Get Mystery Box with random crypto!

የወሎው ዋርካ ምሬ ወዳጆ (በታመነ መንግስቴ) አጭር ነው።ወፍራም ነው።ልባም ነው።ደግ ነው።ጀግና | እዚህ ቤት

የወሎው ዋርካ ምሬ ወዳጆ

(በታመነ መንግስቴ)

አጭር ነው።ወፍራም ነው።ልባም ነው።ደግ ነው።ጀግናም ነው።

"መተኮስ እንጅ መናገር አላውቅበትም።ራስህ ቆርጠህ ቀጥለው።"የሚሉት ቃላት የእሱ ናቸው።

ከሰሞኑ የራያ ተስፋ እሱ ነው።የፋኖነት አርማ ሆኗል።ስሙ ምህረት ወዳጆ ይባላል።ሲያቆላምጡት ምሬ ወዳጆ ይሉታል።"አባ ስበር"በሚሰኝ ቅጽልም ያሞካሹታል።"ዋርካው" ዋንኛ ቅጽል መጠሪያው ነው።

ከአምስት ወራት በፊት ወሎ በኮምቦልቻ እና ደሴ መካከል ቃለ_መጠይቅ አድርጌለታለሁ።አረጎ ገደል ላይ ሆነን የአሁኑን ፈርቸ ስለ መንግስት ዝንጉነት አነሳሁበት፦

"መንግስት ዘነጋ አልዘነጋ የራሱ እቅድ ይኖረዋል።ግን ሕዝብ ራሱን ማንቃት አለበት።ዝም ብለህ ከምትሞት ታግለህ መሞት ጽድቅ ነው"አለኝ።

"የአማራ ፋኖዎች ከተማ ለከተማ እየተዘዋወሩ ሕዝብ ያስቸግራሉ ይሏችሗል" አልኩት።መልሱ ውስጥ ቁጣ አልነበረም።የነበረውን ሐብት እንዴት ጥሎ ወደ ትግል እንደተቀላቀለ፣አገር ሰላም ቢሆን ኑሮ እና አኗኗርን እንዴት እንደሚያውቅባት ነገረኝ።

ምሬ ወዳጆ ተወልዶ ያደገው በራያዎቹ መዲና ቆቦ ከተማ ነው።የራያ ሰው የፍቅሩን ያህል ጠቡ መራራ ነው።ምሬ ወዳጆም የማረካቸውን የሕወሓት ተዋጊዎች ተንከባክቦ የማስቀመጡን ያህል ምሽግ ሲሰብር ምድር ያናውጣል።

ደግሞም ፋኖው እንደ ወንድ ልጅ መታሰር መፈታትን ያውቃታል።ከዓመት በፊት ወልዲያ ታስሮ በመጋቢት ወር 2013 ዓመተ ምህረት ተፈትቷል።

እንደተፈታ በመንግስት ላይ ቂም አልያዘም።"ስለ እነርሱ ተው"ሲል ጋዜጠኛው ስለ አማራ ክልል ባለስልጣናት ሲያነሳበት በዝምታ ያሳለፈው ልባም የልቅስ መከላከያን ያደንቀዋል።