Get Mystery Box with random crypto!

'እኔ መከላከያ ሮጠ፣ሸሸ ብየም ወጥቶኝም አያውቅም።አሁንም አይወጣኝም።የሰራውን ገድል ስለማውቅ።ታሪ | እዚህ ቤት

"እኔ መከላከያ ሮጠ፣ሸሸ ብየም ወጥቶኝም አያውቅም።አሁንም አይወጣኝም።የሰራውን ገድል ስለማውቅ።ታሪክ ሰርቷል።በሚገባ ከአማራ መሬት ላይ የትኛውም ብሔር ወድቋል።" የሚለው ሳተና ፋኖ ስለ መንግስት አካላት ክፉ መናገር አይወድም።

ጀግና እና ሞት እንደተቃቀፉ ነው።ከመይሳው ካሳ እስከ በላይ ዘለቀ፣ከሰላሌው ጀግና አቢቹ እስከ አሁኑ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ድረስ ሞትን ያልናቀ ሰው አገሩን አያስከብርም።ዋርካው ስለሞት እንዲህ ይላል፦

"ፈሪ ከሞት አይድንም  ያችው ሞት ከመጣች ከሶስት ክንድ ጉድጓድ የሚድን የለም።"

"መከላከያ የብቻው እዳ የለበትም" የሚለው ምሬ ወዳጆ ስለ ሕወሓት ሰሞነኛ ማዕበል ሲናገር"እሱም በሕዝብ ማዕበል ነው እየቀለደ ያለው።እኛም በተደራጀ ኃይል አገራችንን ነፃ እናወጣለን!"

ብሏል።

የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ልጆች ጀግና ሲጠሩ ዘመነ ካሴ፣መሳፍንት ተስፉ፣እስራኤል እሸቴ ወዘተ ብለው ምሬ ወዳጆ ማለታቸው አይቀርም።እኔም ይህንን ከአልውሐ ድልድይ እስከ ሆርማት ወንዝ፣ከጉባላፍቶ ተራሮች እስከ ግራ ካሶ ተራራ እየተስፈነጠረ ትውልዱን ከጥቃት የሚታደግ ወዶ ዘማች ሕይወት የዳሰስኩበትን ዝግጅት ለጊዜው አከተምኩ።

በድል ያገናኘን