Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ gazetaw — እዚህ ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @gazetaw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.02K
የሰርጥ መግለጫ

አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም
ኢትዮጵያዊ ሆነን —የሚያግባባ አናጣም!
ዕወቂው ዐለሜ__‼
ኢትዮጵያዊ መሆን —የውርስ እንቁጣጣ
በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ!
(ታመነ መንግስቴ_አባ ወራው)
ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል ና ጥበብ እናወጋለን!
ጀበናዋ ተጥዳለች—ስኒዎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም!
ክህሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ።
ትውልድ❤

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-17 17:28:43 አቡነ ማቲያስ "አትምጡ ስንላቸው መጥተው አስደበደቡን" ብለዋል|ማወዛገብ የጀመረው የኢትዮጵያ የቀጣይ ዓመት ምርጫ|ሬዲዮ ጣቢያው ተዘግቷል።" በ


776 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 17:07:35 ስለ መስሪያ ቤት አጋራችን እንዳልክ በቤታችን ሰርተናል



764 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:20:13
ለሰዎቹ እጅግ በማፈር ላይ

https://t.me/Gazetaw
576 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:09:09 እንደምን አመሻችሁ ጓዶች?


በዛሬው እለት #EBC ያወጣውን የስራ ቅጥር ማስታወቂያ አይታችኋል?

ተስፋ የሚያስቆርጥ አይመስለኝም ጓዶች! እዚህ ቤት እሳት የላሱ ጋዜጠኞች አውቃለሁ! እድላችሁን ብትሞክሩ ባይ ነኝ!

ደህና አምሹ!
231 viewsMulat Amare Mekuria, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 19:49:06 ኢትዮጵያ ቅኔነቷ ለ ነው!



558 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:01:47 90s የሚል የፌስቡክ ፔጅ ላይ ነው ያገኘሁት! እናንተንም እንደኔ ወደልጅነታችሁ ከመለሳችሁ ተደመሙበት!

የልጅነት የኳስ ጨዋታ ህጎች!

1 ምንጊዜም ሰፈር ውስጥ ወፍራሙ ልጅ ጎል ጠባቂ ነው።

2 ሁልጊዜ ጨዋታ የሚያልቀው ሁሉም ተጫዋች ከደከመው ብቻ ነው።

3 አስር ጊዜ ጎል ስታስገባ ብትውልም የሚያሸንፈው መጨረሻ ላይ ጎል ያስገባው ቡድን ነው።

4 ዳኛ ቢኖርም በጩህትና በጭቅጭቅ ያሳመነው ያሸንፋል።

5 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት ካኮረፈና ከተበሳጨ ጨዋታው ያልቃል።

6 ሁለት ጎበዝ ተጨዋች አንድ ቡድን ውስጥ መጫወት በልጅነት ህግ የተከለከለ ነው።

7 ድንገት ተቃራኒ ቡድኑ ፔናሊቲ ካገኘ የኳሱ ባለቤት ከመቅፅበት ጎል"ጠባቂውን አባርሮ ራሱ ጎል ጠባቂ ይሆናል።

8 ኳሱ ፎሪ ወጥቶ የሰው ግቢ ውስጥ ከገባ ያስገባው ልጅ ሙሉቀንና ሙሉ ለሊት ሸፋፋ እየተባለ ሲሰደብና ሲረገም ይውላል።

9 ምንጊዜም በጣም ጎበዙ ተጫዋች የኳሱ ባለቤት ጋር አንድ ቡድን ናቸው።

10 ጨዋታው አንዱን ቲም ከተቃራኒው ለመለየት አንዱ ቲም ከወገብ በላይ ራቁቱን ይጫወታል።

11 ምንጊዜም ጨዋታ የሚጀመረው ኳሷን ወደ ሰማይ በመጠለዝ ነው።

12 አጥቂ ተከላካይ የሚባል የለም ሁሉም ያጠቃል ሁሉም ይከላከላል የደከመው ወገቡን ይዞ በረኛውን ያወራዋል።

13 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት FIFA በለው።

14 ኦፍ ሳይድ የለም ግር ብለህ ታጠቃለህ ግር ብለህ ትከላከላለህ ግሪሳ ሁላ።

15 ድንገት በጨዋታ መሃል እናትህ ከጠሩህ ሰው ተክተህ ትሄድና ስትመለስ የተካህውን ሰው አባርረህ ጨዋታውን ከቆምክበት መቀጠል ትችላለህ።

ጨምሩበት!
220 viewsMulat Amare Mekuria, edited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 23:47:58
የሰንበት ስንኝ

(ታመነ ነኝ)


በቁማችን ሌባ፣ደደብ እና አስመሳይ በሆንባት አገር
ይበልጣል መቃብር፤ሞቶ እንኳን ሲናገር!


ምስሉን ዲያቆን ሰለሞን እንየው አነሳው

https://t.me/Gazetaw
530 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:57:03
አፋልጉኝ

(ፈላጊ፦ታመነ መንግስቴ)

የ2006 ዓመተ ምህረት የአማራ ክልል የስምንተኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ወረቀት የምታገኙ በአድራሻዎቸ አሳውቃችሁኝ ለአጭር ጊዜም ሆነ ለዘለቄታው እንድትሰጡኝ ይሁን።

https://t.me/Gazetaw
207 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, edited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:01:54 "...እግዚያብሔር እንደ ኢትዮጵያ ጠባዩን የለዋወጠበት አገር የለም።በጎጃምና ሰላሌ ሜዳዎች ግንባታው ወቅት ወይ ቡና ጠጥቷል ወይ ሰይጣንን በጥፊ መትቶ ረክቷል።ብቻ በጣም ተደስቷል።የዐባይ ሸለቆን፣የሊማሊሞ ገደልን፣የሰሜን ተራራን ሲያንፅ ደግሞ ክፉኛ ተበሳጭቷል።"

የታመነ መንግስቴ የጥቅምት 27/ 2013 ዓ.ም "ከገጠር እስከ ሸገር" የተሰኘ የጉዞ ማስታወሻ ላይ

https://t.me/Gazetaw


በቃሉ እሱ ባለው

" ውድ ታሜ እነኚህ ዓይነት ቃላቶች ከጽሑፋዊ ውበታቸው ይልቅ ሰዋዊ ትርጉማቸው ብሎም ገሀዳዊ እውነታነታቸው አንድን አካል ጥልቅ የመሥራት ችሎታ እና አቅም ከመግለጣቸው በላይ የተገላጩን ገጽታ የሚያቀጭጩ ይመስላሉ ። አመክኖአዊ በሆነ መንገድም ሆነ በየትኛውም ሚዛን እውነትነቱን ከመቀበል በቀር ልናመሳክርበት የምንችልበት ምንም አይነት መንገድ የለንምና ።

አንድ ሳጥን ስድስቱንም ጎኖች ፣ ውሳጣዊ ደህንነቱን ሳናረጋግጥ እና ሳናይ ስለ ሳጥኑ ጤንነት መናገር እስካልቻልን ድረስ ብንናገርም መላ ምታዊ (thesis ) እስከሆነ ድረስ እርግጠኞች መሆን አንችልም ።

በተለይም ደግሞ ተፈጥሮ ላይ እነኚህ ነገሮች ልክ ናቸው አይደሉም ለማለት ነጻነት ያለን ሰዎች ብንሆንም የአጸፋው ግን ተጋቾች መሆናችን ምንም ጥርጥር የለውም ።

አንተ ጽሑፍ ላይ ያየያዝከው ነገር ላይ ምናልባት እንደዚህ አይነት ዐሳብ ያላቸው አንቀጾችን ተመልክቻለሁ ። ይህ ደግሞ ከሥነ ጽሑፋዊ ለዛነቱ ባሻገር እንደ አማኝም እንደ አንድ ታሪካዊ ማስረጃም ከመጽሐፍ ቅዱስ ዐሳብ ጋር የሚጋጭ መስሎ ታይቶኛል ።

መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን ቃላት ስለ ሥነ ፍጥረት በተነተነበት እና በገለጠበት መንገድ መልካም ሆኖ አየ፣ እጅግ መልካም ... እንደዚህ ዐይነት ውብ ቃላቶችን እያመዛዘነ ጸሐፊውም አጻፊውም ያቀረበልን ሁሉም ውብ እና እርሱ ያደረገው ሁሉ መልካም እንደሆነ ነው ።

ይህን ያልኩህ ምናልባት ለሥነ ጽሑፋዊ ለዛነት የተጠቀምከው ስለመሰለኝ ነው ። እውነትነትንም አብረህ ለማቅረብ እንዲሁ እንደወደድክ ሆኖ ስለታየኝ ነው ። ያ ደግሞ ከእንደ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ሰሪ ሰው ምናልባት ትልቅ እንቅፋት የሚፈጥር ዐሳብ ሆኖ ስለታየኝ ነው ።


( ዐሳብህንም ሆነ የፈለከውን በፈለከው መጠንና በፈለከው ነገር የመናገር ፣ የመጻፍ የመከተልም ሆነ የማራመድ መብትህን እንደማከብር ግን በትልቁ ይሰመርልኝ ። ይህ የመለስኩልህ ምላሽ ሃይማኖታዊ ጉኑ ምን ይመስላል የሚለውን አንገትህን ዞር አድርገህ እንድትመለከተው መሻቴ ነው ። )
240 viewsታመነ መንግስቴ ውቤ, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ