Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilkenema_sc_official — ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ fasilkenema_sc_official — ፋሲል ከነማ (አፄዎቹ) እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club ™🇦🇹
የሰርጥ አድራሻ: @fasilkenema_sc_official
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.59K
የሰርጥ መግለጫ

ወቅታዊ የሆኑ
#ዜናዎች
#ዝዉዉሮችን
እንዲሁም
#የቀጥታ ስርጭት
አስተያየት ለመስጠት እና ለጥቆማ
➠ @empair_bot
አንጋፋውና ተወዳጁ ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ1960 ዓ/ም ተመሰረተ። ይህ አንጋፋ የአፄዎች ክለብ 55 አመታትን አስቆጥሯል፡፡
#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም በላይ ነው!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-06 10:00:44
ሐምሌ 15 እና 24 ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አራት (4) ተጨዋቾችን አስመርጧል።

#ያሬድ_ባዬ
#ሱራፌል_ዳኛቸው
#በዛብህ_መለዮ
#በረከት_ደስታ



#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
748 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:01:23
ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊወርጊስ
ንፅፅር

በ29 ጨዋታ ማን የተሻለ ቁጥሮች አሉት


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene



#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
832 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:29:06 ቀጣይ አመት በደንብ በኩል ማሻሻያዎች ይኖሩ ይሆን?

በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ የተለያዩ ችግሮች መስተዋላቸው ይስተዋላል።ከቅርብ ሳምንታት ብንጀምር እንኳን የሜዳ አመዳደብ ላይ የተነሳ ቅሬታን ማስታወስ እንችላለን።

ታዲያ አወዳዳሪው አካል በዘንድሮው የውድድር ዘመን የታዩ ድክመቶች በቀጣይ እንዳይደገሙ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያሰበው የውድድር ደንቡን ማሻሻል ነው። በዚህም መሠረት ይሄን የክረምት ወቅት ብሎም እስከ መስከረም ድረስ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አዳዲስ የተሻሻሉ ደንቦች በቀጣይ አመት በውድድሩ ላይ እንደሚተገበሩ ይጠበቃል።

የሰሞኑ ጉዳይ በአወዳዳሪው አካል እንዴት እየታቀኘ ነው?

ሌላው የሰሞኑን ጉዳይ በተመለከተ አወዳዳሪው አካል ከእለቱ ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ውይይቶችን ጀምሮ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ለመመርመር በነገው እለት የ3ቱ ጨዎታዎች ኮሚሽነሮች፣ ዋና ዳኞች፣4ተኛ ዳኞች እና ድሬደዋን፣ቅ/ጊዮርጊስን እና አዳማን በመላቀቅ ጠቅመዋል ተብለው የተጠረጠሩት የፋሲል ከነማ፣የአዲስ አበባ ከነማ እና የሀዋሳ ከነማ አሰልጣኞች እና የቡድን መሪዎች ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት የተጠሩትን አካላት አወዳዳሪው አካል በተጠናል የሚያነጋግራቸው ሲሆን ዛሬ ብዙም አጥጋቢ መረጃ ካልተገኘ ተጨማሪ ምርመራዎችን እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።
ከምርመራዎች በኋላም ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ቆራጥ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውንም ለማወቅ ችለናል።

ዳኝነትን በተመለከተስ?

ሌላው ዘንድሮ የታየው ክፍተት የዳኝነቱ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል፤ ይህንንም ለማሻል ያግዝ ዘንድ በአወዳዳሪው አካል ከተያዙ እቅዶች መካከል በክረምቱ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ባለሙያዎች የተለያዩ የብቃት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን ለሊጉ ዳኞች መስጠት ነው። ይህም ተግባራዊ ሊሆን ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን በቅርቡ ይጀመራል።  በተጨማሪም ደግሞ በቴክኖሎጂ ለመታገዝ የቫር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ከውጭ ድርጅት ጋር አወዳዳሪው አካል በንግግር ላይ መሆኑን መግለፃችን አይዘነጋም። አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ይሄንንም ከ2015 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ንግግሮች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የፎርማት ጉዳይ

ሊጉ ዘንድሮ እና አምና በተካሄደበት ፎርማት ነው መካሄዱን የሚቀጥለው።

ዘንድሮ ሊጋችን ከብሮድካስቲንግ ምን ያህል ገንዘብ ወደ ካዝናው አስገባ?

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ በዘንድሮው የውድድር አመት ከዲኤስቲቪ የቴሌቪዥን መብት ሽያጭ 4.25 ሚሊዮን ዶላር( ወደ 222 ሚሊዮን 54 ሺህ 467 ብር የሚጠጋ) ገንዘብ ወደ ካዝናው ማስገባቱን ለማወቅ ተችሏል።
Utopia


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene


#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
833 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 13:11:58
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል። ሐምሌ 15 እና 24 ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ22 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። በተጨማሪ ተጫዋቾቹ ሐምሌ 04 በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠቁሟል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)
በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና)
አላዛር ማርቆስ (ጅማ አባ ጅፋር)

ተከላካዮች

ሱሌማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ)
ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ)
አስራት ቱንጃ (ኢትዮጵያ ቡና)
ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከነማ)
ጊት ካትኩት (ሲዳማ ቡና)

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ከንዓን ማርክነህ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)
በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ)
በረከት ደስታ (ፋሲል ከነማ)
አማኑኤል ዮሃንስ (ኢትዮጵያ ቡና)
መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር)

አጥቂች

ቸርነነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ)
ብሩክ በየነ (ሀዋሳ ከነማ)
ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)


#የአፄዎቹ_ቤተሰብ_ይሁኑ
ግሩፕ
@fasilyene


#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው

@fasilkenema_sc_official
857 views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ