Get Mystery Box with random crypto!

አክሱም እና ትግራይ (ታመነ መንግስቴ ነኝ) የአክሱም ሥልጣኔ መበሻሸቂያ ሲሆን እንደማየት ቀ | እዚህ ቤት

አክሱም እና ትግራይ

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)


የአክሱም ሥልጣኔ መበሻሸቂያ ሲሆን እንደማየት ቀፋፊ ነገር የለም።ከሁሉም በፊት የ3ኛው ክፍለ ዘመን የፋርስ(Persia/ኢራን) ነቢይ ማኒ የሚለውን እናንብብ፦

"በዓለም ላይ አራት ትልልቅ ንግስናዎች አሉ።የመጀመሪያው የባቢሎንና የፋርስ ንግስና ነው፤ሁለተኛው የሮም ንግስና ነው፤ሶስተኛው የአክሱማዊያን ንግስና ሲሆን አራተኛው ደግሞ የቻይናዊያን ነው።"


አክሱም በዘመኗ የዓለማችን ሶስተኛዋ ልዕለ ኃያል አገር ነበረች።

ይህ ማለት ግን አሁን የአክሱም ሐውልቶች ያሉበት የትግራይ ክልል ሕዝብ ብቻ ስልጣኔን አይገልጽም።


ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በየካቲት ወር 2014 ዓመተ ምህረት ያነጋገርኳቸው ከዘጠኝ በላይ መጽሐፍትን የፃፉት መጋቤ ምስጢር ስማቸው ንጋቱ እንደሚሉት ትግራይና የአክሱም ስልጣኔ ግዴታ ሊገናኙ አይችሉም።


እንደ እሳቸው አመክንዮ የአዲስ አበባ ረጅሙ ሕንፃ የኦሮሞ ይሆን ዘንድ ግዴታ አይደለም!


https://t.me/Gazetaw