Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @gazetaw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.02K
የሰርጥ መግለጫ

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም
ኢትዮጵያዊ ሆነን —የሚያግባባ አናጣም!
ዕወቂው ዐለሜ__‼
ኢትዮጵያዊ መሆን —የውርስ እንቁጣጣ
በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ!
(ታመነ መንግስቴ_አባ ወራው)
ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል ና ጥበብ እናወጋለን!
ጀበናዋ ተጥዳለች—ስኒዎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም!
ክህሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ።
ትውልድ❤

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 20:53:08
ጋዜጠኝነት ነገ ይመረቃል!

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

አየለ አዲስ ይባላል።ሞያው የገባው ጋዜጠኛና የጋዜጠኝነት ምሁር ነው።ክብሩን ያበላሸ ሁሉ ለሚወራጭበት የጋዜጠኝነት ሞያ ፍቱን መድኃኒቱ ይህ ሰው ነው።

የማውቀው ምናልባትም ከአስር ዓመታት በፊት በአማራ ሬዲዮ ነው።በመሐል ጠፍቶብኝ ሳለ በወልዲያ መካነ አዕምሮ የጋዜጠኝነት አስተማሪ መሆኑን ሰማሁ።

በሕዳር ወር 2013 ዓመተ ምህረት ደውሎ ያንን ተናፋቂ ድምጹ ሲያሰማኝና ተስፋ ያለኝ ወጣኒ መሆኔን ሲነግረኝ ደስታየ በዶዘር አካፋ ተዝቆ የማያልቅ ሆኖ ነበር።

ጋዜጠኛው፣አስተማሪው፣ተመራማሪው አየለ አዲስ ነገ ከባህር ዳር መካነ አዕምሮ ከእነ አቡነ ኤርምያስ(ወልዲያ ኪዳነ ምህረት ቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ስለ ሕወሓት ወረራ ጊዜ አጋጣሚዎቻቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተላለፈ እና ዝናቸውን ያናረ ቃለ_መጠይቅ

የሰጡት ልጅ ነኝ) ጋር በዶክትሬት ድግሪ ይመረቃል

ደስታህ የእኔ እና የትውልዴ ነው!


https://t.me/Gazetaw
583 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:38:49 አንድ ለአገሬ ደህንነት ስል ስማቸውን የምደብቀው የመከላከያ ሠራዊት ጓድ "በፍጹም አልነካናቸውም" ብለውኛል።

ለሁሉም የቤታችንን ዜና





ላይ ታደሙ
805 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:10:04 እነሆ ዜና



906 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 18:02:37 እነሆ የቤታችን ዜናዎች ናቸው



696 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 14:36:39 (በ በላይሁን ፍስሃ/ዝጎራ ቤል)

"ቂም! ጥላቻ! ካለነሱ መኖር አይቻልም? ተይ ልጄ ለውስጥሽም ሰላም ስጪው፡፡ ህመም እኮ ናቸው! ቂምና ጥላቻ፥ ግዴለም ይቅር እንተወዉ በፍቅር በሰላም እንኑር፥ ትላንትናችን ዛሬያችንን እንዲያበላሽ እድል አንስጠዉ! ልጆችም እኮ ወላጆቻቸው ተከታትለው  ካልቀጧቸው ካልገሰጿቸው፥ ፈተናዎቻቸውን ለማለፍ ይከብዳቸዋል።"

----ከምዕራፍ 4 ክፍል 7 የተወሰደ


እረኛዬ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከጅማሮው እስከ ፍጻሜው ከከፍታ ሳይወርድ፥ ተቋጨ።

ህዝቡን አስነባዉ! ኢትዮጵያዊ ለገጸ-ባህሪ አነባ! ንባቱ #እናና በመሞቷ ብቻ ሳይሆን፥ መልካምነቷን ተመልክቶ ነው። ኢትዮጵያዊ ልቡ እንደዚህ ነው! ሰዉ ያለበደሉ ሲገፋ ማየትን አይሻም። የማያዉቀው ሰዉ ለቅሶ ላይ እግር ጥሎት ቢገኝ፥ ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ የሚያስለቅስ ህዝብ ነው!

አሁን ላይ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ አይቶ ሁሉን መካድ፥ ህዝቡን በጭራቅ መመሰሉ ስሁት አካሄድ ነው። ኢትዮጵያዊ እኮ ለገጸ-ባህሪ አለቀሰ! የተጋጨን ቢመስለን፥ እህል ዉሃችን ያከተመ አርገን ብንቆጥረው፥ እርስ በርሳችን እሳትና ጭድ የሆንን ያህል ቢሰማን… ቀን አለ! ቀና የምንልበት፥ የምንደጋገፍበት። ምክንያት ካላችሁኝ ኢትዮጵያዊ እኮ ልቡ የዋህ ነው የዛሬን የቁርሾ እርሾ አሽቀንጥሮ ነገ ላይ በሰላም ሊኖር የሚችል፥ ለገጸ-ባህሪ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰ ህዝብ ነው።


ወደ እረኛዬ ስመለስ:-

አሁን ላይ ስንተኛዉ ክፍል ላይ እንደሆነ ባላስታውስም፥ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ድራማውን አይቼ እንደጨረስኩ የጻፍኳት ጽሁፍ ነበረች። እንዲህ ትላለች:-

*****

(በ በላይሁን ፍስሃ/ዝጎራ ቤል)

ሳያት ደምሴ (እናናዬ):-

"ጥበቧ ት/ቤት እየገባችብኝ አስቸግራኝ እሷን መልሻት መምጣቴ እኮ ነው፡፡"

መዓዛ ታከለ(ማስረሻ):-

"እናናዬ ታዲያ እኮ ጥበቧ ት/ቤት መግባቷ እኮ ጥሩ ነው፥ጥበብን ፈልጋ ነው፡፡
እሷ ከዚያ ጠፍታ አይደለም እንዴ የተሸበርነው!?"

የሚገርም ቅኔ! ትክክለኛ አገላለጽ!

"እረኛዬ" ተከታታይ ድራማ ማስደመሙን ቀጥሏል፡፡ ከርዕሱ ብነሳ #እረኛ የሚለው ቃል ብቻውን ህልቆ መሳፍርት የሌላቸው ትርጉሞችና ምሳሌዎች ያሉት ሦስት ፊደል የያዘ ቃል ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያክል:- ጠባቂ፥ መሪ፥ አቅጣጫ ጠቋሚ፥ አራቂ፥ ዘብ፥ ወዘተ…

በእረኛ ከሚመሰሉ ጥቂቶቹ ደግሞ:- #እግዚአብሔር (በክርስትና ዕምነት እንደሚታወቀው)፥ የሀገራት መሪዎች፥ የጥበብ ሰዎች(መልካም የሆኑ ልማዶችን ህዝብ እንዲያተኩርባቸው አጽንዖት በመስጠት)፥ መምህራን፥ ግለሰቦች(ራስን መግዛት መቻል ወይም ራስን ወደ ትክክለኛ መንገድ መምራት መቻል) ወዘተ………

ስለ ርዕሱ ይህችን ታክል ካልኩኝ ከላይ መግቢዬ ላይ ከትዕይንቱ ላይ ቀንጭቤ ወደወሰድኳቸው ዓ.ነገሮች ልለፍና የተወሰነ እንድል ይፈቀድልኝ

አመሰግናለሁ!!!

#ጥበብ ለአንድ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ዕድገት(መሻሻል) ጉልህ ሚና እንዳላት መናገሩ ለቀባሪ እንደማርዳት ነው ብዬ አስባለሁ(4ቱ ባህሪያተ ስጋ እና 3ቱ ባህሪያተ ነፍስ ለተቸረው ሰው ለሆነ ሰው ሁሉ)፡፡
ነገር ግን አውቆ ጥቅም ላይ ማዋልና አውቆ ዝም ማለት ለየቅል እንደሆኑም መረዳቱ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡

የቀደሙት አባቶቻችን የጥበብን ጠቀሜታ በአግባቡ ተረድተው በተግባር ሲከውኑት ኖረዋል በተለያዩ አስቻይ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው፡፡ ደመናን ጠቅሰው ከቦታ ቦታ ይጓጓዙ እንደነበር እንሰማለን(ሐሽማልን ያነበበ እጅ ያውጣ እስኪ ) ከነገራችን ጋር(ከታሜ እንደተዋስኳት ይሰመርልኝ) ስለጦርነት ሲነሳ አባቶቻችን፥ ስለጥበብ ሲነሳ አባቶቻችን፥ ስለ ሀገራችን ጥንተ ገናናነት ሲነሳ አባቶቻችን ወዘተ…… ስቅታ ገደልናቸው እኮ እኛስ ባለፈው መኩራትን ብቻ ጀብድ አድርገን ታሪክን ሳንሰራ ታሪክ በመጥቀስ ከተሰፈረልን የዕድሜ ዘመን እየቀነስን የምንኖረው እስከ መቼ ነው???

በዘመናችን ትምህርትና ጥበብ እሳትና ጭድ የሆኑ ያክል ት/ቤቶቻችን ጥበብን ተጠይፈው #ሸምድደህ ትፋው(ታመነ መንግስቴ እንደሚለው) ቲዎሪዎችንና የባዕዳንን አሰስ ገሰስ ቆልለው ትውልዱን አስገድደው እየደፈሩት ነው ብል ቀለል አድርጌው እንደሆነ እንጂ ያጋነንኩት አይመስለኝም፥ ከዚህ በላይ ገላጭ ሐረግ ባገኝ ደስ ባለኝ ነበር!፡፡

እናማ ሀሳቤን ጠቅለል ለማድረግ ያክል እየዘራን ያለነው ዘር(አረ ምንባላበትን እያልኩ አደለም ሆይ መቼም ህዝቤ #ዘር የሚለውን ቃል ሲሰማ 5ቱ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ የፈጠራቸውንም የስሜት ህዋሳት አቁሞ ነው ሚሰማህ)፥ እየበቀለ ያለው ቡቃያ፥ እያጨድን እና እየከመርን ያለነው ነዶ፥ እያስፈጨን ያለነው እህል፥ እያቦካን እና እየጋገርን የምንበላው እንጀራ ወዘተ…… እያቃረን ለጤናችንም ለመንፈሳችንም ሰላም ያልሰጠን #ጥበብ ስጋዎቿ ከሆኑት ት/ቤቶቻችን ተነጥላ እርቃኗን ስለቀረች ነው፥ ፈላጊና ተፈላጊ የፍየልና ቅዝምዝም ሁኔታ አጋጥሟቸው ነውና ልብ መለቱ አይከፋም፡፡ እናስተውል፡፡

ቸር ሰንብቱልኝ እረኛዬን ተመልከቱ እንጂ አትዩ(የሁለቱን ልዩነት መቼም አይጠፋችሁም፡፡)


22/10/2013 ዓ.ም"
*****
ከዓመት
በኋላ ፍጻሜዉን ያገኘዉ ይህ ተከታታይ ድራማ በብዙ መመዘኛዎች ጥበብን ከሰገነቷ ላይ ተደላድላ እንድትቀመጥ የበኩሉን የተወጣ ድንቅ ድራማ ነበር።

ድራማዉን መመልከት ብቻውን መጽሃፍ የማንበብን ያህል፥ ጥልቅ መልዕክቶችን ያዘሉ ቃለ-ተውኔቶች የድራማው ጌጦች ነበሩ። የደራሲዎቹን አቅም ግልጥ አድርጎ ያወጣም ድርሰት ነበር። እርግጥ ነው፥ ከዚህ በፊት የሰሯቸዉ ሌሎች ስራዎቻቸው ደራሲዎቹ ጥበብን ምን ያህል እንደተጣቧት ያስመሰከሩ ነበሩ። ይህ ግን ለእኔ የተለየ ነበር።

ብዙዎች እንደሚሉት "አብነት መንደር" የሀገሬ ቁርጥ ወካይዋ ነበረች። ሳቢና ጎታቹን፥ አሳቢም ተጋላቢም፥ ቂምም ርህራኄም … ሁሉን በአንድ የያዘች መንደር!

በትወናው ረገድ "መስለው ሳይሆን ሆነው" መስራትን የተካኑ የሀገራችንን ድንቅ ድንቅ ተዋንያኖች የያዘ፥ በእግር ኳሱ "የሞት ምድብ" እንደሚሉት አይነት ብዙ የሚችሉና የተጨበጨበላቸውን ተዋንያኖች በአንድ የያዘ ድራማ!

የሳያት ደምሴ(እናና) እረኝነት፥
የድርብ ወርቅ እናትነት፥
የጋሽ ፍቅረኢየሱስ(አባ ሳህሉ) አዋቂነት፥
የመዓዛ ታከለ ስነ-ቃልን አሽሞንሟኝነት፥
:
:
ስንቱን እናውራው? የእነ አማኑኤል ሃብታሙ፥ ሱራፌል ተካ፥ ቃልኪዳን ጥበቡ(የግሌ ተወዳጅ)፥ አበበ ባልቻ(አስናቀ/ሽፈራዉ)…የጋላክቲኮስ ስብስብ ነበር፡፡

እማም ቸርነት(ቸሬክስ) የሚናገሩት እያንዳንዱ ቃል ራሱን የቻለ ትምህርት ነበር!

የኩራባቸዉ(ጣሰውን) እና ወላንሳን ትወናንም ሳያነሱ ማለፍ እንዴት ይቻላል? የምር እስክጠላቸው ድረስ ሆነው ነበር የሰሩት።

አበበ ባልቻ(ሽፈራው) አርፍደው የድራማው ማለቂያ ላይ ቢመጡም ልምዳቸውን ተጠቅመው ነጥብ አስቆጥረዋል!

የቃቆን ቅልጥፍና የታከለበት ተላላኪነትስ እንዴት ይዘነጋል።

"ወደ ኋላ የምንመለከተዉ፥ ምን ያህል እንደመጣን ለማየት እንጂ ለመመለስ መኾን የለበትም!"

ጉዞ ወደ ፊት

አበቃሁ!!!
595 viewsዝጎራ ቤል 🇫 🇮 🇸 🇭, edited  11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 13:28:54 "እረኛየ" እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ!






ላይ ተዳሰዋል።ዲሽታ ጊናም አለ
762 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 22:39:32
"ሆድ ያባዉን…"

ዛሬ በሁለት ነገሮች ከልቤ አለቅስኩ! እንባ አውጥቼ እኮ ነው የሁለቱም ለቅሶዎቼ መነሻ "እረኛዬ" ድራማ ነዉ!


አንደኛዉ፥ በፍቅር ስከታተለዉ የነበረ አና ብዙ ትምህርቶችን የተማርኩበት ድራማ በመሆኑ እና ፍጻሜውን በማግኘቱ ሲሆን፥

ሁለተኛው ደግሞ፥ የድራማዉ አስኳል የሆነችዉ "እናና" መሞቷ ከማጀቢያ ሙዚቃው ጋር ተደምሮ ስቅስቅ ብዬ እንዳለቅስ አስገድዶኛል፡፡ ምን ምርጫስ አለኝና ላለማልቅስ፥ ሰዉ አይደለሁ!



#ቅድስት ይልማ የነካችዉ ድርሰት ግን እንዴት ነው ነገሩ?

"ረቡኒ" ላይ ዋናዋን ገጸ-ባህሪ ገድላ አስነባችን።

"እረኛዬ" ላይ እንደዚህ



#
248 viewsዝጎራ ቤል 🇫 🇮 🇸 🇭, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 17:06:52 ኧረ የሐረር "ራስ" የታሉ?





ላይ ጠይቀናል
834 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 16:38:59 የደብረ ታቦሯ ጸሐይ በደብረታቦር ዋዜማ ወጣች!




ውስጥ እንሙቃት
800 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 06:57:46
ነሐሴ 12 የወጡልን ፀሐይ፥
ለእኛ አብሪ ሲሆኑ ለጠላት አቃጣይ።




#እንኳን አደረሳችሁ!!!
255 viewsዝጎራ ቤል 🇫 🇮 🇸 🇭, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ