Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilkenema_sc_official — ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilkenema_sc_official — ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹
የሰርጥ አድራሻ: @fasilkenema_sc_official
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.59K
የሰርጥ መግለጫ

ወቅታዊ የሆኑ
#ዜናዎች
#ዝዉዉሮችን
እንዲሁም
#የቀጥታ ስርጭት
አስተያየት ለመስጠት እና ለጥቆማ
➠ @empair_bot
አንጋፋውና ተወዳጁ ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ1960 ዓ/ም ተመሰረተ። ይህ አንጋፋ የአፄዎች ክለብ 55 አመታትን አስቆጥሯል፡፡
#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም በላይ ነው!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 20:27:33 “በጀመርነው ፎርማት ውድድራችንን እንቀጥላለን” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 ኮከቦቹን በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው።

ከሽልማት ስነ ሥርዓቱ አስቀድሞ የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ተነስቶላቸዋል። በዋናነት ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን በተከታዩ መልክ አቅርበንላችኋል፡፡

በቀጣዩ ዓመትም ውድድሩ በተመረጡ ሜዳዎች ስለመደረጉ

“በሚቀጥለው ዓመት ሊጉን በጊዜ ለመጀመር አስበናል፡፡ የተቀመጠውን መለኪያ ያለፉ ስታዲየሞች ፣ የተቀመጡትን መስፈርት ያሟሉ ሆቴሎች ፣ በተጨማሪም መለኪያውን ያለፉ የልምምድ ሜዳዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ከምንም በላይ ፀጥታው የተጠበቀ አካባቢን ነው የምንፈልገው ስለዚህ እነዚህ ባሟሉ ቦታዎች በጀመርነው ፎርሙላ ውድድራችንን እንቀጥላለን፡፡

በመጨረሻ ጨዋታዎች ስለነበረው የጨዋታ መላቀቅ ቅሬታ

ገና ነው አላለቀም፡፡ ማች ፊክሲንግን ለማጣራት እና ዕርምጃ ለመውሰድ ረጅም ጊዜ ነው የሚፈጀው ፤ እውነቱ እስኪታወቅ ድረስ። ታውቃላችሁ ጣሊያን ውስጥ የተፈጠረውን ፤ የጣልያን ፌዴሬሽን አይደለም ያጋለጠው ፤ አንድ ጋዜጠኛ ነው ማስረጃዎችን አውጥቶ ክለቦች እንደዲቀጡ ያደረገው። እኛም ሀገር እንደዚህ አይነት ሁኔታ መከሰቱን ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች አሉ። ነገር ግን እነኚህን ጥርጣሬዎች በህግ እና በደንብ ተቀብለህ በጥርጣሬ ብቻ እርምጃ አትወስድባቸውም። ለማንኛውም ሁለት ነገር አለ፡፡ ይሄ አሁን ያለው ሁኔታ በቻልነው መጠን ለማጣራት እንሞክራለን፡፡ ሁለተኛ ከዚህ ሂደት ተነስን የሚቀጥለው ዓመት ምን እናድርግ ፤ ደንባችን ውስጥ ምን እንክተት ፤ ምን አይነት ህግ እንቅረፅ የሚለውን እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት እኔ ሳስበው አሁን አስራ አራተኛ ፣ አስራ አምስተኛ እና አስራ ስድስተኛ ወጥታችዋል እናንተ ትወርዳላችሁ የሚለው ብቻ አያስኬድም። ወደፊት ወራጆች እንዴት ይውረዱ የሚለው እጅግ አሳሳቢ ጥያቄ ነው፡፡ እሱን በቀጣይ በህግ አጥብቀን ተቀባይነት ሲያገኝ ወደ ራሳችን ጠቅላላ ጉባኤ አቅርበን ደንባችን ውስጥ አካተን በዛ እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡

በቀን ስለተደረጉ ጨዋታዎች

“ባለን ተጨባጭ ሁኔታ ስታዲየሞቻችን መብራት ቢኖራቸው የአካባቢው ሁኔታ የተረጋጋ ፀጥታ ቢኖረው በማታ ማጫወትን እንመርጣለን፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ስታዲየሞቻችን የማታ መብራት የላቸውም በተለይ የባህርዳር ከዛም አልፎ ደግሞ መብራት እንኳን ቢኖርም ደግሞ ተመልካቹ ህዝብ አምሽቶ ጨዋታ ቢያይ ምን አይነት የደህንነት ሁኔታ የተረጋገጠ ነገር አለ የሚለው ለእኛ የለም። ስለዚህ ከእነኚህ ከእነኚህ ሁኔታዎች ተነስተን ውድድሩ አራት ሰዓት እና ሰባት ሰዓት መርጠናል። ሌላ ምንም አማራጭ የለንም፡፡


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
383 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:23:42 በ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው ከሰባት ሚሊየን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ( 7,696,373 ) ብር እስከ አስር ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ዘጠኝ ( 10,994,819 ) ብር ተበርክቶላቸዋል ።

በተጨማሪም ውድድሮቹን በማስተናገድ ላይ ለነበሩት ለአምስቱም ስታድየሞች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሚሊዮን ( 2,000,000 ) ብር ተበርክቶላቸዋል ።


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
364 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:23:39 #UPDATE

የዘንድሮው የውድድር ዓመት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን የከፍተኛ ግብ አግቢነት በአስራ ስድስት ግቦች ያሸነፈው ይገዙ ቦጋለ የ 200,000ሺህ ብር አሸናፊ ሆኗል ።


ይገዙ ቦጋለ ሽልማቱን ከተበረከተለት በኋላ ባደረገው ንግግር የሲዳማ ቡና ስራ አስኪያጅ ፣ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ፣ የክልሉን ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም ወላጅ እናት እና አባቱን ከልብ አመስግኗል ።

#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
355 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:46:15
ሰኔ 30 አስቀያሚዋ ቀን
ስቃይ እንግልት ዱላ ዝናብ ፀሀይ እርሃብና ውሃ ጥም ይሄ ሁሉ በአንድ ቀን

#ለፋሲል ከነማ በጣም የማይረሱ 2 ዓመታት

ለፋሲል ከነማ ቡድን በጣም የማይረሱ 2 ዓመታት የፍፃሜ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 30/2011 ዓ.ም በመቀሌ ከነማ የዋንጫ አሸናፊነት የተጠናቀቀው እና የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም በቅዱስ ጊዮርጊስ የዋንጫ አሸናፊነት የተጠናቀቀው
በ2ቱም ዓመታት 2ኛ ሁነን ነው ውድድሩን የጨረስነው
እኛም ዋንጫውን ለመብላት ጫፍ ደርሰን ሿሿ የተሰራንበት
የ2011 ዓ.ም የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ መቀሌ ከነማን አሳምነን ረተን የዋንጫው ባለቤት ሁነናል ዘንድሮስ?

#ለታላቁ_ፋሲል_ከነማ_የተከፈለ_መስእዋትነት

ሁሌም_ድል_ለአፄዎቹ

ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው!!!


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
495 views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:05:37
#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
483 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:44:39 #ቀጣዮን_የውድድር_ዘመን_ከተስፈኛ_ልጆቻችን_ጋራ

#እኛ ደጋፊዎች ያለፈውን ዓመት በዬሄዱበት ሄደን ደጀን: ወኔ: ተጨማሪ አቅምን የፈጠርን በውድድሩ ዓመት መጨረሻም ጀግኖች ልጆቻችንን በማመስገን : በደማቅ አቀባበል በማንገስ እንደቋጨን (እንደደመደምን)ሁሉ ለቀጣዮ ዓመት ደግሞ በክለባችን ላይ በአንክሮ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጦት ሊሰራ ስለሚገባ የሁሉም ደጋፊ ቀዳሚ አጀንዳ: ፍላጎት የሆነውን የስራ ዘርፍ ለክለባችን የበላይ ቦርድ አባላት: ለክለቡ ፕሬዘዳንት: ብሎም የ2015 የቡድኑ ኮቺንግ ስታፍ በሙሉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

#በቀጣዮ ዓመት ለስኬት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሚደረጉ ዝግጅቶች ዋነኛው በዝውውሩ መድረክ ክለቡ ንቁ ተሳታፊ መሆኑ የታወቀና እርግጥ ቢሆንም ይህ የዝውውር እንቅስቃሴ በቢጫ ተሴራ ላይ ያሉ ብሎም አሁን ለሚጨመሩ የተስፉ ቡድኑ ግብአት የከተማችን ፍሬዎች : ከድጋፍ ጀምሮ ልባቸው ውስጥ ከልጅነት እስከ እውቀት ፋሲልን አትመው ላደጉት : እስትንፋሰ ፋሲላዊ : የክለባችን ታማኝ ተረካቢ: እንቁ ልጆቻችንን #የሚገፉ #የሚጫን ሊሆን እንደማይገባ የዝውውሩ ሂደት እኛ ደጋፊዎች በአፅዕኖት መናገር እንወዳለን።

#ከዛም በላይ አቅማቸው የተሻሉ መሆናቸው እየታመነ ከተቀያሪ ወንበር ሳይነሱ ዓመቱን የሚጨርሱበት መንገድ በስንት አስቸጋሪ የከተማ ዕድሜ ዕርከን ውድድር እስከ አሰልቺ የፕሮጀክት ስልጠና እዚህ የደረሱ ልጆቻችን ከአቋም ዝቅ እያደረገ: በስነልቦናም እያዘቀጠ : በቁጥርም እያመነመነ : አቅም ችሎታቸው ላይ ተፅዕኖን እየፈጠረ መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ለቀጣይ የውድድር ዘመን አቅማቸውን የሚያሳዩበትን በቂ የመጫወት ጊዜ እንዲያገኙ እንሻለን እፈልጋለን።
#በክልላችን :በከተማችን ጎንደር ተጫዋቾች በቅለው በብሔራዊ ቡድን እና በፕሮፌሽናል ደረጃ የማይታዮበትም ምክንያት ክለቦቻችን ለታዳጊ የሚሰጡት አነስተኛ ትኩረት መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ከሌሎች ክልል ቡድኖች አንፃር በፋይናንስ የተሻልን ሆነን ሳለ በታዳጊ ማብቃት ደረጃ ደካማ የሆንበት ምክንያት በጥናት ተደግፎ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑንም ለመጠቆም እንወዳለን።

#ከተማችን ጎንደር ብዙ የመሰረተ ልማት ግድፈቶችን ከዕይታዋ ገለል አድርጋ ከጎዶሎው መቀነቷ ፈታ የምትቸረው የአብራኳ ክፋይ ክለባችን ምንም በሀገራችን እግር ኳስ ፎርማት ድክመት አትራፊ ሆኖ የገንዘብ ትርፍ ባይመጣም የከተማዋን ፍሬዎች: የህዝቡን አካል ታዳጊዎች በተሻለ በማብቃት ህዝቧን ሊክስ ይገባል ወደ ህዝቧም ክለቡ ሀፍቱን ሊያፈስ ይገባል የሚል አፅዕኖታዊ ጥያቄ አለን። እንጂ ከታዳጊ ያነሰ አቅምን ይዘው ከነሱ በላይ እየተከፈላቸው ቡድናችን ወደ ዝቅታ የሚመሩ ልጆችን ዕልባት እንስጥ ...ለቡና መጠጫ እንኳ የማይተርፍ ሳንቲም የሚያገኙ ታዳጊ ልጆቻችን ተጠቃሚ እና ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን መንገድ መፈለግ እንደ ቀዳሚ ስራ ትኩረት ቢደረግበት በሚል የኛ ደጋፊዎችን ዕሳቤ ለመጠቆም እንወዳለን።

ሁሌም እኛ ደጋፊዎች ትላንትም ነበርን ዛሬም አለን ሁሌም የጀርባ ደጀናቹህ እና አቅማቹህ እየሆን ለዘላለም አለን።

#የክለቡ ቀዳሚ ባለቤቶች እኛ ደጋፊዎች እስከሆንም ድረስ ድምፃችን ይሰማ። #በውስን ግለሰብ ፍላጎት ብቻ ክለባችን መመራት ሊያቆም ይገባል በሁሉም ውሳኔ የኛ ደጋፊዎች ፍላጎት ቦታ ሊያገኝ ይገባል።

#ዝንተ ዓለም ፋሲል ከነማ

#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
511 views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:44:34
482 views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:38:26
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ሰኞ ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ያቀናሉ።

በፋሲል ከነማ ደጋፊ ባለሀብት ቃል በተገባላቸው መሰረት በፈረንሳይና በግሪክ የተዝናኖት ግዜ ይኖራቸዋል።

አሰልጣኝ ስዩም ፋሲል ከነማን በ2013 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳ አድርገዋል።



#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
515 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:09:19
አለምነህ ዋሴ ከሳምንት በፊት
"ሀዘኔን ምገልጸው አሁን ለሞቱት አይደለም። ቀጥሎ ለሚሞቱት ነው ሀዘኔን ምገልጸው። በቁም እየሰሙ ለሚሞቱት ማለት ነው። ምንም የተለወጠ ሁኔታ የለም። the same thing እነዚህ ሰዎች ደሙን ጠርገው ወደ እርሻ ወደ ሱቅ ይሄዳሉ፡ until it happens again፡ አሁን እነሱ ናቸው በቁም እያሉ የማዝንላቸው፣ የሚሰሙኝ። እንደወንድም እንደወገን በጣም አዝናለው" ብሎ ነበር።

(አሁን ጥያቄው ቋሚውን እንዴት እናድነው ነው? ከምኑም ውስጥ የሌሉ ንፁሃን በማንነታቸው እየተጨፈጨፉ የመፍትሄ ያለህ! ማለት የለብንም? በሀገራችን ላይ ይህ ነውር ሲፈፀም መፍትሄ መጠየቅ የለብንም? እየሞተ ያለው ክቡር የሰው ልጅ ነው። ኢትዮጵያዊ ውድ ወገናችን ነው።

ይህን የምፅፈው መፍትሄ በጋራ እንድንፈልግ ነፍሴ ስቅዝ አድርጋ ስለያዘችኝ ነው። እንደ ሰው፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ስለታመምሁ ነው። ለሀገሬም ስለምሰጋ ነው። ለአማራ ያልሆነች ሀገር ለማናችንም አትሆንም። ኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ መድረሷ ያሳዝናል። አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋል።

ምን ተሻለን?

ክልሎች ልዩ ሀይላቸውን ልከው የወለጋን አማራ ይጠብቁ፣ ወይ ወደ ሌሎች ክልሎች ይጓጓዙ፣ ወይ ሁሉም ይታጠቁና አልሞትባይ ተጋዳይ ይሁኑ፣ ወይ ወደ ጎሮቤት ሀገራት ይሰደዱ፣ ወይ የተባበሩት መንግስታት ይረከበን፣ ወይ በቁማቸው አሁኑኑ RIP እንበላቸው? መፍትሄ )
706 views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:10:07 ሊግ ካፓኒው ለዛሬ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግራለሁ ባለው መሰረት የሚወሰኑ ውሳኔወችን አየጠበቅን ነው ሚዛናዊ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን


ከዛ በፊት
#ሸር ይደረግ
ከጨዋታው በፊትም በጨዋታው በኋላም ብዙ ትኩረትን የሳቡ የ30ኛው ሳምንት የኢ. ፕሪሜርሊግ ለሻምፕዮንና ላለመውረድ የነበሩ ክስተቶች፦
1. አዲስ አበባ ከተማ ከጊዮርጊስ የነበሩ ክስተቶች ስናይ
አዲስ አበባ ከተማ
-በቁጥር በረከት ያሉ ቋሚ ተጫዋቾች ተጠባባቂ ወንበር ላይ መቀመጣቸውና አሰልጣኙ ሲጠየቅ ያሳፈቸው መሆኑ
-አሰልጣኝ ጳውሎስ ከጨዋታው በፊት የፋሲልና ድሬደዋ ጨዋታን በተመለከተ ቅድመ ክስ ማስያዙ
-ጨዋታው ላይ ከአዲስ አበባ ተጫዋቾች እስከ ዳኛው ውሳኔ የነበሩ ትይንቶች
-አሰልጣኙ ቡድኑን የመሩበት ከወትሮው የተለየ የተነሳሽነት ማነስ
- ተጫዋች ሮቤል ያለቀሰበትና በጨዋታው ተጠባባቂ ስለሆነበት ምክንያት ከአሰልጣኙ ጋር ስለተነጋገሩበትና ሌሎች

2. ሀዋሳና አዳማን በተመለከተ በአመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳማዎች 3 ጎሎችን በ9 ደቂቃ ማስቆጠራቸው በኋላም ሀዋሳ በተከታታይ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠሩበትና ጨዋታው የተጠናቀቀበት መንገድ

3. ወደ ድሬደዋና ፋሲል ጨዋታ ስንመጣ፦
ጨዋታው እስከ 76ኛው ደቂቃ ምንም እንኳን ፋሲል 2 ለ0 ቢመራም ጥሩ የመሸናነፍ ፍላጎት የነበረበት ሲሆን ጊዮርጊስ 2 ለ0 መምራቱን ተከትሎ ከዋንጫው ፉክክር ውጭ የሆኑት ፋሲሎች የመጫወት ፍላጎት ማጣትን አጋጣሚ ድሬዎች በመጠቀም በ13 ደቂቃ ውስጥ 3 ለ 2 በማሸነፍ በሰላማዊ መንገድ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ነገር ግን ድሬደዋ ከነማ ሶስተኛውን ጎል ሲያስቆጥር የጊዮርጊስንና የአዲስ አበባ ከተማን ጨዋታ በአይነ ቁራኛ ሲከታተል የነበሩ ጥቂት የፋሲልን መለያ የለበሱ ተመልካቾች መጨፈራቸው ትኩረትን የሳበ ነበር። እዚህ ላይ ስለ Emotional እናንሳ አንዳንድ ፀሀፍት ስሜታዊነት መዳረሻው ራስን እስከ ማጥፋት ይርሳል ይላሉ ያውም በደል ተጨምሮበት ለዚህ ነው ደጋፊዎች ጨዋታው ላይ የተሰራውን ደባ በመረዳት ስሜታቸው ያዘዛቸውን ያደረጉ፤ ይህን ለመወንጀል ቦታው ላይ መሆን አይጠበቅም። ነገር ግን እነ መርጦ አልቃሽ ውስን የስፓርት ጋዜጠኛ በአለም ላይ ተደርጎ የማያውቅ በማስመሰል ፍፁም ሚዛኑን በሳተ መልኩ የክለባችን መልካም ገፅታ በማበላሸትና የወከለውን ማህበረብ እሴት፣ መገለጫና ማንነትን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ከፍተዋል።
ከዚህ በተጨማራ አወዳዳሪው አካል አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅና መዘገብ ሲገባው ሆን ተብሎ ውሳኔ ሰጭዎችን ጫና ውስጥ ለመክተት ዘመቻ አጠናክረው ቀጥለዋል።

#በመጨረሻም ፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ አወዳዳሪው አካል በህጉ መሰረት ውሳኔ እንዲሰጥ የማድረግ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡና ከውሳኔ በኋላ የፁሁፍም ሆነ የድምፅ ማስረጃዎችን በመያዝ የሚዲያ ህግ በሚፈቅደው መሰረት እነዚህን ተቋማትና መርጦ አልቃሽ ግለሰቦችን ለህግ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።

#ለደጋፊዎችና ስፓርት ወዳድ ማህበረሰብ በሙሉ በተለይ አዲስ አበባ አካባቢ ያላችሁ አስፈላጊውን ማስረጃ መሰብሰባችን እንዳንዘነጋ፤
ሁሉም ደጋፊዎች ከስሜት ወጥተን በተረጋጋ መንገድ ነገሮችን እንድንከታተል።

#እኛ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የሁሉም ክለብ ደጋፊዎች ተፎካካሪዎቻችን እንጅ ጠላቶቻችን አይደሉም።
#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ!!!


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
827 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ