት ነው ቀለቤ"
የሚለውን ዘፈኑ አዚሞ ከሬዲዮው ሞገድ እየወረደ ነው።

ሻምበል ሳሙኤል ግን የትዝታ ክር እያጠነጠኑ  ከሃያ ዓመት በፊት መገንጠሏን አምነው ወደተለዩዋት አገረ ኤርትራ በሃሳብ ነጎዱ።

እናም አክሊሉ ስዩም በፖሊስ ኦርኬስትራ ስር ታቅፎ ማቀንቀን ከጀመረበት የ18 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች በናቅፋ፣አልጌና፣አፍአበት፣ሳህል ጦር ሜዳዎች ኤርትራን ከ"ገንጣይ አስገንጣዮች" ሊያድን ለሚዋደቀው የኢትዮጵያ ጦር እየሄደ ሳይዘፍንለት አልቀረም።

ሻምበል ሳሙኤል ሺህ መላሽ ለአዘጋጁ  ስለ አክሊሉ ስዩም እንደነገሩት አዲስ አበባ የምትኖር ልጅ አለችው።የኢትዮጵያዊያንን የፍቅር ትካዜ ለዓመታት በተለያዩ ርዕሶች ሲያዜም የኖረው አክሊሉ ስዩም አፍቅሮ፣ተፈቅሮ፣አስርጎ ስለማግባቱ ዝርዝር መረጃ የለንም። ሻምበል ሳሙኤል ግን ስለ አስገራሚው የፍቅር ታሪኩ የሚያውቁት አላቸው።

ብቻ ብቻ ዘፈኖቹ ብቻውን በናፍቆትና የሰው ረሃብን ሲሰቃይ የኖረ ኢትዮጵያዊ እሮሮዎች ይመስላሉ።ዜማዎቹም በአብዛኛው ተመሳሳይና በማይም ሰው አረዳድ አራራይ ቢጤ ናቸው።

አክሊሉ በዚች ምድር የኖረው አምሳ ስድስት ዓመታትን ብቻ ነው።በ1946 ተወልዶ በኢትዮጵያውያን የዘመን ቀመር 20ዐ2 ዓመተ ምህረት ዓለምን ተሰናበታት።

ይህን በሙዚቃዎቹ ልዕልና በአድናቂዎቹ ዘንድ በምስጢር የሚወደድ ዘፋኝ "አውቀዋለሁ"የሚሉ ዘፋኞች፣የሙዚቃ ስንኝ ቀማሚዎች፣አቀናባሪዎች ብዙ አይደመጡም።

ምናልባትም ከ1980ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት በሗላ ወደ እስራኤል አገር ስለሄደ ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት የ1970ዎቹ ዝነኛ ዘፋኝ ስሙ እየደበዘዘ መጥቷል።ቢሆንም ግን አክሊሉን ከዘመናቸው ጋር እያሰላሰሉ አድናቂዎቹ እየተመሰጡበት አሉ።

የዛሬን አበቃን

ከሰንበት ወጎች ጋር ነበራችሁ።ስለ ጣፋጩ ዘፋኝ በቅንነት የሚያውቁትን የነገሩንን የአሁኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፣የዚያኔውን የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሻምበል ሳሙኤል ሺህ መላሽን እናመሰግናለን!

@Gazetaw
218 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:10:46 የኢትዮጵያ ልጆች ሰቆቃ ቀጥሏል!





እኒያ ደጋግ ራያዎች ዳግም በሕወሓት እጅ መውደቃቸውን፣እየተፈናቀሉ መሆናቸውን አወቅን
403 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ